ፊልጵስዩስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤
²⁴ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።
በዚህች ምድር ላይ ስንኖር ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ጉልበታችንን እስክንሰጥ ድረስ ብዙ ትኩረታችንን የሚፈልጉ ሁኔታዎች ይገጥሙናል። ሰው እንደመሆናችን ማሰብና መጨነቃችን አዲስ ነገር ባይሆንም ጉዳዮቻችን አዕምሮአችንን ተቆጣጥረው ከዛ ውጪ ማሰብ የማንችልበት ሁኔታ ላይ ከደረስን ግን መንፈሳዊ ዝለት ውስጥ ከመክተታቸውም ባሻገር ነገን የማየት ፍላጎታችንን ሊነጥቁ ጭምር ይችላሉ።
የጳውሎስን የጭንቀት ምንጮች ስናይ አንድ ነገር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ለመሞት ሲጓጓ ኢየሱስን በመናፈቅ፣ ለመኖር ሲያስብ ደግሞ ለኢየሱስ የሚሆን ሰውን ስለማዘጋጀት ብሎ ነበር። ጳውሎስ ከእስር ቤት ወጥቶ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ስለመትከል አልተጨነቀም ይሄም ቢሆን እኮ አስደናቂ ሀሳብ ነበር ነገር ግን ጳውሎስ የሚበልጠውን ናፈቀ እርሱም ኢየሱስን በአገልግሎቱም ሆነ በሞቱ ማየት ነው። ኢየሱስ ላይ ትኩረት ስናደርግ አሁን ላይ እየተጨነቅንባቸው ያሉ ጉዳዮች በእርሱ ሀሳብ ይተካሉ። እየኖርም ሆነ እየሞትን እርሱን ስለማክበር ማሰብ እንጀምራለን። አንድ ሀሳብና ትኩረት እርሱም ኢየሱስ ብቻ ይሁንልን!
FOLLOWING THE KING
ንጉሱን መከተል
KNOW I OBEY I REST
ማወቅ I መታዘዝ I ማረፍ
Follow Us On 🔗
🌐TELEGRAM 💻INSTAGRAM 🖥 YOUTUBE