Darash Media


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣️‼️ትክክለኛው ቻናል ይሄ ብቻ ነው።
ይህን ቻናሌን ለሌሎች ሰዎች ሼር አድርጉ።
#አመሰግናለሁ🙏
ለማስታወቂያ ስራ👇
@Dershsupport

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


በተወዳጁ ቻናላችን ስራዎትን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ???

ያናግሩን👇
@Dershsupport
@Dershsupport
👆 ማስታወቂያ ለማሠራት


ስልክ መስራት ጀምሯል‼

ለቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት በመቀሌ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም መስራት መጀመሩ ተሰምቷል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ የሞባይል የስልክ ጥሪ ድምፅ እና የሞባይል ዳታ (ኢንተርኔት) አገልግሎት በአሁኑ ሰዓት መስራት ጀምሯል።

የአገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ የመመለስ አሁንም በስፋት እየተሰራ ነው ተብሏል።

@darashMedia
@darashMedia


ወደ ግብፅ አቅንተው ከአልጀዚራ የአረብኛው ክፍል ጋር ቆይታ ያደረጉት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት “ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት መብትና አቅሙ አላት” ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል። ሐሰን ሼኽ አክለውም ኢትዮጵያ በሀገራቸው በሶማሊያ ግዛት በኩልም ቢሆን የባሕር በር ብታገኝ የሞቃዲሾ ይሁንታ መሆኑን አሳውቀዋል።

@darashMedia
@darashMedia


መቀሌን ለቀናል-ህወሓት‼️
ህዝባችን ላይ ሊፈፀሙ ከሚችሉ ጥቃቶች በመስጋት መቀሌን ለቀን ወጥተናል ሲል ህወሓት አስታወቋል።
ሰማዩ የእኛም እንደሆነ በዚያው ይቀጥላል፣ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብሏል።
ከሰሞኑ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአፋር ክልል ለተፈፀሙ የድሮን ጥቃቶች ህወሓት ሀላፊነት ወስዷል።

@darashMedia
@darashMedia


ሰው የበላችው ዩጎዝላቪያ........

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እስከ 1980ዎቹ ድረስ በአለም በኢኮኖሚና በወታደራዊ መዋቅር ጠንካራ ከሚባሉት ሃገራት ተርታ የምትሰለፍ በጣም ወሳኝ የአለም ክፍል ላይ የምትገኝ ሃገር ነበረች::

ነበረች ነው
ስሟም ዩጎዝላቪያ ይባል ነበር። ይህች ሃገር ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ አንድ ያደረጋትን መሪ በ1980 በሞት ታጣዋለች። በዚህ ጊዜ ኢኮኖሚዋ ይወድቃል፣ ፖለቲካዋ ይረብሻል።

የኮሙኒዝም ስርዓት መዳከም ሲጀምር የፖለቲካ መሪዎች የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም የብሔረተኝነት ስሜትን መቀስቀስ ጀመሩ። ተዋደው፣ ተቻችለው ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች በፖለቲከኞች ሴራ ተቃቃሩ። አንድ ፖለቲከኛ ተነስቶ ጠላት ያለውን ህዝብ ሲሰድብ ከሱ ወገን ተውም ያለው የለ። ከዚያኛውም ወገን እንደዚሁ። ከመካሪውና ከተው ባዩ ይልቅ ያኛው ሕዝብ ሲሰደብ ማዶና ማዶ ቆመው ለጦርነትና ለፀብ ተጠራሩ።

ከዛም የዘሩትን አጨዱ በጦርነት ተማገዱ ታላቋ ዩጎዝላቪያ ትንንሽ መንደሮች ሆነች። ከ1990 - 2001 በተደረጉ የተለያዩ ጦርነቶች እስከ 140ሺ የሚጠጉ ንፁሐን ሰዎች ተገደሉ። የዘር ጭፍጨፋ ተፈጸመ። እስከ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች አካል ጉደተኛ ሆኑ። የሃገሪቱ ግማሽ የሚሆነው ህዝብ ከሚኖርበት አካባቢ ተፈናቀለ።

በመጨረሻም ከ30,000 - 50,000 የሚሆኑ ሴቶች ተደፈሩ። እህቱንና እናቱን ያልጠበቀ ወንድ ደግሞ ሃገሩን አይጠብቅምና ዩጎዝላቪያም ተደፈረች 7 ትናንሽ ሃገርም አደረጓት። የሚገርማቹህ ዛሬም በእነዚህ 7 ትንንሽ ሃገሮች ውስጥ ሌላ የብሔርና የጎሳ ጥያቄ አለ ወደፊት ደግሞ ተባዝተው አስር ሊሆኑ ይችላሉ።

ምን ልላቹህ ፈልጌ ነው ቆም እንበልና እናስብ። እንደ ህዝብ ተበላሽተናል። በለው እንጅ ተው የሚል ጠፍቷል።

ሰው ሲሞት አየን ዝም
ሴቶች ሲደፈሩ ዝም
ህፃናት ተደፍረው ሲገደሉ መጀመሪያ ብሔራቸውን ነው የምንጠይቀው። የኛ ብሔር ከሆኑ ዝም ለማለት የሌላኛው ከሆኑ ደግሞ ለመሳደብ።

እንደ ህዝብ ተበላሽተናል፣ እንደ ሰው ስናየው ደግሞ ሞተናል። በሔድንበት ፍቅርን፣ መቻቻልን፣ ኢትዮጵያዊነትን እናውራ።


ለአስተያየት 👇
@Dershsupport

@darashMedia
@darashMedia


ጦርነት ገጥመን አንድ ሰው ከሚሞት: እየተጨቃጨቅን፣ እየተወያየን 100 አመት ብንቆይ ይሻላል።

ያ የሚሞተው ወጣት እናት አለውና!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
👆የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመቀሌ

@darashMedia
@darashMedia


በመቀሌ ከተማ ዘረፋ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ‼️

በመቀሌ ከተማ የመንግሥት እና የግል ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ እየተፈፀመ መሆኑ ታወቀ።

ከትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ ጀምሮ ሁሉም ማለት ይቻላል የመንግስት ቢሮዎች እና የግል ነጋዴዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘረፉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በተለይ በህግ ጥላ ስር የነበሩና ከእስር ቤት የወጡ ግለሰቦች በከፍተኛ ሁኔታ ዘረፋ እየፈፀሙ ነው ተብሏል።

@darashMedia
@darashMedia


#AddisAbaba

መንገዶች ተከፍተዋል።

ኢሬቻ 'ሆራ ፊንፊኔ' በዓል በመጠናቀቁ በአዲስ አበባ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተዋል።

@darashMedia
@darashMedia


የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ!
 
ከበርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተመሙ ታዳሚዎችን ያሰባሰበውና ለሁለት ቀናት የሚቆየው የኦሮሞ ህዝብ የኢሬቻ በዓል የመጀመሪያ ቀን ስነ-ስርዓት በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
 
የኦሮሞን ህብረ-ብሄራዊ እሴቶች የሚያንጸባርቁ ባህላዊ አልባሳትን የለበሱ ወጣቶች (ቄሮዎችና ቀሬዎች)፣ የሲንቄ እናቶች እና አባ ገዳዎች በዚህ ደማቅ በዓል ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።ትላንት ከልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለመጡት እንግዶች በአምስቱም የአዲስ አበባ መግቢያ በሮች  የሞቀ አቀባበል ተደርጓል።
 
በአዲስ አበባ የሚደረገው ይህ ስነ-ስርዓት፣ እሁድ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ከሚከበረው የዓመቱ በዓል በፊት የሚከናወን ነው።
 
በፀደይ (አርፋሳ) እና በበጋ/መኸር (ብራ) ወቅቶች የሚከበረው የኢሬቻ በዓል፤ የምስጋና፣ የምርቃት፣ የሕዳሴና የእርቅ ምልክት የሆነ የኦሮሞ ባህላዊ በዓል ነው።

@darashMedia
@darashMedia


Update‼️ወደ ኤርትራ ወስደዋቸዋል‼️

ጀነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ 5 ከፍተኛ አመራሮች በሃይል ወደ አስመራ መወሰዳቸው ተገለጸ።

በመቐለ ከተማ፣ ላጪ አካባቢ ከሚገኘው «HZ» ሆቴል ታስረው የነበሩት ጀነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ አመራሮች በሃይል ተወስደው ወደ ኤርትራ (አስመራ) መወሰዳቸው ተገለፀ

በሃይል ተወስደዋል የተባሉት ግለሰቦች፦

🚫ጀነራል ታደሰ ወረደ
🚫 ኢሳይያስ ታደሰ
🚫ተወልደ ዕምበብ
🚫ነጋሽ (ሸኾርተት)
🚫 ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር (ሓመድ ሸጠ) ናቸው።

ግለሰቦቹ በላጪ አካባቢ በሚገኘው HZ ሆቴል አንድ ክፍል ውስጥ ታስረው የቆዩ ሲሆን፣ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለሁለት ቀናት ያህል ዓድዋ ላይ እንዲቆዩ ተደርገው እንደነበር ታውቋል። ከዛ በመቀጠልም ወደ መቐለ HZ ሆቴል እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለት በሆቴሉ ዙሪያ ከፍተኛ የጸጥታ ውጥረት ሰፍኖ ውሏል።

በመጨረሻም በለሊቱ 9:00 ገደማ ታጣቂዎች የሆቴሉን በር በሃይል በመስበር፣ የታሰሩትን አመራሮች በዓዲግራት መስመር አድርገው ወደ ኤርትራ ወስደዋቸዋል ተብሏል።

@darashMedia
@darashMedia


🚨 እስከ 35% ቅናሽ! ያለምንም ወለድ እና የዋጋ ጭማሪ በምርጥ ቦታዎች የቤት ባለቤት ይሁኑ! 🚨
ኑሮዎን በአዲስ አበባ ማዕከላዊ እና ውድ ስፍራዎች ለማድረግ አስበዋል? ቴምር ሪል ስቴት (Temer Properties) እጅግ ማራኪ በሆኑ የክፍያ አማራጮች ዘመናዊ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን አቅርቦልዎታል።
✅ በየትኛው ቦታ መኖር ይፈልጋሉ?
📍 መገናኛ (ቤልቪው ሆቴል አጠገብ)
📍 ቡልጋሪያ (አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት)
📍 አዋሬ (ቤተመንግስት አጠገብ)
📍 ሳር ቤት (አዳምስ አጠገብ)
💰 ልዩ የክፍያ አማራጮች (በኢትዮጵያ ብር ብቻ)፡
100% ለሚከፍሉ፡ እስከ 35% ታላቅ ቅናሽ!
40% ቅድመ ክፍያ፡ የ 10% ቅናሽ ተጠቃሚ ሲሆኑ፤ ቀሪውን 60% ቤቱን ሲረከቡ ይከፍላሉ።
20% ቅድመ ክፍያ፡ ቀሪውን በ16 ዙር፣ በረጅም ጊዜ ከፍለው ይጨርሳሉ።
🏠 የአፓርትመንት አማራጮች (ከስቱዲዮ እስከ 3 መኝታ)፦
• ስቱዲዮ (ከ 32 ካሬ ጀምሮ)
• 1 መኝታ (ከ 60 ካሬ ጀምሮ)
• 2 መኝታ (ከ 90 ካሬ ጀምሮ)
• 3 መኝታ (ከ 118 ካሬ ጀምሮ)
🎯 ልብ ይበሉ፡ ክፍያው ያለምንም የባንክ ወለድ እና የግንባታ እቃዎች የዋጋ ጭማሪ የሚፈፀም ነው!
እነዚህ ውሱን ቤቶች ከመጠናቀቃቸው በፊት አሁኑኑ ይደውሉልን!
📞 +251941255153 👈 በ whats up ያገኙናል
User name telegeram👉 @wendii02


የኬንያው ግዙፍ  ባንክ ወደኢትዮጵያ ገበያ ሊገባ ነው

የኬንያው ኤንሲቢኤ ባንክ (NCBA Bank) በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል። ባንኩ አዲስ ባንክ የመክፈት ሀሳብ የሌለው ቢሆንም፣ ከሀገር ውስጥ ባንኮች ጋር ድርድር ስለመጀመሩ እስካሁን የሰጠው ግልጽ መረጃ የለም።

ኤንሲቢኤ ባንክ በሁለት ግዙፍ የፋይናንስ ተቋማት ውህደት የተመሠረተ ሲሆን፣ በዲጂታል ባንክና በብድር አገልግሎት በምሥራቅ አፍሪካ የሚታወቅ ትልቅ ባንክ ነው። ባንኩ በአሁኑ ወቅት በኬንያ፣ በኡጋንዳ፣ በታንዛኒያ እና በሩዋንዳ በስፋት እየሰራ ይገኛል። ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ያቀደውም የደቡብ አፍሪካው ኔድባንክ በውስጡ የከፍተኛ ድርሻ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ ነው።

ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረጓን ተከትሎ፣ የዚህ ባንክ መግባት በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ጥሩ ውድድር ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

@darashMedia
@darashMedia


💥➡️ዛሬ እጅግ በጣም ትልቅ የስራ እድል ቀርቦላችዋል

🤑በቀን ቢያንስ ከ 10ሺ ብር በላይ ልታተርፉበት የምችሉበት ብዙ ሰው ያልነቃበት ልዩ የonline ስራ መትላችዋል

⭐️ስራውን መጀመር የምትፈልጉ እና ስለስራው በቂ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ 👇በዚ 📎🔗

https://t.me/+6ASVmu9Q6Rk3YzNk

https://t.me/+6ASVmu9Q6Rk3YzNk ❗️❗️እዚ ቻናል ውስጥ ሙሉ መረጃው አለላችው ዛሬ ደግሞ ቻናሉ ውስጥ ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅታል🫳💵💵

@Eyuelofficial በዚም አናግራችው ዛሬውኑ ስራውን መጀመር ትችላላችው


ባለቤቶቹ አህዮቻቸውን እንዲወስዱ ጥሪ ቀረበ‼️
በራያ ኮረም በህወሓት ተወሰደው  የነበሩ አህዮችና ፈረሶች ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተደረገ‼️

በራያ ኦፍላ እና ኮረም አካባቢ በህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ተነጥቀው ተተኳሽ ለማጓጓዝ እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች/ተልዕኮዎች ይውሉ የነበሩ በርካታ አህዮች ፣በቅሎዎችና ፈረሶች በአሁኑ ወቅት በኮረም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዚህ መሠረት የእንስሳቱ ባለቤቶች ወደ ኮሌጁ በመሄድ እንስሳቶቻቸውን ለይተው እንዲወስዱ ይፋዊ ጥሪ ተላልፏል።

@darashMedia
@darashMedia


#መቀሌ
የመንግሥት ኃይሎች በሦስት አቅጣጫ
ወደ መቀለ እየተቃረቡ መሆኑ ተሰማ

የፌደራል መንግሥት ተባባሪ የሆኑት የትግራይ ሰላም ኃይል ሚሊሺያዎች፣ ከትግራይ ዋና ከተማ መቀለ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን «ሚላዛት» የተባለች ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታወቁ። ሮይተርስ ባሰራጨው የቪዲዮ መረጃም በከባድ መኪናዎች የተጫኑ ታጣቂዎች «መቀለ መቀለ» እያሉ ሲጮኹ መታየታቸውን ዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ትስስራቸውን ማቋረጣቸውን ተከትሎ ጦርነቱ አካባቢውን ያዳርሳል የሚለው ስጋት ከፍ ብሏል።

ባለፈው ሳምንት በተቀሰቀሰው ውጊያ የመንግሥት ጦር እና ተባባሪዎቹ በወሰዱት እርምጃ የትግራይ አማጽያን ከአጎራባች ክልል መውጣታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። እንደ መረጃ ምንጩ ገለጻ፣ የመንግሥት ኃይሎች በሦስት አቅጣጫ ወደ መቀለ የሚያደርጉት ግስጋሴ አሁንም ቀጥሏል።

@darashMedia
@darashMedia


ዜግነት 350ሺህ ዶላር ግዙኝ❗️

🇦🇷 በከፍተኛ የኢኮነሚ ጫና እና ግሽበት ውስጥ ያለችው አርጀንቲና ገንዘብ ካላችሁ ዜግነት እንኩ ብላለች።

🇦🇷 በተጨማሪነት የመንግስት  ቦንድ ግዢ 800 ሺህ ዶላር ማውጣት ያለባችሁ ሲሆን ፣ የትዳር አጋር ካላችሁ እና ዜጋ ትሁን ካላችሁ 100ሺህ ዶላር  ፣ ልጅ ኖርዋችሁም አርጀንትናዊ ይሁኑ ካላችሁ እድሚያቸው ከ18-25 ከሆኑ እና ካላገቡ 100ሺህ ዶላር ጨምራችሁ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ ትችላለችሁ ብላለች።

🇦🇷 አርጀንቲና እድሚያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ካላችሁም 25ሺህ ዶላር ትከፍላላችሁ ብላለች።

🇦🇷 ከ170 በላይ ሀገራት ያለ ቪዛ ወይም ኦን አራይቫል ቪዛ የመጓዝ እድልም አላችሁ ብላለች።

🇦🇷 በሁሉም የላቲን አሜሪካ ሀገራት የመንቀሳቀስ የመስራት እና የመኖርም መብት ይሰጣል የአርጀንቲና ዜግነት። 

🇦🇷 በዚህ ዓመት እስከ 35 በመቶ የዋጋ ግሽበት እና ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ውስጥ የገባችው አርጀንቲና የገጠማትን የዶላር እጥረት ለመቅረፍ ፣ ከሀገራችሁ የገንዘቡን ምንጭ እና የፖሊስ ክሪላንስ ካመጣችሁ ዜጋዬ ብዬ እቀበላችኋለሁ ብላለች።

@darashMedia
@darashMedia


የህወሃት ታጣቂዎች እነ ጄኔራል ታደሰ
ወረደ ያሉበትን ሆቴል ከበዋል ተባለ

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች በህወሃት  ታጣቂዎች መከበባቸው ተሰማ።

የ«አውራምባ ታይምስ» ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እንደገለጸው፣ የህወሃት የጸጥታ ሃላፊዎች የቀድሞዎቹን አመራሮች «ወደ ኤርትራ እንወስዳችኋለን» በማለት አሁን ላይ ታስረው የሚገኙበትን HZ ሆቴል ከበውታል። ይሁን እንጂ ታሳሪዎቹ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ «አንሄድም!» እያሉ መሆናቸውን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አስታውቋል።

@darashMedia
@darashMedia


አቶ አብዱላሂ አደን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በመሆን ተሾሙ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አቶ አብዱላሂ አደን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

ላለፉት ዓመታት በከንቲባነት ያገለገሉት አቶ ከድር ጁሃር በአቶ አብዱላሂ አደን ተተክተዋል።

@darashMedia
@darashMedia

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.