መውደድ........
ከልብ መዋሀድ
መናፈቅ
እየሄዱም እየመጡም ደርሶ እንደመጠበቅ
ናፍቆት እንደ ህማም
የልብን ስር ድካም
በትዝታ ቋጥኝ ተዘፍቆ መገኘት
በማፍቀር ሰንሰለት ተጠፍሮ መዋተት
ፍቅር...
በምሽት ጨረቃን ደርሶ እንደመጎብኘት
በማለዳ ፀሀይ ሞቆ እንደመደሰት
በሀሩር ቃጠሎ በዝናብ እንደመራስ
ከቀዝቃዛ በረዶ በሙቀት ነፍስን አንስቶ እንደማደስ
ትዝታ....
ተለያይቶም ደርሶ ታስሮ በትላንቱ
ይታወስ ሲጀምር ሲደረደር ስንቱ
ፍቅር ተጀምሮ
ናፍቆት ተደምሮ
ትዝታ እያሰረ
እየደረደረ
✨ነፍስን ከስጋ ከአለም አላቆ
✨ሞትን አስመኝቶ ህይወትንም ነጥቆ
✨በጭላንጭል ተስፋ ነፍስን እንደመስቀል
✨ፍቅር ይሉት ጉዳይ ራስንም ያስረሳል
✍️ቃል
@betagitim
@betagitim
ከልብ መዋሀድ
መናፈቅ
እየሄዱም እየመጡም ደርሶ እንደመጠበቅ
ናፍቆት እንደ ህማም
የልብን ስር ድካም
በትዝታ ቋጥኝ ተዘፍቆ መገኘት
በማፍቀር ሰንሰለት ተጠፍሮ መዋተት
ፍቅር...
በምሽት ጨረቃን ደርሶ እንደመጎብኘት
በማለዳ ፀሀይ ሞቆ እንደመደሰት
በሀሩር ቃጠሎ በዝናብ እንደመራስ
ከቀዝቃዛ በረዶ በሙቀት ነፍስን አንስቶ እንደማደስ
ትዝታ....
ተለያይቶም ደርሶ ታስሮ በትላንቱ
ይታወስ ሲጀምር ሲደረደር ስንቱ
ፍቅር ተጀምሮ
ናፍቆት ተደምሮ
ትዝታ እያሰረ
እየደረደረ
✨ነፍስን ከስጋ ከአለም አላቆ
✨ሞትን አስመኝቶ ህይወትንም ነጥቆ
✨በጭላንጭል ተስፋ ነፍስን እንደመስቀል
✨ፍቅር ይሉት ጉዳይ ራስንም ያስረሳል
✍️ቃል
@betagitim
@betagitim