እንደ አንድ አካል ተናበን፣ እንደ አንድ ልብ አስበን ጭካኔን ስሙን ጠርተን ልናወግዘው ይገባል።
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ከዘገየም ቢሆን ዛሬ በሀሩን ሚዲያ ያየሁት ዘገባ ልቤን ሰብሮታል። ሀገርና ማህበረሰብን በስነምግባርና በመንፈሳዊ ስብዕና አንፀው ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሚያፈሩ የሀይማኖች መሪዎችን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መግደል ትውልድን መግደል ነው።
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታላቁ አሊምና ሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም በሆኑት በሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የተፈፀመውም ይኸው ነው። ኢማማችን ከነበቤተሰባቸው ካገቱ በኃላ ለማስለቀቅ 2 ሚሊየን ብር የጠየቁ ቢሆነንም የሀይማኖት መምህር መሆናቸው እየታወቀ ከሰው ነፍስ ገንዘብን አብልጠው ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሊገደሉ ችለዋል።
ይህንን ጉዳይ ያለብሄር ልዩነት ፣ ያለ ሀይማኖት አጥር ሰብዓዊነት የሚሰማው የሰው ልጅ ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ ጉዳይ ነው። እንደዚህ አይነት አስደንጋጭ ክስተት ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ሲቪክ ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቆም ብለው እንዲያስቡበት ማድረግ ካልቻለ የልጆቻችን ነገ እና እኛም የቆምንበት ዛሬ ጥያቄ ውስጥ ነው።
እንደ አንድ አካል ተናበን፣ እንደ አንድ ልብ አስበን ጭካኔን ስሙን ጠርተን ልናወግዘው ይገባል። የሀይማኖት መሪን መድፈር ቀይ መስመር እንደሆነ የትኛውም አካል ማወቅ አለበት።መንግስትም፣ የሀይማኖት ተቋማትም እንዲህ አይነት እሴት ሲሸረሸር በዝምታ ሊያልፉት አይገባም።
መንግስት በሰላማዊ ዜጎች እና በእምነት አባቶች ላይ እየተፈፀመ ያለውን አረመኔያዊ ግድያ እና እገታ ለማስቆም ሊሰራ ይገባዋል:: የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የመንግስት ትንሹ ኃላፊነቱ ነው። ከኢማሙና ቤተሰቦቻቸው ግድያ ጋር በተያያዘ የሚመለከተው አካል ጉዳዩን አጣርቶ ለህዝብ እንዲያሳውቅ ጥሪዬን አቀርባለው።
በኢማማችን እና በቤተሰቦቻቸው አሳዛኝ ግድያ ሁላችን አዝንናል። አላህ ከሸሂዶች ይመድባቸው ዘንድ ዱዓችን ነው።