🙏ሰላም እንዴት አደራቹልኝ🙏
በችግሮችህ ላይ ያለህ እይታ ምን ይመስላል?
“ጉዞው ሲበረታ፣ ብረቱዎች ጉዟቸውን ይቀጥላሉ”
በአሁን ሰዓት እኔና አንተ የምንጋራቸውን ነገሮች እንዘርዝር ብንል ብዙ ሁኔታዎችን እናገኛለን፡፡ ከእነዚህ ሁኔታዎች አንዱ “ችግር” የሚባለው ጉዳይ ነው፡፡ ሁላችንም ብንሆን በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ችግሮችን እንጋፈጣለን፡፡ ችግርን በመጋፈጥ ደረጃ አንድ ስንሆን፣ የምንለያየው በችግራችን ላይ ባለን አመለካከት ነው፡፡
ችግሮችህ ከአቅምህ ቢበልጡ ኖሮ ባለፉት ሁኔታዎችህ ተውጠህ በቀረህ ነበር፡፡ አንተ ማንኛውም ሰው ካሉበት ችግር አልፎ የመሄድ ብቃት እንዳለው ከሚያመላክቱ ዋነኛ ምልክቶች አንዱ ነህ፡፡ አንድናድ ጊዜ ግን ችግሮችህ ያየሉና ከአቅምህ በላይ እንደሆኑ ልታስብ ትችላለህ፡፡ ይህ የመሸነፍ ስሜት ከተለያዩ ተጽእኖዎች ሊመጣ ይችላል፡፡
ከሚከተሉት አጉል ተጽእኖዎች ነጻነትህን አውጅ፡-
1. የሌሎች ልምምድና ሁኔታ ተጽእኖ
አሁን በሕይወትህ የሚጋፋህ ችግሮች ከዚህ በፊት በሌሎች ሰዎች ላይ ያስከተሉትን አስከፊ ሁኔታዎች ስታስብ የፍርሃት ስሜት ሊያጠቃህ ይችላል፡፡ አንድ ችግር ሌላውን ሰው አሸነፈው ማለት ግን አንተን ያሸንፍሃል ማለት አይደለም፡፡
2. የግልህ ልምምድና ሁኔታ ተጽእኖ
አሁን የተጋፈጥከው ችግር ከዚህ በፊት ጎድቶህ ካለፈ አሁንም ያው ሁኔታ የሚደገም ስለሚመስልህ ፍርሃት ሊጫጫንህ ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ከመፍራት ይልቅ ሁኔታው ከዚህ በፊት ሳያሸንፍህ እዚህ መድረስህ ላይ ማተኮርን ምረጥ፡፡
3. የመሰረተ-ቢስ ፍርሃት ተጽእኖ
አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ራሱ ያስፈራናል፡፡ በውስጥህ የሚሰማህን ፍረሃት ምንጭ ለማወቅ ብትሞክር እንኳ ላታገኘው ትችላለህ፡፡ ይህ አይነቱ ፍርሃት እንዲያደክምህ ግን መፍቀድ የለብህም፡፡ መፍራትህን በመፍራት አትንበርከክ፡፡ አደጋው ያለው ፍርሃት ላይ ሳይሆን
ለፍርሃት የምትሰጠው ምለሽ ላይ ነው፡፡
ቸር ቀን🙏
#በቅንነት_ሼር_ያድርጉ 👇
✨ Share with your Friends
🎖📖🎖
@aplusacademyy