ከመሬት መንቀጥቀጡ በኋላ...
----◉-----
ከበርናባስ በቀለ
ትላንት ምሽት አዲስ አበባና በአካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ (እነርሱ ንዝረት ነው ብለዋል፤ እኔ ግን እላለሁ፦ መንቀጥቀጥ ነው!😶) የእኛንም ሰፈር ለደቂቃዎች በአንድ እግሩ አቁሞት ነበርና ሰው እየሮጠ ሲወጣ እኔና ቤቴም ከሕንጻው ወደ መሬት ስንወርድ ከለበስነው የምሽት (የቤት ውስጥ) ልብስና በእጄ ከያዝሁት ስልክ በቀር ምንም ይዘን አልወጣንም።
ከሰፈሩ ሕዝብ ጋር በውጭ ስንገናኝም ማንም ምንም አልያዘም፤ ሁሉም ደንብሮ ራሱን ብቻ ይዞ ባዶ እጁን ወጥቷል። ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ጭንቀት ውስጥ ሆኖ በውጭ ተሰብሷል፤ ድሃ የለ፣ ሃብታም የለ! ባለ ሥልጣን የለ... ወዛደር የለ... ወቶ አደር የለ... ሁሉም በምሽት ልብሱና በነጠላ ጫማው ወጥቶ በፍርሃት ተውጦ ቆሟል። ክልል የለ፣ ኦሮሞ የለ አማራ የለ...ካምባታ የለ... ጉራጌ..! ሁሉም ሰላም ወጣችሁ!? አራሷ ወጣች? ነፍሰ ጡሯስ? በቃ ሁሉም እኩል ሆኖ ተሰልፏል አልኳችሁ! እመኑኝ፤ ማንም ምንም ይዞ አልወጣም።
በቅርቡ አንድ ባሕር ማዶ የተከሰተ ተመሳሳይ story ሰምቻለሁ፤ አንድ ባለ ሕንጻ (ባለ ሃብት) ሰውዬ ፎቁ ላይ የተከራየውን ነጋዴ ኪራይ ሳምንት አሳልፎ በመክፈሉ ውጣልኝ ብሎ ያስወጣዋል፤ ተከራዩም የከፈለበትን ወር ብቻ ሠርቶ እያለቀሰ ሌላ ሱቅ ፍለጋ ይዞራል። በሳምንታት ውስጥ በአገሪቱ በተከሰተ ርዕደ መሬት ሕንጻው ወድሞ ባለ ሱቁም ሌላ ሱቅ ሳያገኝ ስራውን አቁሞ ሁለቱም መንግሥት ለተጎጂዎች በሠራው መጠለያ ተገናኙ የሚል ዘገባ አንብቤአለሁ (ቃል በቃል አላሰፈርሁ እንደሆነ ይቅርታ!)። ባለ ሕንጻ የነበረው ሰውዬ (የቀድሞ ባለ ሃብት) አሁን ግን ተረጂ፣ ባለ ሱቁም (የቀድሞ ባለ ሱቅ) አሁን ግን በመንግሥት የሚረዳ ሆነው ቁጭ አሉ። አይገርምም!? ሕይወት ይህችው ናት። በመጨረሻም የምታስመልጡት ራሳችሁንና ራሳችሁን ብቻ ነው።
ያከማቻችሁት ሃብት የእናንተ አይደለም፤ እጃችሁም ያለው እናንተን (ራሳችሁን) አይደለም። እናንተ ማለት ይዛችሁ የወጣችሁት ማንነታችሁ ነው። በዚያ ሰዓት ዘር፣ ዝና.. ታዋቂነት እና አዋቂነት አይሠሩም። ሁሉም እኩል! "አለኝ" የምትለው በፍጻሜ የአንተ አይደለምና ይዘኸው መሸሸ የቻልኸው ራስህን (አንተነትህን) በትኩረት እይ! ትምክህትም አለኝ በምትለው አይሁን፤ ከተፈጠረው ክስተት "አለኝ" የምትለው እንደማይከተልህ አስተውለሃልና!! ይኸው ነው።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊