የኔ ልጅ እባክህ ላስቸግርህ እርዳኝ(መለኩሴው ጫት ከምሸጥበት መደብ ፊት ቆመው
አይ አባ እኛም እኮ ቸግሮናል ኑሮ ውድ ነው(ወደ ኪሴ እየገባሁ
አይደለም ልጄ እኔኮ ብር ፈልጌ አይደለም(ሰው እንዳይሰማ በሹክሹክታ እያወሩ
እሺ ምን ፈልገው ነው አባቴ መንገድ ልጠቁሞት?
አረ በፍፁም!!እኔማ ከዝች ከጫቷ ቆንጠር አድርገህ እንድትሰጠኝ ብዬ ነበር(በመሸማቀቅ አይናቸውን ስብር አድርገው
የተቀመጥኩበት ወንበር የሰመጠ ያህል ተሰማኝ ጥያቄያቸውን ተከትሎ አፌን ከፍቼ አይኔን አጉረጥርጬ ቅንድቤን ሰቅዬ አየኋቸው።ምናልባት ይህን ቃል የሠማሁት አጠገቤ ካለ የጫት ደንበኛዬ እንዲሆን በማሰብ
አከባቢዬን ቃኘሁት ግን ሁሉም ተርዚናውን አጭቆ አፉን የሚያላውስ የለም የተናገሩት እኚ መለኩሴ ናቸው?ጆሮዬ ነው?ግራ በመጋባት ደርቄ ስቀር..
የኔ ልጅ አልሰማከኝም?እባክህ ሱስ ሆኖብኝ ነው ሰው ሳያይ ቀስ ብለህ ስጠኝ
ተነስቼ መሮጥ ፈለኩኝ፣አልያም በአስማት ከዛ ቦታ
የሚሰልበኝን ተአምር ባገኝ ብዬ ተመኘሁ ግን እኚ በነጭ ቆብና በጥቁር ካባ ያሸበረቁ ለሠማይና ለምድር የከበዱ
መልዐክ የሚመስሉ መለኩሴ አሁንም ከፊቴ ፊትለፊቴ ቆመው በልምምጥ እያዩኝ ነው
አባ ይቅርታ እኔ ለእርሶ አልሸጥም
እንዴ ለምን እኔ ሰው አይደለሁ?
አይ እርሶ የእግዜር ሰው ኖት ሌላ ቦታ ይሂዱ
ብታቅማ አንተም የእግዜር ልጅ ነህ ግን ደሞ ሱስ ነው የምልከው ልጅ አጥቼ ብቸገር እንጂ ..
እኚ መለኩሴ ለምን አይሄዱም?ደግሞስ እውነት ብሰጣቸው እዚ አደባባይ ላይ ይቀበሉኛል?የሚሆነውን ለማየት እጄ እየተንቀጠቀጠ አንድ እስር ጫት በፔስታል አድርጌ እየፈራሁ ወደ መለኩሴው እጄን ስዘረጋ
ጎሽ የኔ ልጅ በል እንካ ሂሳብክን(በደስታ እየተፍለቀለቁ
እኔ የእርሶን ብር አልፈልግም ሂዱልኝ ከዚ ቦታ ሁለተኛ እኔ ጋር እንዳይመጡ(እኚ መለኩሴ ዛሬ ምነው ሚስማር ካልዘነበ መብረቅ ካልወረደ አሉሳ?ንዴቴ አናቴ ላይ ወጥቶ
አንባረቅኩባቸው
የማየው የምሰማው ነገር ድብልቅልቅ አለብኝ እውነት ግን ለምን ተናደድኩ?እኚ ሰው ቆብ ያድርጉ እጂ እንደኔ ሰው አደሉ?ደሞስ እኔ ማን ሆኜ ነው ምወቅሳቸው? ምናልባትም አንዱ የቸገረው ዱርዬ ጫት መቃም ፈልጎ የፈጠረው ድራማ ቢሆንስ?(ጭንቅላቴን በጥያቄ ወጥሬ ያልተሸጠ ጫቴን እያስተካከልኩ መልሶ የሚጥል ድንጋጤ ወረረኝ...ያኚ ጫት ካልሰጠከኝ እያሉ ሲነታረኩኝ የነበሩት መለኩሴ ለጫት ሲንገበገቡ መስቀላቸውን የጫት
መሸጫዬ ላይ ጥለውት ሄደዋል!!
ድንጋጤ ቅፅበታዊ ሲሆን ፍርሀት ትከሻ ሲወዘውዝ የገጠመኝ በዚህ ቀን ነበር ፍርሀት የማያውቀኝ ሰውዬ እየተርበተበትኩ መስቀሉን አንስቼ ያኚ መዘዘኛ መለኩሴ ወደሄዱበት አቅጣጫ ከነፍኩ..ደርሼባቸው በእጄ የያዝኩትን መስቀል እስክሰጣቸው ልቤ ቆሟል ከኋላ አውሬ የሚያባርረኝ ያህል እየተሰባበርኩ ከሩቁ አባ መቋሚያቸውን እያስቀደሙ ሲራመዱ አየኋቸው ግን
እንደ እብድ ብጮኽ አባ አይሰሙም የምርቃና ሰአታቸው ደርሷል.
አባ..አባቴ..ይቁሙ..(አጠገባቸው ደርሼ ትንፋሼ
እየተቆራረጠ ጠራኋቸው
አባ የቤ/ክኑ በር ላይ ደርሰው እየተሳለሙ ጥሪዬን ሰምተው
በድንጋጤ ዞር አሉ
አቤት ምን አጣህ ምን ፈለክ?(በቁጣ ግንባራቸውን ቋጥረው እያዩኝ
አረ እኔ መስቀሎትን ጥለው.(በፍርሀት እያየኋቸው
በል ና እዚህ ጥሩ አይደለም ውስጥ እቀበልሀለው
እኚ ሰው ዛሬ ለምን አይተውኝም?ገብቼ ደሞ እንቃም ሊሉ ነው?ደሞስ ጫቱን ወደ ቤ/ክ ይዘው ሲገቡ አያፍሩም?በዛ ሁሉ ድካም ውስጥ ይሄ ሀሳብ አእምሮዬ ላይ ሲያቃጭል ዘገነነኝ።ግን አማራጭ ስለሌለኝ ተከትያቸው ቤ/ክኑን አልፈን እስከ ቤታቸው አደረስኳቸው።
ና እስቲ አረፍ በል ቆንጆ ምሳ አለ
አረ አባ መስቀሉን ይቀበሉኝ እኔ ለዚ ቦታ አልገባም ልሂድ...
ግድ የለም አትፍራ..(አባ ፈጠን ብለው በሰሀን እንጀራ በምስር ወጥ ይዘው መጡ...
እኚ ሰውዬ ግራ እያጋቡኝ ነው ውስጤ ብዙ ጥያቄ አለ ይሄን የመሠለ የመመረጥ ህይወት ትተው አለማዊ ነገር መመኘታቸው እያስገረመኝ...
ቆይ አባ ጫት መቃም ሀጥያት አይደለም እንዴ? (በጥርጣሬ ጠየኳቸው
አረ በፍፁም ሀጥያት አይደለም!ይኸው አንተ ትቅም የለም እንዴ?
እኔማ ሀጥያተኛ ነኝ ሁሌም ስራዬ ይህ ነው እርሶ ግን ..
ጎሽ የኔ ልጅ ተባረክ አየህ አሁን ትልቅ ቁም ነገር አወራክ ሰው ከፈጣሪ እንዳይታረቅ የሚያደርገው ዋናው ነገር ሀጥያት ሰልጥኖበት ሳለ ሀጥያተኛ ነኝ ብሎ አለማመኑ ነው ሰው ሁሉ ሀጥያተኛ ነው ግን ደሞ መርሳት የሌለብህ እግዚአብሔርም መሀሪ መሆኑን ነው።(አባ እያወሩኝ ከሰል ማንደጃቸው ላይ የገዙትን ጫት እያስቀመጡ
ታድያ ሀጥያት ከሆነ ለምን እኔ ጋር መጥተው ገዙ?ደሞስ ለምን ያቃጥሉታል?(ጋዝ አርከፍክፈው የሚያቃጥሉትን ጫት ሲንቦገቦግ በድንጋጤ እያየሁ..
አየህ ወጣትነት ማለት እንደዚህ እሳት ነው የያዘውን የቀረበውን ሁሉ ይፈጃል።ይህ እሳት ንፋሱ ወዳለበት አቅጣጫ እንደሚነድ ሁሉ ወጣትነትም አለም ባነፈሰችው ባራገበችው የሀጥያት አየር እንድንገፋ ያደርገናል።ይህ እሳት እንዲነድ ጋዝና ወረቀት ጨምሬበታለሁ ያለዚያ እንዲህ አይነድም ነበር ወጣትነትም ከልክ በላይ ሰውን
እንዲያነድ እና እንዲያጠፋ በጋዙ ቦታ ጫት ሱስ ዝሙት የመሣሠሉትን ሰይጣን ይጨምርብናል ያኔ እንደዚ እሳት በአለም ላይ እንነዳለን።
ቅድም ጫት ስጠኝ ስልክ ድንጋጤክን አስተውያለሁ..አንተ እኔ እንዳልገዛ እንዳልቅም እየከለከልከኝ እንዴት ለራስህ መሆን ያቅትሀል?እኔም አንተም በእግዜር አምሳል የተሠራን ክቡር ፍጥረታት ነን ለኔ ያልተገባ ሀጥያት እንዴት ላንተ ይገባል?ጫት ማለት ለጊዜያዊ መነቃቃት እና ደስታ ለስጋችን የምንጠቀመው እፅ ነው ይሄን ተከትሎ ደሞ መጠጥ ስካር ዝሙት የሚባል ሀጥያት ይመጣል።አንተ ይህን ጫት ቤ/ክ ይዤ ስገባ የጨነቀክ የእግዚአብሔር ቤት ስለሆነ አደል? በምድር ላይ ግን ሰውን የሚያክል የእ/ ር ቤተመቅደስ የለም!እና የእግዜር ቤተመቅደስን በጫት በሱስ ታረክሳለህ?ሱስ ማለት እግዜር የሠጠኝ ደስታ ሰላም አቅም አንሶብኛልና ሌላ ተጨማሪ ነገር ያስፈልገኛል ብሎ መልፋት ከፈጣሪ መጣላት በስራው መጠራጠር ነው! ስለዚህ የመዳን ቀን ዛሬ ነውና ከፈጣሪህ ታረቅ አምላካችን ሀጥያትን እንጂ ሀጥያተኛን አይጠላም ከሴሰኞች ጋር አትተባበሩ1ቆሮ5-9እንዳለ መፅሐፍ ለሀጥያት ለሱስ
አትተባበር።
ቅድም እንደዛ ሲነድ የነበረው እሳት አሁን አመድ ሆኗል! ሰው እንዲ ነው..ወጣትነት ማያልፍ ይመስላል ግን እንደዚ አመድ መክሰማችን አይቀርም።''ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን
ትወልዳለች"ያዕ1፥15 ስለዚህ የሞት ሞት እንዳትሞት የስጋ ምኞትህን ለፈጣሪ አስገዛ።
እኔም ሱሰኛ ነኝ ግን የፆም የፀሎት የስግደት ነው።ቅድም መስቀሌን ጥዬው ሳይሆን አንተ ተከትለከኝ እንድትመጣ ስለፈለኩ ነው ጥዬው የመጣሁት።አንዳንዴ ሰወች ወደ ቤ/ክ መምጣት ሲደክሙ ቤ/ክ ወደ ህዝቡ መሄድ አለባት እኔ የቤ/ክ አንድ አካል ስለሆንኩ አንተን ፈልጌ መጣሁ ታድያ ተሳክቶልኛል?
በትክክል አባ!ሁለተኛ እዚ ሀጥያት ውስጥ አልገባም እንደኔ ያሉትንም ለማምጣት ቃል እገባለሁ ይቅር በሉኝ አባቴ(እንባ ተናንቆኝ እግራቸው ስር እየወደቅኩ
እግዚአብሔር ይቅር ይበልክ በል ተነስ
አባ በፈገግታ ተሞልተው አነሱኝ እኔም የማትጠገብ ምስር እና የማይጠፋ ምክር ተመክሬ ቡራኬ
ተቀብዬ ልቤን ለፍቅሩ አስገዝቼ ወደቤቴ
ተመለስኩ።
✍️chaቻ
@cherstianawiwetat