በተባለው ሳይሆን
ከተናቀ ስፍራ ፥
ከተናቀ ሥራ ፥
ሰብኮን በተጠሩ ፥
ፊደል ባልቆጠሩ ፥
ጥሪት ባልቋጠሩ ፥
አንደበተ ርቱ ፥ ባልሆኑ ጠቢባን
በኮልታፋ ልሳን ፥ ክርስትና ገባን ።
ሳይሆን ሳለ ወጣት፥
በጉብዝናው ሰዓት ፥
እንዳይል ሀይሉ ፥ ጥበቡ የራሴ
በእርጅናው ወራት ፥ በደከመ ጊዜ
ነፃ ማውጣት ቻለ ፥ እስራኤልን ሙሴ።
ደፍሮ የሚፋለም ፥
ሲባል ማንም የለም ፥
አንድ ጀግና ጠፍቶ ፥ ከእስራኤል ሰራዊት ፥
ጣለው ጎልያድን ፥ የተናቀው ዳዊት።
ፈጣሪ
ብርቱ ነው በጉልበት ፥
ወይም አለው ሹመት ፥
በተባለው ሳይሆን ፥ ከሁሉ ይበልጣል
በደካማው ድካም ፥ ሀይሉን ይገልጣል ።
✍ አቤል ታደለ
ለአስተያየት : @abeltadele
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ከተናቀ ስፍራ ፥
ከተናቀ ሥራ ፥
ሰብኮን በተጠሩ ፥
ፊደል ባልቆጠሩ ፥
ጥሪት ባልቋጠሩ ፥
አንደበተ ርቱ ፥ ባልሆኑ ጠቢባን
በኮልታፋ ልሳን ፥ ክርስትና ገባን ።
ሳይሆን ሳለ ወጣት፥
በጉብዝናው ሰዓት ፥
እንዳይል ሀይሉ ፥ ጥበቡ የራሴ
በእርጅናው ወራት ፥ በደከመ ጊዜ
ነፃ ማውጣት ቻለ ፥ እስራኤልን ሙሴ።
ደፍሮ የሚፋለም ፥
ሲባል ማንም የለም ፥
አንድ ጀግና ጠፍቶ ፥ ከእስራኤል ሰራዊት ፥
ጣለው ጎልያድን ፥ የተናቀው ዳዊት።
ፈጣሪ
ብርቱ ነው በጉልበት ፥
ወይም አለው ሹመት ፥
በተባለው ሳይሆን ፥ ከሁሉ ይበልጣል
በደካማው ድካም ፥ ሀይሉን ይገልጣል ።
✍ አቤል ታደለ
ለአስተያየት : @abeltadele
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19