Postlar filtri


በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና የባንክ ሂሳብ ትስስር ላይ አዲስ ማብራሪያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ (Fayda) ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር ጋር እንዲያስተሳስሩ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት፣ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ባንኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ለተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አሳውቋል፡-

• ከሐረሪ ክልል እንዲሁም ከዋና ዋና የክልል ከተሞች እና ከአስተዳደሮች ውጭ በሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች ሂሳብ የከፈቱ ደንበኞች፣ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ይጠበቅባቸዋል።

• እግድ ስለተጣለባቸው ሂሳቦች፡

* በአዲስ አበባ፣
* ድሬዳዋ፣
* ባህር ዳር፣
* ጎንደር፣
* ደሴ፣
* ደብረብርሃን፣
* ኮምቦልቻ፣
* ሀዋሳ፣
* አርባ ምንጭ፣
* ወላይታ ሶዶ፣
* ሆሳዕና፣
* ወራቤ፣
* ቡታጂራ፣
* ወልቂጤ፣
* ሸገር፣
* ጅማ፣
* አዳማ፣
* ሻሸመኔ፣
* ቢሾፍቱ፣
* ባቱ፣
* አምቦ፣
* መቐለ፣
* አክሱም፣
* ዓዲግራት፣
* ጋምቤላ፣
* አሶሳ እና
* በሐረሪ ክልል የሚገኙ ደንበኞች፤ እስካሁን ትስስሩን ባለማድረጋቸው ምክንያት በሂሳባቸው ላይ የተጣለውን የወጪ ማድረግ እግድ (Debit Freeze) ለማስነሳት መታወቂያቸውን ማስተሳሰር ይኖርባቸዋል።

* ደንበኞች የፋይዳ አባልነታቸውን የሚያረጋግጠውን ቁጥር (FAN) በመያዝ በአካል በአቅራቢያቸው በሚገኝ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመቅረብ ወይም በይነ-መረብን (Website) በመጠቀም በ https://cbefayda.cbe.com.et በኩል በቤታቸው ሆነው ማስተሳሰር ይችላሉ።

* እስካሁን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያላወጡ ደንበኞች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ መታወቂያ ይዘው ወደ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ መመዝገብና የፋይዳ ቁጥራቸውን ማግኘት እንደሚችሉ ባንኩ አሳውቋል።

Via የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ




ሰላም ውድ የቴሌግራም አባላት! 👋

ጥሩ ዜና አለኝ። 🎉
Mastercard በጥሩ ዋጋ ማግኘት ከፈለጋችሁ፣ ይህን Telegram Account ያነጋግሩ። 💳

በMastercard የተለያዩ Online ክፍያዎችን መፈጸም፣ Subscription መክፈል፣ Online Shopping ማድረግ እና ብዙ International Services ላይ መጠቀም ትችላላችሁ። 🌍

👉 @simple_cards_support


" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።

በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም


" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ መጥታችሁ የራሳችሁን ንብረት በመለየት መረከብ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተሽከርካሪ እቃዎችን በመስረቅ የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦችንና የተሰረቁ እቃዎችን ይገዙ የነበሩ 2 ተቀባዮችን በድምሩ 7 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለጸ።

ፖሊስ በክፍለ ከተማው በተበራከተው የመኪና እቃ ስርቆት ላይ የተመሠረተ ክትትል ሲያደርግ ከቆየ በኋላ፣ ለአንድ ወር ከ15 ቀን በተካሄደ ምርመራ ተጠርጣሪዎቹን መያዙን ገልጿል።




💥💥💥  ምዝገባ ተጀመረ 💥💥💥
👉 በካቢን ክሩ
👉  AMT
ዘርፍ የኦንላይን ምዝገባ ተጀመረ
ሊንኩ ከስር የምትመለከቱት ነው 👇👇👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/eaa/applocation-for-local/Index


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


#Amhara

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ከሰኔ 3-5/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና 173,699 ተማሪዎች ውስደው ነበር።

ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ተማሪዎችም ውጤታቸውን https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ ፤ በሚመጣው ቅጽ ላይ የተማሪ መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት ፤ ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ።

ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው https://amhara.ministry.et/#/complaint ላይ በመግባት ቅሬታቸው ማቅረብ እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።


ሰበር ዜና እና አሳሳቢ ጉዳይ! ሴዶ ማርሻል እና ጆኒ መንገድ ላይ መደባደባቸው ተሰማ::

በጉጉት ለሚጠበቀው ታላቅ ፍልሚያ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው፣ ውልና ፊርማቸውን አጠናቀው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍለሚያቸውን ለማየት በከፍተኛ ጉጉት የሚጠብቃቸው ሴዶ ማርሻል እና ጆኒ ባልተጠበቀ ሁኔታ መንገድ ላይ ተገናኝተው በቡጢና በትግል መጋጠማቸው ታውቋል።

የግጭቱ አጀማመር አስገራሚና አሳዛኝ ነበር። ሴዶ ማርሻል ማህበረሰባዊ አሻራውን ለማሳረፍ ችግኝ ይዞ በቆመበት ሰዓት፣ ጆኒ በቅፅበት ከበስተጀርባው በመምጣት እግሩን ይዞ ለመጣልና ለመቆለፍ (Lock) ጥረት አድርጓል። ሆኖም ግን በአካባቢው በነበሩ የፖሊስ አባላትና በህዝብ ርብርብ ሳይከፋፈል ሊገላገሉ ችለዋል።

ይህ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ከመሆኑ ባለፈ፣ በኢትዮጵያ ስፖርት እና በስፖርተኞች ስነ-ምግባር ዙሪያ ትልቅ ጥያቄና ስጋት ፈጥሯል።

* በህጋዊ መንገድ መድረክ ተዘጋጅቶላቸው፣ ህዝብ በክብር የሚጠብቃቸው ስፖርተኞች በመንገድ ላይ የጎዳና ላይ ጠብ ውስጥ መግባታቸው ለሙያው ያላቸውን ክብር ያሳንሳል።

* ስፖርት ህፃናትና ወጣቶች በአርአያነት የሚከተሉት ዘርፍ ነው። እንዲህ አይነት ድርጊቶች ግን ለወጣቱ ትውልድ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋሉ።

* ማህበረሰባዊ በጎ ተግባር (ችግኝ የመትከል ስራ) እየተከናወነ ባለበት እና ሰላማዊ ድባብ ባለበት ቦታ ላይ እንዲህ አይነት ጥቃት መፈጸም ፍፁም ተገቢ አይደለም።

"እውነተኛ ስፖርተኛነት የሚለካው በሜዳ ላይ በሚታይ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ ከሜዳ ውጪ በሚታይ ጨዋነት፣ ትዕግስትና ስነ-ምግባር ጭምር ነው!"

ይህ አይነቱ ድርጊት በኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ላይ ጥላ እንዳያጠላ፣ የሚመለከታቸው አካላትና ስፖርተኞቹ ራሳቸው ቆም ብለው ሊያስቡበትና ራሳቸውን ሊገሩ ይገባል። ስፖርት ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት ነው!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ !

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን 97.48% የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።

የ2018 የትምህርት ዓመት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ 84,257 ተማሪዎች መካከል 82,137 የሚሆኑ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ሆኖ የተቆረጠውን 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበዋል።

768 ትምህርት ቤቶች ፈተና አስፈትነው 543 ያህሉ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ይህን ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ/ም


ለጣሊያን ሀገር የሥራ ዕድል የምዝገባ ጥሪ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በጣሊያን ሀገር በሆቴልና መስተንግዶ (Hospitality) ዘርፍ የሰው ኃይል ይፈለጋል።

የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ጣሊያን ሄደው መስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን።

🏨 የሥራ መደቦች፦

🔹ጸሐፊ(Commis de Rang / F&B Server) – 19 ቦታዎች

🔹 የፅዳት ሰራተኛ (Room Attendant / Housekeeping) – 20 ቦታዎች

🔹 ረዳት ሼፍ (Commis Chef) – 13 ቦታዎች

🔹 የእቃ አጣቢ (Kitchen Steward / Dishwasher) – 11 ቦታዎች

🔹 የወለል ረዳት (Floor Porter / Houseperson) – 3 ቦታዎች

🔹 የቢሮ አስተናጋጅ (Front Office Agent / Receptionist) – 4 ቦታዎች

🔹 የጥገና ቴክኒሺያን (Maintenance Technician) – 1 ቦታ

🔹 የስፓ ቴራፒስት / የማሳጅ ባለሙያ (Spa Therapist / Masseuse) – 1 ቦታ

📌 የማመልከቻ መስፈርቶች

✅ ከስራው ጋር ተያያዥ የስራ ልምድ ያላቸው ተመራጭ ናቸው።

✅ ለአብዛኛዎቹ የስራ መደቦች የእንግሊዝኛ እና/ወይም የጣሊያንኛ ቋንቋ እውቀት ያስፈልጋል።

✅ ለአንዳንድ የሙያ መደቦች ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫ ወይም የሆቴል እና መስተንግዶ ትምህርት ተመራጭ ነው።

📅 የሥራ ቆይታ

አብዛኛዎቹ የስራ መደቦች ለ2026/2027 የክረምት የቱሪዝም ወቅት የሚቀጠሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የስራ መደቦች ዓመቱን ሙሉ ወይም በበጋና በክረምት ወቅት የሚሰሩ ናቸው።

✅ ለመመዝገብ

1.Labor ID ካሎት በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ያመልክቱ።

2.Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦

1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ።
በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ።

1. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ https://forms.lmis.gov.et/italy-hotel/ ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ።

ማሳሰቢያ

• ምዝገባም ሆነ ስምሪቲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ብቻ የሚከናወን ሲሆን ሚኒስቴሩ ለየትኛውም አካል ውክልናም ሆነ ፈቃድ አለመስጠቱን እንገልፃለን።
• ምንም አይነት ክፍያም የለውም


ተማሪዎች ውጤታቸው መመልከት ይችላሉ።

በ2018 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ ተደርጓል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ይህንን ማስፈንጠሪያ https://aa.ministry.et/#/result በመጫን መመልከት ይችላሉ።

ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ/ም


🚀 NEXORA EDITING ACADEMY ተከፍቷል! 🎬
Do you want to learn professional video editing and start earning from your skills?

በ Nexora Editing Academy ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ፕሮፌሽናል ደረጃ በተዘጋጀ ሙሉ ፕሮግራም ይማራሉ።

📚 What You'll Learn:

✅ Module 1: የቪዲዮ ኤዲቲንግ መግቢያ
✅ Module 2: የኤዲቲንግ መሰረታዊ ክህሎቶች
✅ Module 3: ፕሮፌሽናል Motion Graphics
✅ Module 4: Text & Typography ንድፍ
✅ Module 5: Visual Effects (VFX)
✅ Module 6: Color Correction & Color Grading
✅ Module 7: Sound Design መሰረት
✅ Module 8: TikTok እና Short Video Editing
✅ Module 9: Commercial & Client Projects
✅ Module 10: Freelancing እና ገንዘብ መስራት

🎁 Bonus Resources

⚫️ Premium Presets
⚫️ Project Files
⚫️ Templates
⚫️ Private Support Community
⚫️ Lifetime Updates

💰 የኮርሱ ዋጋ: 1000 ብር ብቻ

🎯 ለሚስማማቸው:
✔️ ጀማሪዎች
✔️ Content Creators
✔️ Freelancers
✔️ በቪዲዮ ኤዲቲንግ ገንዘብ መስራት የሚፈልጉ
🔥 TikTok, YouTube Shorts, Reels እና ፕሮፌሽናል የclient ስራዎች የሚጠቀሙትን ትክክለኛ ክህሎት ይማራሉ።

📩 አሁኑኑ ይመዝገቡ: @NEXORA_EDITING_ACADEMY




ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ይፋ ተደረገ።

ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት መመልከት ይችላሉ።

መጀመሪያ የተቀመጠውን ሊንክ ይጫኑ በመቀጠል 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤት መመልከት ይቻላል።

ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ/ም




ሚሊየን ሎተሪ 2018 ዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል::



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.