ባህርዳር‼️
የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ማኅበራትን ለማደራጀት ዝግጅት ማጠናቀቁን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመፍታት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ለመገናኛ ብዙኀን በሰጡት መግለጫ ከተማ አሥተዳደሩ የነዋሪዎቹን የልማት እና የመልካም አሥተዳዱር ጥያቄዎች ለመመለስ የሠራቸውን ሥራዎች ዘርዝረዋል።
የከተማው ሕዝብ ከሚያነሳቸው ጥያቄዎች ውስጥ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አንዱ በመኾኑ ጥያቄውን ለመመለስ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ለተደራጁት 896 ማኅበራትን መሬት አቅርበን አብዛኞቹ አግኝተዋል ብለዋል።
በቀጣይም የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ለመስጠት የከተማ አሥተዳደሩን የጸጥታ መዋቅር፣ የመንግሥት ሠራተኞችን እና የከተማ ነዋሪዎችን እንደ ቅደም ተከተላቸው ለማደራጀት ለምዝገባ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳውቀዋል።
አሁንም ካለው ሰፊ የሕዝብ ጥያቄ አኳያ በ2013 ዓ.ም በማኅበር መደራጀት እንዲቆም ከንቲባ ኮሚቴ ወስኖ እንደነበር እና አሁን ላይ እገዳው ተነስቶ መደራጀት እንዲቻል የከንቲባ ኮሚቴው መፍቀዱን ገልጸዋል።
ከንቲባ ኮሚቴው ከ500 በላይ የቤት ማኅበራት እንዲደራጁ ፈቅዷል። አደረጃጀቱም በቤት ሥራ ማኅበር መመሪያ ይኾናል። ከአሁን በፊት የነበሩ ችግሮችንም እንቀርፋለን ብለዋል። ማደራጀት ያለበትም የማኅበራት ጽሕፈት ቤት ብቻ በመኾኑ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ይሠራል ብለዋል።
የማደራጀት ሂደቱ በሦስት ምዕራፍ እንደሚከወን የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ከሚያዝያ 06/2017 ዓ.ም ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የጸጥታ አካላት እና የከተማ ነዋሪዎችን የማደራጀት ሂደት እንደሚከተል ገልጸዋል።
በከተማዋ የሃሰተኛ መታወቂያን ችግር ለመቅረፍ እንደሚሠራም ነው የተናገሩት።
መላው የከተማ ነዋሪዎችም ከአደራጅ መሥሪያ ቤቱ እና ኮሚቴዎች ውጪ የሚቀርብ አደረጃጀት ተቀባይነት የሌለው በመኾኑ ከጉዳይ አስፈጻሚ ደላላ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ነዋሪዎች የሚተላለፈውን ማስታወቂያ በመከታተል በግንባር ቀርበው እንዲደራጁ አሳስበዋል።
ከዚህ በፊት እውቅና የሌላቸው እና ተደራጅተው የተገኙ 936 ማኅበራት ሕግን ያልተከተሉ እና ስህተት ያለባቸው ኾነው መገኘታቸውንም ጠቅሰዋል። የሚጠየቁ አካላትም እንዲጠየቁ እየተደረገ መኾኑን ነው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የገለጹት።
ተቀባይነት በሌላቸው ማኅበራት ተደራጅተው የተገኙ ነዋሪዎች ግን አሁን ላይ በተፈቀደው ማኅበር መደራጀት እንደሚችሉ ነው በመግለጫው የተገለጸው።
በቂ ዝግጅት አድርገናል፤ በአጭር ጊዜ የማደራጀቱን ሥራ እንጀምራለን ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ በአራቱም አቅጣጫዎች የቦታ ዝግጅት እንዲደረግ መወሰኑንም ነው የገለጹት።
መደራጀት የሚፈልጉ ነዋሪዎች ማሟላት የሚገባቸውን መረጃ በተመለከተ ከላይ ከተያያዘው ምስል መረጃ ይውሰዱ።
አዩዘበሀሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s