የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያካታቸዉ ይዘቶች
(የካቲት 14/2017 ዓ.ም) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያካታቸዉ ይዘቶችን አስመልክቶ የሚከተሉትን ነጥቦች አስቀምጣል፤
የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት ፣ ከ11ኛ-12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡ በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ አሉ፡፡
በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።
ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-
1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት
2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች
3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች
4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል
5) የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ
ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ
ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል።
በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc