የግጥም ውድድር
“በእዝነት ጥላ ስር” በሚል መርህ በተዘጋጀው የ1446/2017 የነሲሓ ኮንፈረንስ ላይ የሚቀርብ በአይነቱ ለየት ያለ የግጥም ውድድር ላይ ይሳተፋ!!!
➢ ርዕስ ፡“ለአለማት እዝነት ” በሚል የረሱል (ሱለሏህ አለይሂ ወሰለምን) ስብዕና እና ተልዕኮ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ተያያዥ ርዕሶች ዙርያ በማዘጋጀት ውድድሩ ላይ መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል (አላህ ነብያችንን መላኩ የራህመቱ መገለጫ መሆኑን፣ ለኡመታቸው መስተካከል ያላቸው ጉጉትና ርህራሄ ፣ ስነምግባራቸው ፣ ወደ ፊት ላላዩቸው ኡመቶቻቸው ያላቸው ውዴታና እዝነታቸው፣ በእኛ ላይ የሳቸው ሀቅ እና እሳቸውን መቃረን ያለው አደጋ)
👉🏻 ርዝመት ፡ ከ30 እስከ 40 ስንኝ ያልበለጠ
👉🏻 ቋንቋ ፡ አማርኛ
👉🏻 ውድድሩ የሚጀመርበት ቀን ጥር/20/2017
👉🏻 ውድድሩ የሚያበቃበት ቀን ጥር/30/2017
የተመረጡ ተወዳዳሪ የግጥም አቅራቢዎች በቅድሚያ በማዕከሉ ዋና ቢሮ በሚደረጉ የማጣሪያ ፕሮግራሞች ላይ በአካል በመቅረብ የሚለዩ ሲሆን አሸናፊዎች የካቲት 16/2017 በሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄደው የነሲሃ ኮንፈረንስ ላይ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።
ሽልማት
1. 50,000ብር
2. 30,000ብር
3. 20,000ብር
ማሳሰቢያ
➢ ተወዳዳሪዎች በ0972757575 የቴሌግራም አድራሻ ብቻ ስማቸውንና ስልክ
ቁጥራቸውን በማካተት ግጥማቸውን በጹሁፍ እና ለወንዶች በድምጽ መላክ አለባቸዉ፡፡
➢ ለተጨማሪ ማብራሪያ 0972757575 መደወል ይችላሉ።
ነሲሓ ቲቪ / Nesiha Tv
T.me/dawudyassin