ሚሊዮኖች ሆነህ፣ በውል የደረጀም አቅም ኖሮህ ነገር ግን አንድ ባለመሆንህ እንዲህ እንደ እናት ጡት ሁለት ሆነው እዚህም እዛም በቆሙት ነገር ግን በተደማመጡ ስብስቦች ብልጫ ይወሰድብሃል።
እነ እስክንድር ነጋ ትግላችንን ጠምዝዘው የብልጽግና አቁማዳ ውስጥ ለመክተት የሄዱበትን መንገድ የፈቀድንላቸው በእኛው በራሳችን ድክመት ነው። እነ እስክንድር ነጋ "ፍላጎታቸው የፌድራል ስልጣን ማግኘት" መሆኑን በዚህም የቀሪ ፋኖዎችን አደረጃጀት መረጃ ለአገዛዙ ለመስጠትና አንዳንድ አባላቶቻቸውን በአገዛዙ የህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ አሳልፎ ለመስጠት መስማማታቸውን ከመሰረት ሚዲያ ያገኘነው ከላይ የተያያዘው መረጃ ያስረዳል።
ትንሽ መዘግየት ዋጋ በሚያስከፍል ትግል ውስጥ ሆነን እዚህም እዛም ባሉት መዘግየቶች ምክንያት ጥቂቶች ውርውር እንዲሉ ፈቅደን የማርያም መንገድ ሰጥተናል። ለዚህ ሁሉ ስህተቶች ኢጎን መግራት ያልቻሉ የተናጥል አካሄዶቻችን ምክንያት ናቸው።
የሆነው ሆኖ የረቀቀ የደህንነት መዋቅር ያላቸው የምዕራቡ ዓለም ሰዎች፣ ይህ አካሄድ እውነተኛ ሰላምን ሊያመጣ እንደማይችል ለመረዳት ይከብዳቸዋል የሚል እምነት የለንም። በጥቂት የነፍስወከፍ መሳሪያ የጀመረው ትግላችን፣ አሁን ጎምርቶ ለደረሰበት የእድገት ደረጃ የማንም ውጫዊ አካል ድጋፍ ኖሮ አይደለም።
እናም አሁንም የአንድነት ጉዟችንን ካፋጠን ለትግል የወጣንለትን ዓላማ የህዝባችንን ህልውና በዘላቂነት የማረጋገጥ ግብን የመታ ድል ማስመዝገብ እንችላለን። ይህንን ግብ ማረጋገጥ የሚቻለው ደግሞ አንድም 4 ኪሎን በመጨበጥ ወይም ለሃገሪቱ ቀጣይነት ከሶስተኛ አካል ጋር ውይይቶች ከታሰቡም አብይ አህመድን ጨምሮ የአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ተሳትፎ ያላቸው በሙሉ ለህግና ተገቢ ፍትህ የሚቀርቡ መሆኑ ከጅምሩ መግባባቶች ካሉ ብቻ ይሆናል።