“ያድርስልህ ለሰው”
————-//———-
አርከፍክፍ እንባህን፣ ስሜትህን ማግደው
በቁስልህ ምድጃ ህመምህን አንድደው፤
ይንተክተክ ውስጠትህ ቱግ ቱግ እያለ!
መግላሊቱን ይግፋ እየገነፈለ፤
ይብሰል! እሳት ይምታው እንዲ’በላ ጣፍጦ
ጥልል ይበል ስቡ ይታይ ተቅለጥልጦ
ልብህ ደዌ ችሎ፣ ስቃይ አጣጥሞ
እግርህ ሰላ ብሎ፣ ከናድህ ፈርጥሞ
ራዕይ ለመሞላት እንዲወስድህ ፍጥሞ፤
ቁስልህን ጉልቻ፣ መከፋትህን ድስት
እንባህ ቤንዚን ይሁን፣ ማቃሰትህ ክብሪት
የመድረሻ አቅጣጫ እንዲሰጥህ ምሪት፤
ስሜትህን ማግደህ ሰባራው ልብህ ላይ
ለኩሰው እሳቱን፣ አጢያጢሰው
ጢሱን ይሂድ ወደ ሰማይ!
አግመው ነዲዱን ይትጎልጎል ቆስቁሰው
አውሎውን አንፍሰው! አየሩን አምሰው!!
የልብህን መሻት ላልተገነዘቡት
ያሳውቅ ለአገር፣ ያድርስልህ ለሰው።
ስማኝማ አንተዬ!!
አልያ እንኳን እቀድ የም’ተገብረው
እንኳን የድል ዜማ የምትዘምረው
ስለ መዳረሻህ የምትፈክረው
ስጋና እስትንፋስም ከደዌህ አብረው
ከማትስማማቸው፣ ከጠሉህ ተባብረው
ይዶልቱብሃል ሊሸኙህ አሻግረው!!
አይዳ (ቃል እና ቀለም)
ተፃፈ በቀን 12/4/2024
Break Room በምሳ ሰዓት
ግጥሙን ለመፃፍ ውስዋስ የሆነኝ
“TURN YOUR PAIN IN TO POWER”
የሚል ባለቤቱን ያላወቅሁት ጥቅስ ነው።
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
————-//———-
አርከፍክፍ እንባህን፣ ስሜትህን ማግደው
በቁስልህ ምድጃ ህመምህን አንድደው፤
ይንተክተክ ውስጠትህ ቱግ ቱግ እያለ!
መግላሊቱን ይግፋ እየገነፈለ፤
ይብሰል! እሳት ይምታው እንዲ’በላ ጣፍጦ
ጥልል ይበል ስቡ ይታይ ተቅለጥልጦ
ልብህ ደዌ ችሎ፣ ስቃይ አጣጥሞ
እግርህ ሰላ ብሎ፣ ከናድህ ፈርጥሞ
ራዕይ ለመሞላት እንዲወስድህ ፍጥሞ፤
ቁስልህን ጉልቻ፣ መከፋትህን ድስት
እንባህ ቤንዚን ይሁን፣ ማቃሰትህ ክብሪት
የመድረሻ አቅጣጫ እንዲሰጥህ ምሪት፤
ስሜትህን ማግደህ ሰባራው ልብህ ላይ
ለኩሰው እሳቱን፣ አጢያጢሰው
ጢሱን ይሂድ ወደ ሰማይ!
አግመው ነዲዱን ይትጎልጎል ቆስቁሰው
አውሎውን አንፍሰው! አየሩን አምሰው!!
የልብህን መሻት ላልተገነዘቡት
ያሳውቅ ለአገር፣ ያድርስልህ ለሰው።
ስማኝማ አንተዬ!!
አልያ እንኳን እቀድ የም’ተገብረው
እንኳን የድል ዜማ የምትዘምረው
ስለ መዳረሻህ የምትፈክረው
ስጋና እስትንፋስም ከደዌህ አብረው
ከማትስማማቸው፣ ከጠሉህ ተባብረው
ይዶልቱብሃል ሊሸኙህ አሻግረው!!
አይዳ (ቃል እና ቀለም)
ተፃፈ በቀን 12/4/2024
Break Room በምሳ ሰዓት
ግጥሙን ለመፃፍ ውስዋስ የሆነኝ
“TURN YOUR PAIN IN TO POWER”
የሚል ባለቤቱን ያላወቅሁት ጥቅስ ነው።
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19