ቪክቶር ቫልዴዝ ይናገራል ስለ ፋቲ የባርሴሎና ታዳጊዎች ልምምድ በሚያደርጉበት ቀን ፋቲ ይዞት የመጣው ጫማ እንደጠበበው ይመለከታል ምክንያቱም የጫማ መግዣ አልነበረውም ይህን ያየው ቪክቶር ቫልዴዝ ለፋቲ የመጫወቻ ጫማ በመግዛት ስጦታ አበርክቶለታል በፋቲ የእግርኳስ ህይወት ላይ አሻራ አስቀምጧል ቫልዴዝ
ፋቲ የዘር ግንዱ ከአፍሪካዊቱ ሀገር ጊኒ ቢሳው የሚመመዝ ሲሆን በዛው በጊኒ ነው የተወለደው በስድስት አመቱ ወደ ስፔን የመጣው እና በስፔን ግዛት በሆነችው የሲቪያ ከተማ ህይወት ጀመረ
2009/10 እዛው በሲቪያ ከተማ ሄሬራ ለተባለ ክለብ መጫወት ጀመረ በአመቱ ደሞ ለሲቪያ ከ2010 እስከ 2012 መጫወት ቻለ ድንቅ ችሎታውን ያዩት የላማሲያ መልማዮች በ2012 ለባርሴሎና አስፈረሙት በአስራ አንድ አመቱ
በአስራ ስድስት አመቱ ለዋናው ቡድን የተጠራው ታዳጊ የእግርኳስ እድገቱ ለብዙዎች አስገራሚ ነበር ለዚህም ነው ስፔኖች አጣድፈው ስፔንን እንዲመርጥ ያደረጉት
በጁላይ 24,2019 የመጀመሪያ ኮንትራቱን ለባርሴሎና እስከ 2022 ፊርማውን አኖረ የመጀመሪያ ጎሉን ከኦሳሱና ሲያስቆጥ በባርሴሎና ታሪክ ሶስተኛው በትንሽ እድሜው ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ሆነ
በዘንድሮው የውድድር አመት በሮናልዶ ኮይማን ስር የመጀመሪያ ተመራጭ መሆኑን በሚገባ እያሳየ ይገኛል
➪ለስፔን ብሔራዊ ቡድን በትንሽ እድሜው ጎል ያስቆጠረ የምንግዜም ታዳጊ ሆነ
➪በታላቁ የኤልክላሲኮ ጨዋታ ጎል
አስቆጠረ
➪በሻምፒዮንስ ሊግ ጎል አስቆጠረ
➪በላሊጋው በአምስት ጨዋታ አራት ጎሎች አስቆጥሮ የጎል ተፎካካሪ ሆኗል
ፋቲ እንደ በፊቱ ጫማ የሚገዛለት አያስፈልገውም ምክንያቱም ከናይኪ ጋር ኮንትራት ተፈራርሞ የናይኪ ተከፋይ እና አስተዋዋቂ ሆኗል
ታዲያ አንሱን ፋቲ ህልሙን አሳክቶ ያሰበውን ራዕይ እየኖረ ጥረቱን በሚገባ እየቀጠለ ወዳሰበው ስኬት እያመራ ይገኛል በባህሪው መልካም የሚባል ተጫዋች ነው እድሜው ገና 17 ሲሆን ብዙ የከፍታ ጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ድንቅ ታዳጊ ሲሆን የሊዬኔል ሜሲ አልጋ ወራሽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ጊዜው ገና ቢሆንም
አዘጋጅ እና አቅራቢ➪
@amangn@ahadusport1 @ahadusport1