የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች "ፋይዳ" መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደንበኞች "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ዓለምእሸት መሸሻ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት እና መወሰኑን ተጠቁሟል።
በመሆኑም ከህዳር 1 ቀን 2017 ጀምሮ ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ተገልጿል።