የአማራ ፋኖ በጎጃም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እና መግለጫ
በመጀመሪያ በዱርና በገደሉ፣ በሃሩርና በብርዱ፣ በከተማ ኦፕሬሽንም ሆነ ምሽግም ውስጥ፣ በሰፊዉም ሆነ ጠባቡ እስር ቤት ዉስጥ ያላቹህ፤ ቆላ ወርዳቹህ ደጋን ወጥታቹህ ከጠላትት ጋር ግብ ግብ የገጠማችሁ፣ በምትሰሩት ተጋድሎ ሁሉ የኅሊና ወቀሳ የሌለባቹህ፣ ከጠላት ጋር እየተናነቃችሁ ለህዝባችን ማህበራዊ እረፍት ማግኘት ለምትታገሉ ፋኖዎቻችን በሙሉ... እንኳንም አብሮ አደረሰን!! በዓሉን ለምታከብሩ የሰው ልጆች ሁሉ እንኳንም "ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል" አደረሳችሁ።
-
-
የአማራ ፋኖ በጎጃም ድርጅታዊ ዕዝና ሰንሰለት ያለው፣ ተጠየቅን ያነገበ ተቋም መሆኑ ይታወቃል። በዚህ አሰራርም ከዓላማችን በተፃራሪ የሄዱ ወንድሞቻችን ላይ የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ውስጣዊ አንድነቱን ያስጠበቀ ኃይል መገንባታችን ውሎ ያደረ ሃቅ ነው። ለጉድለቶች ተጠየቅን፣ ለመሻሻሎችም ምስጋናን የሚያቀርብ አሰራርም አለን። እለት ከእለት ለመሻሻል ከመስራት፣ ለአንድነትም ከመስራት የማያሳልስ ጥረት ከማድረግ ተቆጥበን አናውቅም።
ዳሩ ግን አንድም ወታደራዊ ሽንፈቱን በውጊያ ሜዳ የተጋተው አገዛዙ ከውጭ በኩል፣
ሌላም የአንድነትን አስፈላጊነት በውል ያልተረዱና የዉጊያን ሜዳ አስከፊነት የማያውቁ ውስጣዊ እቡዮች ተባብረው በሚፈጥሩት ውስብስብ አጀንዳ ምክንያት 'ጠላት በሚዲያ የሐይል አሰላለፉ' በኩል የደረሰበትን ምት በማስተባበልና የጣረ ሞት መንፈራገጥ ላይ ይገኛል። በዚህም በድርጅታችን የአማራ ፋኖ በጎጃም ውስጥ "የተለየ ነገር የተፈጠረ ለማስመሰል" የሚደረገው ጥረት ሁሉ የበሬ ወለደ ወሬና ፍፁም ተጨባጭ ያልሆነ አጀንዳ መሆኑን በማወቅ የውጊያም የስንቅም ደጀን የሆነው ህዝባችን ትኩረቱን ሁሉ የጠላት ሐይል ላይ ብቻ እንዲያደርግ ስል ወንድማዊ ጥሪየን አቀርባለሁ። የፋኖ ሰራዊታችን በዓሉን በወትሮ ዝግጁነት እንዲሁም ከጠላት የድሮን አሰሳና ጥቃት በተጠንቀቅ እንዲያከብር እያሳሰብኩ በዓሉን ለምታከብሩ ሁሉ በድጋሜ መልካም በዓል እላለሁ።
ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ደለለ
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ