Postlar filtri




The Southern Peoples Are Victims Too: Why the New Alliance Matters to Ethiopia’s South. Read more.
https://borkena.com/the-southern-peoples-are-victims-too-why-the-new-alliance-matters-to-ethiopias-south/ #Ethiopia #Allianceforsurvival #Ethiopianpolitics






The Red Sea,  Its Strategic Complication, The Multiple Actors And  Ethiopia’s Quest For Access To The Sea. Read more.
https://borkena.com/the-red-sea-its-strategic-complication-the-multiple-actors-and-ethiopias-quest-for-access-to-the-sea/ #RedSea #Ethiopia #Eritrea #SaudiArabia #Egypt #Somalia #Sudan #Iran #usa #China #Russsia


የአማራ ብሔረተኝነትና ኢትዮጵያዊነት  (ክፍል ሁለት)
https://tinyurl.com/ycyd899e #Ethiopia #EthiopianPolitics #Amhara 


አምና እና ዘንድሮ(ጠገናው ጎሹ)
https://shorturl.at/cR3W3 #Ethiopia #politics #EthiopianPolitics 


ምንድነው የመጀመሪያ ምርጫችን? ጦርነት ወይስ የፖለቲካ ስምምነት?
https://tinyurl.com/5d47n5dp #Ethiopia #EthiopianPolitics #EthiopianConflict 


በፈተና ላይ የወደቀው የፕሮፌሸናሊዝም ምሰሶ፦ የመከላከያ ሰራዊት ተቋማዊ ቀውስ፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እና የስትራቴጂካዊ ውድቀት ዋጋ https://shorturl.at/rGomx#Ethiopia #Ethiopianpolitics #Defenseforce 


«ለእውነተኛው የአማራ ፋኖ ታጋዮች የቀረበ ጥብቅና አስቸኳይ ግልፅ ጥሪ፦ የባርነት ካምፑን ሰብራችሁ ወጥታችሁ የሕዝባችሁን ክብርና ነፃነት አስከብሩ!» https://shorturl.at/yK5O7 #Ethiopia #EthiopianPolitics #Fano 


የገዳ ሥርዓትና ባንዲራ ኦሮሞ ለሆነውና ኦሮሞ ላልሆነው አብዛኛው ሕዝብ ምኑ ነው?
https://shorturl.at/EiLsc #Ethiopia #EthiopianPolitics #Geda #Oromo 




የትግራይ ሰላም ኃይል ራያ እና እንደርታ ከተማን በመቆጣጠር ወደ መቀሌ እየተጓዝኩ ነው አለ።

ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት በትግራይ ክልል ውስጥ እየተዋጋ የሚገኘው "የትግራይ ሰላም ኃይል" (TPF) አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ዛሬ ባወጡት አዲስ መግለጫ ኃይላቸው አብዛኛውን የራያ አካባቢ እንዲሁም የጥምቢያን እና የእንደርታ ክፍሎችን መቆጣጠሩን አስታውቀዋል።

አዛዡ አክለውም በቅርቡ ሙሉ ትግራይን ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ የገለጹ ሲሆን፣ ይህ መግለጫ ከሴፕቴምበር 23ቱ የውጊያ መባባስ በኋላ የሰጡት የመጀመሪያው ይፋዊ መልእክት ነው።

በመግለጫቸው ለጸጥታ ኃይሎች ባስተላለፉት መልእክት የትግራይ ሠራዊት፣ ሚሊሻ እና ፖሊስ አባላት እንደ ጠላት እንደማይታዩ አረጋግጠዋል።

አባላቱ ወደ ቀድሞ ጦር ከመመለስ ይልቅ በአካባቢያቸው በመቆየት ማህበረሰባቸውን እንዲጠብቁ፣ የትግራይ ንብረት የሆነውን ትጥቃቸውንም ለጊዜው በእጃቸው እንዲያቆዩና በኋላ ላይ በተደራጀ መንገድ እንዲያስረክቡ መክረዋል።

የአዛዡ መግለጫ ዋና ማጠንጠኛ "በቀል አይኖርም" የሚል ሲሆን፣ አሁን ካለው አመራር ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ ምንም ዓይነት የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድ አረጋግጠዋል።

ወንጀል የፈጸሙ ቢኖሩ እንኳ በህግ አግባብ ብቻ እንደሚዳኙ ተናግረው፣ የህዝብ፣ የመንግስት እና የግል ተቋማትም ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #ትግራይ #መቀሌ #ጦርነት #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና


ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እየተካሄደ ባለው ውጊያ "ከባድ የህልውና አደጋ ተደቅኗል አሉ

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሰሜኑ ጦርነት ዳግም ካገረሸ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አሁን እየተካሄደ ያለውን ውጊያ "ከባድ የህልውና አደጋ አምጥቷል" ካሉት የፌደራል መንግስቱ አስተዳደር ጋር የሚደረግ ትግል መሆኑን ገልጸው፣ አዲሱን የውጊያ ስልታቸውንም አመላክተዋል።

ሊቀመንበሩ እንዳስታወቁት ኃይላቸው በቀጣይ የሚያደርገው ውጊያ ከተሞችን አጽንቶ ይዞ በመከላከል ላይ የተመሰረተ አይሆንም። ከዚህ ይልቅ "ተቀናቃኞቻችንን እኛ በመረጥነው ጊዜ እና ቦታ እንገጥማለን" በማለት፣ ኃይላቸው ከመደበኛ የመከላከል ውጊያ ይልቅ ወደ ተንቀሳቃሽ እና የደፈጣ (ጎሬላ) ስልት መሸጋገሩን በግልጽ ጠቁመዋል።

አክለውም ጦርነቱ የቀጠናዊ ይዘት እና የውጭ ኃይሎች ተሳትፎ ያለበት መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ ህዝቡ እና የዳያስፖራው ማህበረሰብ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #ትግራይ #ህወሃት #ደብረፅዮን #አስመራ #ጦርነት #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና


ግብፅ የኢትዮጵያን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውጡ አለች።

ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የግብፅ ዲፕሎማት አህመድ ሞሀረም አህመድ ሱሊማንን በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሀገር እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ፣ ካይሮ በአጸፋው በግብፅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ የሆኑትን ዲፕሎማት በተመሳሳይ የ48 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ሀገር ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች ተብሏል።

ግብፅ እርምጃውን ዓለም አቀፉን የአጸፋ መርህ ተከትላ የወሰደችው መሆኑን በመግለፅ፣ የኢትዮጵያን ውሳኔ የሚያሳዝን ስትል ተችታለች።

ኢትዮጵያ በትናንትናው እለት የግብፅ ዲፕሎማትን ከሀገር እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥታለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ የግብፅ ኤምባሲ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ አንድ የግብፅ ዲፕሎማት አንድ ዲፕሎማት በተቀባይ ሀገር ተቀባይነት የሌለው (persona Non Grata) ተብለው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ማዘዙ ተገልጿል።

አህመድ ሞለራም ሶሊማን የተባሉት የግብፅ ዲፕሎማት፣ ማስታወቂያው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 48 ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መሰጠቱ ተገልጿል።


ኢትዮጵያ በትናንትናው እለት 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች።

በተመሳሳይ መልኩ አስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዘግታለች።

ይህ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ ቀጠናዊ ውጥረት ማስፈኑን ያመላከተ ተደርጓል።

#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #ኤርትራ #ግብፅ #አዲስአበባ #አስመራ #ኤምባሲ #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና


በጋሞ ዞን በፀጥታ አካላት ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ9 አባላት ሕይወት አለፈ።

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ በሚገኝ የኢንቨስትመንት መሬት አካባቢ ፀጥታ ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ በተከፈተ ጥቃት የዘጠኝ የፀጥታ አባላት ሕይወት ማለፉን የገረሴ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።

​ከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የሐዘን መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ቀደም ሲል በአካባቢው የሚገኘውን የመንግስት የኢንቨስትመንት መሬት በኃይል ለማስለቀቅ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት ሁኔታውን ለማረጋጋት እና ፀጥታ ለማስከበር በተሰማሩ አካላት ላይ ነው።

​በዚህ ህገ-ወጥ ጥቃት ምክንያት ሕይወታቸው ካለፈው 9 የፀጥታ አባላት መካከል፦​3 አባላት ከገረሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ እንደሞቱ አስታውቋል።

4 አባላት ከገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ፣ እንዲሁም ​2 አባላት ከገረሴ ዙሪያ ወረዳ ሚሊሻ መሆናቸው ተረጋግጧል።

​የገረሴ ከተማ አስተዳደር በታጠቁ አካላት የተፈጸመውን ጥቃት፣ የዜጎችን እና የፀጥታ አባላትን ሕይወት ማቀጠፉን በጽኑ ያወገዘ ሲሆን፣ በተሰውት አባላት ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማዶች እና ባልደረቦች ላይ ለደረሰው መሪር ሐዘን መጽናናትን ተመኝቷል።

#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #ኤርትራ #ቦንጋ #ፖሊሶች #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና


የአፋር ክልል የኤርትራ ወታደሮች ጥቃት እያደረሱብኝ ነው አለ።

የአፋር ክልል መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ከህወሓት ታጣቂዎች ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ሲል ወንጅሏል።

የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ መሃመድ አሊ በክልሉ እየተዋጉ ነው ያሏቸው የኤርትራ ወታደሮች እንዲሁም ወታደራዊ ቁሳቁሶች መማረካቸውን አስታውቀዋል።

የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ስለመግባቱ እና እየተደረገ ባለው ጦርነት ላይ በቀጥታ ስለመሳተፉ የፌደራል መንግሥቱ እስካሁን ድረስ ያለው ነገር የለም።

የኤርትራ መንግሥትም የአፋር ክልል ባለሥልጣናት ለሚያቀርቡት ክስ እስካሁን ድረስ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም።

ነገር ግን ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ በማስታወቂያ ሚኒስትሩ በኩል በሰጣቸው መግለጫዎች የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ ተቀዋሚዎችን ይረዳል መባሉን አስተባብሏል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በዚህ ሳምንት ለአልጀዚራ በሰጡት መግለጫ የኤርትራ ጦር በክልሉ ላይ ቀጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "እየተዋጋን ያለነው የውጪ ኃይሎችን ፍላጎት ለማስፈጸም ከተሰባሰቡ እና ከተደራጁ ኃይሎች ጋር ነው" ብለው ነበር።

#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #ኤርትራ #አዲስአበባ #አስመራ #ኤምባሲ #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና


ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች።

10 የኤርትራ ዲፕሎማቶችም እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥታለች።

​በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግበቡን ተከተሎ፣ ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ማባረሯን ይፋ አድርጋለች።

​የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወደ 10 የሚጠጉ የኤርትራ ዲፕሎማቶች በአስቸኳይ አገር ለቀው እንዲወጡ ወስኗል።

ዲፕሎማቶቹ ትእዛዙ በደረሳቸው በ48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ እንደሚወጡ ተገልጿል።

​የኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህ አክራሪ እርምጃው እንደ ምክንያት የጠቀሰው፣ የኤርትራ መንግሥት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም በተቃራኒ በመቆሙ ነው ብሏል።

ከዚህ ውሳኔ ጋር ተያይዞ ሁለቱ አገራት የነበራቸው መንግሥታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጡ ተደርጓል።

​ይህ ድገተኛ ውሳኔ በሁለቱ ጎረቤት አገራት የወደፊት ግንኙነት እና በቀጣናው ሰላም ላይ ከፍተኛ ጥላ ያሳደረ ሆኗል።

#Ethiopia  #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa  #amharic_news #borkena_news  #ኢትዮጵያ #ኤርትራ  #አዲስአበባ #አስመራ #ኤምባሲ #አማርኛ_ዜና  #ዜና  #ቦርከና_ዜና


አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው ተሾሙ።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አቶ ሙስጠፌ መሃመድን በድጋሚ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አርድጎ መርጧል፡፡

የሲዳማ ክልል ምክር ቤትም መሳይ ሀይሉን (ዶ/ር) የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል።

#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #አማራ #ሶማሌ #ሲዳማ #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.