አንዳንድ ታሪኮች ርእስ የላቸውም - ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ።አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም - ኖረው እንዳልኖሩ።አንዳድ ገድሎች አልተዘከሩም - የባከኑ መሥዋዕትነቶች ይባላሉ። አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም - እንዳልተፈፀሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ። አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ተጋርደዋል - ዙሪያውን ገላምጠን ልብሳችንን አራግፈን እንቀጥላለን።አንዳንድ ሕዝቦች በወል ተረስተዋል-ለመታሰቢያ የቀረላቸው ምንም የለም። አንዳንድ ኮቴዎች በመረሳት ተጠቅተዋል - አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል።ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ልቦች በሦስት መሃላ ተክደዋል።
ሄኖክ በቀለ