ለወንድም ጌታቸው ሽፈራው
ጌታቸው በሙሉ ልቡ ይመለሳል የሚል እምነት ነበረን። ነገር ግን የቦታ እንጅ የአቋምና አመለካከት ለውጥ አለማድረግህ ያሳዝናል። ትናንት የብልጽግና ታዛ ስር ሆነህ ያንፀባረቀውን "ኢመደበኛ ኃይላት ይጥፉ" የሚል ሃሳብ፣ ዛሬም በእየሩሳሌም ከትመህ በውስጠ ወይራ መልዕክትህ ደግመኸዋል። መጣህ ስንል፣ ሩቅ ነህ፤ በጠስከው ስንል ያው ነህ። እስራኤል ድረስ በረዥሙ አስሮ ያለቀቀህ፣ የታዛ ስር ትብታብ ተስፋ አስቆራጭ ነው!
ለማንኛውም "መከላከያ የህዝብ ትራንስፖርትን እንደ ከለላ" እየተጠቀመ መሆኑን ሰሞኑን አንተ እራስህ ፅፈሃል። ይህንን ለህዝብ ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውን የአገዛዙን ድርጊትና የውጊያ ስልት ለማክሸፍ፣ ፋኖዎቻችን የትራንስፖርት እቀባ በማድረግ ጠላትን ነጥሎ ለመምታት የውጊያ እቅድ ማውጣታቸው የሚያስተች አይደለም።
ይህ የትራንስፖርት እቀባ እኮ ለወገን አሉታዊ ተፅዕኖ ሳይኖረው ቀርቶ አይደለም፤ ነገር ግን አንድን አካል ለማጥቃት ሌላ ምስል ሰጥቶ ማቅረቡ በእጅጉ ትዝብት ላይ የሚጥል ነው። የሚሻለው በተቀመጠው መመሪያ መሰረት በሁሉም አካባቢዎች ያለ አምራች የተባለው ክፍል በምን መልኩ ምርቱን ይሰብስብ የሚለውን ማመላከቱ ላይ ነው።
እንጅማ… ሶስት ልጆቹን ሳይሰስስት ለህዝብ ህልውና መረጋገጥ የገበረ ጀግና መሪያችን ምንም ባላለበት ሁኔታ፣ "የጤፍ ማሳየ ደርሷልና" ብሎ አብዝቶ የሚጮህና ፀጉር ስንጠቃ ውስጥ የሚገባ "ፍላጎቱ ምንድን ነው?" የሚያስብል ሳይሆን ቀርቶ አይደለም። ወንድም ጌታቸው ስምክን አንስተን የጻፍንልህ፣ ከልብህ ብትመለስና "አማራ" ሆነህ ዳግም ብትቆም… ነፍስ ያለህ የምትጠቅም ልጅ እንደሆንክ ዛሬም ስለምናም ነው።