ቦብ ማርሌይ AKA ብርሀነ ሥላሴ
በነጮቹ አቆጣጠር 1977 አንዲት የተረገመች ቀን በደቡባዊ ለንደን በሚገኝ አንድ ፓርክ ውስጥ አንድ ዝነኛ ሰው ከጓደኞቹጋ እጅግ የሚወደውን እግር ኳስ እየተጫወተ ነበር። በጨዋታ መሃል በድንገት የተረገጠችው አውራ ጣቱ ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለተፈጠረው የህይወቱ መጥፋት ምክያት ሆነች።
በእግር ኳስ መሃል የተጎዳው አውራ ጣቱ ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ ካንሰርነት ተቀየረ። ዶክተሮች የካንሰሩን ስርጭት ለመግታት የእግር ጣቱ እንዲቆረጥ ሐሳብ አቀረቡ። እሱ ግን እምቢ አለ። የምከተለው የራስተፈሪያኒዝም ክቡር የሆነውን ሰውነቴን እንድቆርጥ አይፈቅድልኝም አለ። ዘሌዋውያን 21:5 ላይ “ራሳቸውን አይላጩ፥ ጢማቸውንም አይላጩ፥ ሥጋቸውንም አይንጩ።'' የሚለውን የመፅፍ ቃል እናስታውሳለን።
በህመም ላይ የነበረው ሰው ህመሙ ሳይበግረው እ.ኤ.አ. በ1980 Could you beloved እና Redemption Song የተካተቱበትን Uprising የተሰኘውን ዘመን ተሻጋሪ አልበም ለህዝብ አበረጀተ። በዚያው ዓመትም ሚላን ውስጥ ከ100ሺ በላይ አድናቂዎቹ የታደሙበትን ታላቅ ኮንሰርት አዘጋጅቶ አለምን አስደነቀ። በሙዚቃ የተረሳው ካንሰር ግን በአደገኛ ሁኔታ ወደ አንጎሉ፣ ሳንባው እና ጉበቱ እየተዛመተ ነበር።
ህይወቱን ለማራዘም ባደረገው የመጨረሻ ሙከራ ወደ ጀርመን ሃገር ተጉዞ ብዙ ወራትን በህክምና ቢያሳልፍም ካንሰሩ ግን ኦልሬዲ የማይቀለበስበት ደረጃ ደርሷል። ለመኖር ረጅም ጊዜ እንደሌለው የተረዳው ሰው የመጨረሻ ዘመኑን በሚወዳት ሃገሩ ላማሳለፍ ስለፈልገ ይመስላል ሻንጣውን ሸክፎ ወደ ጃማይካ ለመመለስ ወሰነ።
እሱን ይዞ ወደ ጃማይካ ሲበር የነበርው አውሮፕላን ግን እንደታሰበው ብዙ ርቀት ተጉዞ ጃማይካ መድረስ አልቻለም። በጉዞ ላይ እያለ ህመሙ የተባባሰውን የሬጌ ንጉስ ህይወት ለማትረፍ ጉዞውን ቀይሮ ወደ ፍሎሪዳ በመብረር ማያሚ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እንዲገባ ተደረገ።
ሁሉም ነገር ግን አብቅቶ ነበር። ህይወቱ ከማለፉ በፊት እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስረአት በብፁእ አቡነ ይስሃቅ እጅ “ብርሃነ ሥላሴ” በሚል የክርስትና ስም ተጠምቆ ክርስትናን ተቀበለ። ለአለም ክስተት የሆነው የሬጌው ንጉስ ከ36 አመታት የህይወት ጉዞ በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ በተገኙበት በሚወዳት ሀገሩ ጃማይካ የቀብር ስነ ስርዓቱ ተፈፀመ።
ብርሃነ ሥላሴ ዛሬ በህይወት ቢኖር ኖሮ ድፍን 80 አመቱ ነበር። Happy birthday the one and only Bob Marley!