በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡
በክልሉ መንግስት የዘፈቀደ የጅምላ እስር መፈጸም ከተጀመረ ድፍን አራት ወራት ተቆጥረዋል ያሉት የድርጅቱ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታ በክልሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ ባለበት ሁኔታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታ ከማሳፈርም በላይ ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የመብት ተሟጋቾች ጭምር በጅምላ ታፍሰው በግፍ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ተጽዕኗቸውን ተጠቅመው ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የህግ የበላይነት ተረግጦ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ዓለም በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አይቶ እንዳላየ ማለፉን ሊያቆም ይገባልም ተብሏል፡፡
መንግስት በዘፈቀደ እያፈሰ በጅምላ ያሰራቸውን ሊለቅ ካልሆነም ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባላቸው የተጠያቂነት የህግ መስፈርቶች ክስ ሊመሰርትና በህግ ሊጠይቃቸው እንደሚገባም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡