"ነይ በናትሽ ልሳምሽ?" አላት መልሶ።
"መሳሳም ግን አይገርምም? ለምንድን ነው ሰው የሚሳሳመው?" አለች
"አሁን ከሌሊቱ ሰባት ሰአት ይሄን መጠየቅ ምን ይጠቅማል? መሳሳም ነው እንጂ" አለ ክብሩ።
"አይ እንዲያው ግን አይገርምህም? የሰው ተፈጥሮ አልጋ ላይ ሲወጣ እና ልብስ ለብሶ ሲሄድ ያለው ልዩነት" አለች
"ውይ! አንቺም ተጋባብሽ?" አላት ክብሩ።
"ምኑ?" አለች።
"የደስታ በሽታ ነዋ!" አላት።
ቀልድ መሆኑ ቢገባትም "የእሱ ደግሞ በሽታ ምንድን ነው?" አለች።
"ሁሉን ነገር መጠየቅ፣ሁሉን ነገር ማሰብና ሁሉን ነገር መመርመር ነዋ!" አላት።
"እሱስ በያዘኝ" አለች ውቢት።ግን የመሳሳሙ ነገር አይገርምም?" አለች አሁንም።
"በይ በይ ሲነጋ ትደውይና የሚልሽን ትሰሚያለሽ፣እኔ አሁን የተግባር ልምምዱ ላይ ነው ማቶኮር የፈለኩት" አላት።
"ካልክ ምን ይደረጋል?" ብላ በከንፈሩ ላይ ተሳካችበት።በዚህ ልምምድ መካከል እያሉ ስልኳ ሲጮህ ተሰማት፤ሰአቷን ስትመለከት ከሌሊቱ ሰባት ሰአት ከሩብ ይላል።
ርዕስ፦አለመኖር
ደራሲ፦ዳዊት ወንድምአገኝ
@betagitim