የቴሰስ መርከብ
የቴሰስ መርከብ እንቆቅልሽ በጽሑፍ ደረጃ የተገኘው በጥንታዊው የግሪክ ፈላስፋ ፑልትሪክ ስራ ላይ ነው፡፡ በፑልትራክ ስራ ላይ ቴሰስ (አቴንስን የመሰረተ ንጉሥ ነው) ከረጅም የባህር ጉዞ ላይ ሲመለስ ይተርካል፡፡ በጉዞው ላይ አሮጌና የበሰበሰው የመርከቢቷ ጣውላዎች በአዲስ ተተክተው አልቀው ነበር፡፡ ጉዞው ረጅም ነበርና የመርከቧአካሎች በየጊዜው ይበላሹ ይበሰብሱ ነበር፣ እናም ቴሰስ በመንገዱ ላይ የመርከቧን አካሎች በአዳዲስ አካላት እየለወጠ መንገዱን ቀጠለ፡፡ ይህም ጥያቄን አስነሳ " ንጉሡ የሄደባትና የተመለሰባት መርከብ ተመሳሳይ ናት ?" ምናልባት ከነባሮቹ የመርከቧ ጣውላዎች አንዱ ሳይቀየር ቢቀርስ ? መቼስ ነው መርከቡ ሌላ መርከብ የሆነው? በግማሽ ሲቀየር ወይንስ የሆነ ያህል እና የተወሰነ አካሉ ሲቀየር ?
የቶማስ ሆብስ ጭማሪ
ከቴሰስ መርከብ እየቀየርን የወሰድናቸው አሮጌ አካላትን ብንሰበስባቸውስ ?ለቃቃሚ ቢኖርና የመርከቧን ስብርባሪ ጣውላዎች እያነሳ የራሱን መርከብ ቢሰራስ ? ሲል እንቁቅልሹን ይበልጥ አወሳሰበው፡፡ አንድ ነገርን እናውቃለን፣ እነዚህ ሁለት መርከቦች (ከቅያሪ ወይም ልቅምቅም አካላት የተሰራችው እና በመንገድ ላይ ሙሉ አካሏ የተቀየረላት መርከብ አንድ ሊሆኑ እንደማይችሉ፡፡ በዚህ ተቃርኖ እንቆቅልሽ ላይ የቴሰስ መርከብ የትኛዋ ናት ? አንድን መርከብ መርከብ የሚያሰነው የተሰራበት የአካል ክፍሉ ነው ? ወይስ መዋቅሩ ? ወይስ የመርከቡ የኋላ ታሪክ ?
ራሴላስ ጋሻነህ (እንደተረጎመው )