ነጃሺ ቲቪ በነባር እስላማዊ ሚዲያዎች ውህደት መመስረቱ ተበሰረ ።
(ነጃሺ ቲቪ :- ጁሙዓ ታህሳስ 25 ቀን 2017)
በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ የሚታወቁት እስላማዊ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ጄይሉ ቲቪ ፣ ቢላል ቲቪና መርከብ ሚዲያ ውህደት ፈጥረው ነጃሺ ቲቪን መመስረታቸውን ዛሬ በይፋ አብስረዋል ።
የሚዲያዎቹ ኋላፊዎች የሚዲያውን መመስረት ባበሰሩበት መግለጫ ሚዲያው በሀገራችን የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን አዲስ ሚዲያ መመስረቱንና የጋራ ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የእዝነት፣ የፍትህ ፣የአንድነት ተምሳሌት በሆነው ንጉስ ነጃሺ ስም በተሰየመው የነጃሺ ቲቪ ጥላ ስር ሚዲያዎቹ መሰባሰባቸውን የቴሌቪዥኑ ስራ አስኪያጅ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጀማል አህመድ ገልፆል ።
የቴሌቪዥኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ጃፈር ስዩም በበኩሉ ነጃሺ ቲቪ ይህን ጉዞ ሲጀምር ከፍተኛውን የታማኝነት ፣የሙያ ብቃትና የአገልግሎት ደረጃዎችን ለመፍጠር ሀብታችንን ፣ እውቀታችንንና አቅማችንን በማስተባበር ህብረተሰባችንን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ተዘጋጅተናል ብሏል።
ነጃሺ ቲሺ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በኢትዮ ሳት ስርጭት ይጀምራል ያለው የቴሌቪዥኑ የፕሮግራም ክፍል ሀላፊ ዓሊ አሚን ይዘቶቹንም በተከታታይ ማስተዋወቅ እንደሚጀምር ገልፆል ።