በስዊድን የካሽ ገንዘብ መቅረት ህዝቡን ለዘረፋ እያጋለጠው ነው
ስዊድን ካሽ አልባ ማህበረሰብን ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት ለብዙ የዲጂታል ወንጀሎች እየተጋለጠች እንደሆነ ተዘግቧል። ዘራፊዎቹ እንደ ባንክ አይዲ ያሉ መረጃዎችን በመጠቀም የባንክ ደምበኞችን ይዘርፋሉ፣ ለምሳሌ ኤለን የምትባል ሲውዲናዊ ወጣት ልብስ ለመሸጥ አካውንቷን በምታስገባበት ሰአት በሳይበር ወንጀለኞች አንድ ሺህ ዶላር መሰረቋን ዘግባለጭ።
በስዊድን እየትባባሰ በመጣው የዲጂታል ገንዘብ ስርቆት በ2023 ብቻ 1.2 ቢሊዮን ክሮነር የኦንላይን ዘረፋ ተፈጽሟል ይህም በ2021 ከተፈጸመው ጥቃት በእጥፍ የጨመረ ነው። ይህ የወንጀል ኢኮኖሚ የስዊድንን 2.5% ይሸፍናል።
ካሽ የማይጠቀም ማህበረሰብ መገንባት ጥሩ ጎኖች ቢኖሩትም በዲጅታሉ አለም የሚሰራው የወንጀል አይነት እየተራቀቀ እና ከጊዜ ወደጊዜ ዘመናዊ እየሆነ ስለመጣ ምንም እንኳን የባንኮችን ሳይበር ሰኩሪቲ ለመጨመር ቢሞከርም በዲጂታል የባንክ ስርሃት ላይ እየተጋረጠ የመጣው አደጋ እየጨመረ መጥቷል።
በነዚህ ወንጀለኞች የሚፈጸሙ የማታለል አይነቶችን በሌላ ጊዜ በሰፊው ምንመጣበት ሲሆን ለአሁን ግን በእንደዚህ አይነት ዘራፊዎች እንዳንታለል ማድረግ ያለብንን ጥንቃቄዎች እንይ፡
1 ጠንካራ ፓስዎርድ መጠቀም እና ፓስዎርዳችንን አለማጋራት
2 የምንጠቀማቸውን የባንክ እና የተለያዩ የዲጅታል ገንዘብ መተግበርያዎች በየጊዜው አፕዴት ማድረግ
3 ከባንኮች እና ከተለያዩ የመርጃ ምንጮች የሚሰሙ የሳይበር መረጃዎችን መከታተል
4 እንደ ቪፒኤን ያሉ ኔቶርካችንን ሰኪውር የሚያደርጉ መተግበርያዎች መጠቀም
5 በስልክ ከሚመጡ ከምንጠቀመው ባንክ ጋር የሚመሳሰሉ መልዕክቶች እና ፖፕአፖች ስሚኖሩ እነሱን በተጠንቀቅ መፈተሽ
እነዚህን ጥንቃቄዎች በማድረግ ከሳይበር ወንጀለኞች ራሳችንን ማዳን እንችላለን።