ወደ ማወቅ መጓዝ ጥድፊያን ይከላል። በጥድፊያ የሚደረስ እውቀት የለም። ማዝገም ነው ማወቅ። በሩጫ ማስተዋልን ጸጋ ማድረግ አይቻልም። አዝጋሚ ነው ጉዞው፥ የረጋ ጥሞና የሚያደምቀው ልምላሜም እንዲሆን የሰከነ ልብ ይፈልጋል።
እየሮጡ ማወቅ ማወቅን መካድ ነው። ቅጽበቶች ሁሉ ሰፊ የእውቀት ምዕራፎች ይወልዳሉ የተረጋጋ ነፍስ ላለው አእምሮ። ስሜቶቻችን ሲያሮጡን አእምሯችን ሊያረጋጋን ይሞክራል። በውስጣችን ያለው በላጭ ኃይል እኛን የሰራው ነው። ስንኖር የሚመራን ወይ ከስሜታችን ወይም ከማሰባችን ካንዱ ይበልጥ ይጎላል።
ይሔም በምናጸባርቀው የየእለት ጠባያችን ይገለጣል። የታየው የስሜታችን ወይም የማስተዋላችን ገሃድ ስለሚሆን በምንኖረው ህይወት አዋቂነት ወይም የስሜት ሰውነታችን ፍንትው ብሎ ለሌሎች የሚታይ ይሆናል። በአካባቢያችን የሚሰጠን ስምም ከዚሁ አመላችን አይርቅም።