بسم اللہ الرحمن الرحيم وبہ أستعين.
🌴ጾምን የሚያፈርሱ ነገሮች 🌴
1/ መብላትና መጠጣት እንዲሁም ምግብን የሚተካ መርፌና ጉልኮስ መውሰድ።
የመድሃኒት መርፌዎችንና የስኳር ኢንሱሊን መውሰድ ጾምን አያፈርስም፤ ሆኖም ግን ከተቻለ እነዚህንም ማታ ላይ ማድረጉ ይመረጣል።
2/ መጨረሻ ላይ ባያደርጉት እንኳ ጾምን ለማፍረስና ለመብላት ወይም ለመጠጣት እንዲሁም ሌሎችን ጾም የሚያፈርሱ ነገሮችን ለማድረግ መወሰን።
3/ የግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈጸም።
4/ ያለ ግብረስጋ-ግንኙነት እንኳ ቢሆን በራስ ፍላጎት ( ስሜትን የሚቀሰቅስ ነገር ደጋግሞ በማየት፣ ከተቃራኒ ጾታ ጋር በስሜት በማውራት፣ ብልትን በመነካካት ወዘተ) የዘር-ፈሳሽ ማስወጣት።
በተኛበትና ያለፍላጎቱ የዘር-ፈሳሽ የወጣው ሰው ግን ጾሙ አይፈርስም።
ልብ ይበሉ! ከዘር ፈሳሽ ውጪም ያሉ በስሜት መቀስቀስ ምክንያት የሚወጡ ፈሳሾችም ጭምር (መዚይ) ጾምን እንደሚያፈርስ ኢማም አሕመድን ጨምሮ የተወሰኑ ሊቃውንት ገልጸዋልና ይጠንቀቁ!
5/ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መፍሰስ።
6/ በዋግምት፣ ደም በመለገስና በመሰል መንገዶች ብዛት ያለውን ደም ከሰውነት ማስወጣት፤
ይህ በሊቃውንት መካከል ኺላፍ ቢኖርበትም ጾም ያፈርሳል በሚለው መሄድና መጠንቀቁ የተሻለ ነው።
🔸ለምርመራ ደም መስጠት ግን ችግር የለውም።
7/ ፈልጎና ሆን ብሎ ማስመለስ።
በመጨረሻም፥ ምራቅን መዋጥ ጾም አያፈርስም።
አኽታ ምራቅ ቆሻሻና ጎጂ ከመሆኑ አንጻር እሱን መዋጥ የተከለከለ ነው።
💥ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች በሙሉ ጾም የሚያፈርሱት:-
1/ ጾምን እንደሚያፈርሱ እያወቁ፣
2/ ረስተው ሳይሆን እያስታወሱና ሆን ብለው ካደረጉት፣
3/ ተገደው ሳይሆን በሙሉ ፍላጎት ከሆነ ብቻ ነው።
ረስቶ ወይም ባለማወቅ ወይም ተገዶ ከነዚህ አንዱን ያደረገ ሰው ጾሙ አይፈርስም። እንዳወቀ መታቀብና ጾሙን መቀጠል ብቻ ነው የሚጠበቅበት።
✍ ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
ረመዷን 6/1438 ዓ.ሂ
🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸
🌐
https://telegram.me/ahmedadem