ያ ጊዜ ይናፍቃል!
ከዓመት በፊት ከእነ ሙሉጌታ አንበርብር፣ የፈራ ይመለስ፣ ምስጋናው ዘ-ግዮን፣ አዲሱ ደርቤ እና ሌሎችም ጋር ሆነን ትግላችንን ከጫፍ ጫፍ አንድ ቃል ተናጋሪ አድርገነው ነበር። በጠላት ላይ የወሰድነው የፕሮፖጋንዳና የሚዲያ ብልጫ ለእኛም አስደማሚ ነበር። ጠላት ሜንስትሪም ሚዲያና ተከፋይ አክቲቪስቶችን ይዞ ነገር ግን ድምፁ እንደ አረጋ ከበደ የሰለለ ነበር።
ህብረታችን እጅጉን ያስቀና ነበር። ህብረታችን ጠላትን ነጭ ወረቀት ላይ እንዳለ ጥቁር ነጥብ አጋልጦ በማሳየት ለወገን ኃይል ብርቱ ክንድ መሆን ችለን ነበር። ፁሑፎቻችን ጠላትን አቅርበው የሚያሳዮ፣ ለአፈሙዝ የሚያመቻቹና የጠላትን ጓዳ ጎድጓዳ የሚጎበኙ ነበር። እኛን እንዲበረብር የተቋቋመው ኢንሳ የሚባለው ተቋም ውስጥ ሁሉ ገብተን ሴራዎቻቸውን የዋትሳፕ ልውውጣቸውን ሳይቀር ስናጋልጥና ጠላትን መፈናፈኛ ስናሳይ ነበር። በእውነቱ ያ ጊዜ የሚናፈቅ፣ የሚዲያን ሚና በውል ያሳየ ወርቃማ ጊዜ ነበር። ዛሬ ብዙዎቻችን ከሚዛኑ ብንጎድልም ነገር ግን እነ ሙሉጌታ ዛሬም በልካቸው አሉና እንደምንኮታባችሁ መደበቅ አንፈልግም።
የሆነው ሆኖ ከሚዛኑ መጉደላችን ለጠላት ምቹ ሆኖ ፊደል ያልዘለቀው ካድሬ ሁላ በወገናችን ላይ የሚዲያ ዥዋዥዌ እንጫወት ፈቀድንለት። ይህ ሁሌም ያንገበግበናል! እንደሚዲያ ሰው ገመዱን ወንጭፍ ማድረግ ሲገባን፣ እኛም ጫፍና ጫፍ ይዘን መጓተቱን መረጥን። በቀደመ አበርክቷቸው ልክ ያከበርናቸው ወንድሞች ለአፍታ እንኳን "ጉዞዬ ልክ ነው?" ብሎ ቆሞ ብሎ ማሰብ ተስኗቸው ለእልህና ኢጎ እጅ ሰጠው አየናቸው። በእኛ አቅም የተሞላ ስንፍና ምክንያት ለጠላት ጊዜ ሰጠነው።
አሁንም ቢሆን ያን ጊዜ መመለስ ይቻላል? የእኛ መልስ አዎ ይቻላል የሚል ነው። ሚናውን የለየ ጠንካራ የሚዲያ እንቅስቃሴ ትግልን ወደድል ማማ ማስፈንጠር እንደሚችል ብዙ አስረጅዎችን ማቅረብ ይቻላል። እንኳን አንድ ሆነን መጥተን ይቅርና ይህን "አንድ እንሁን የሚል ፁሑፍ" ደጋግመን ብንፅፍ እራሱ ጠላት እንደነፍሰ ጡር ጠዋት ጠዋት ማስታወኩ አይቀርም።
መረዳት ያለብን ነገር… እርስበርስ ከመከባበር እንጀምር፤ እንደነ አሳዬ ደርቤና ሙሉጌታ አንበርብር እንደሰሞኑኑ አብሮ በመስራት እንቀጥል፤ የጋራ አጀንዳዎችን ቀርፀን እንቀሳቀስ፤ የአንድነት እንቅስቃሴዎችን እናበረታታ፤ ለአንድነት እርምጃዎች እድሉን እንስጥ። (ይህንን የምንለው "አንድነት አንድነት" ሲሉ ከርመው ኢ/ር ማንችሎት ከደቡብ ጎንደር ፋኖዎች ጋር ሰራ ብለው የሚያጉሩ ምንዱባኖችን ስላየን ነው። ካልተነጋገርክና ካልተቀራረብክ እንዴት ነው አንድነት የሚመጣው? ይህንን መሰል እንቅስቃሴዎች ከቀጠቀጥክ ከጠላት በምን ተለየህ? አንድነትስ ከምን ይዝነብልህ?)
(ምንም ያክል የአደረጃጀት ልዮነት ቢኖር ጠላትን እየታገሉ ያሉ ወንድሞችን ከጠላት በላይ መጥላቱ ልክ ሊሆን ፈፅሞ አይችልም። አሸናፊ የሚያደርግህ ኢንጅነር ደሳለኝ ከመከታው ማሞ ጋር ቢያንስ አብሮ እንዲሰራ ማበረታታቱ እንጅ፣ መከታውን መከራው በማለት መከራችንን ከማራዘም የዘለለ ፋይዳ እንደሌለው ለመረዳት ለአፍታ ቆም ማለትን ይጠይቃል። ከወንድሙ ጋር ሳይስማማ ከጨፍጫፊው ጋር ጠረጴዛ ለመጋራት የሚኳትነውም እንዲሁ እራሱን ከማስበላትና የወገኑን ስቃይ ከማራዘም ውጭ ዘላቂ መፍትሔን እንደማያመጣ አሁንም ለአፍታ መስከንን ይጠይቃል። ለአንድነት ሲባል ደፈር ተብሎ የአደረጃጀት መስመሮችን ማለፍ የግድ ይለናል። የምንፈልገው አንድነት እውን ሆኖ እስክናይም ቢያንስ ቢያንስ በአደረጃጀት ልዮነት ውስጥ ያሉ ፋኖዎቻችችንን በትብብር እንዲሰሩ ማበረታታቱ ከምንም በላይ ትንሽ ከሚያውቅ ሁሉ የሚጠበቅ የብልህ ጉዞ ነው።)
እናም ያን ጊዜ ለመመለስ እንትጋ፤ እናስብበት ወገን!