ማኅበረ ቅዱስ ገብርኤል dan repost
🕊
[ ✞ እንኩዋን "ለተአምረ እግዝእትነ ማርያም": "ቅዱስ ደቅስዮስ": "ቅዱስ አንሰጣስዮስ" እና "ቅዱስ ገብርኤል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
---------------------------------------------
🕊 † ተአምረ ማርያም † 🕊
- "ተአምር" የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ [በላይ] : ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ [ሲፈጸም] ተአምር ይባላል::
- ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው "ኤልሻዳይ - ከሐሌ ኩሉ - ሁሉን ቻይ" እያልን የምንጠራው::
- እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ [ኦሪትን ተመልከት] እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ [፩ ነገሥት] እንደ ነበር ይታወቃል::
- እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: [ማቴ.፲፥፰, ፲፯፥፳, ማር.፲፮፥፲፯, ሉቃ.፲፥፲፯, ዮሐ.፲፬፥፲፪]
- እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: [ሐዋ.፫፥፮, ፭፥፩, ፭፥፲፪, ፰፥፮, ፱፥፴፫-፵፫, ፲፬፥፰, ፲፱፥፲፩]
- በተአምራት ብዛት ደግሞ ከጌታ ቀጥላ ድንግል እመ ብርሃን ትጠቀሳለች:: ዛሬም የምናስበው የእርሷን ተአምራት ነው::
- የእግዝእትነ ማርያም ሙሉ ሕይወቷ ተአምር ነው:: አበው:- "ድንግል ተአምራት ማድረግ የጀመረችው ገና ሳትወለድ ነው" ሲሉ የሚጸንባቸው ሰዎች አሉ:: ከአዳም ውድቀት በሁዋላ በእርሷ እንደሚድን "ሴቲቱ" [ዘፍ.፫፥፲፭] በሚል ከተነገረው በሁዋላ ድንግል በብዙ ተአምራት [በምሳሌ] ተገልጣለች::
- ለአብነት ያህልም እግዚአብሔር ኖኅን ከጥፋት ውሃ እንዲሁ ማዳን ሲችል ተአምራቱን በመርከብ ገለጠ:: [ዘፍ.፯፥፩] ለሚያስተውለው ያቺ መርከብ ናት ድንግል::
- አብርሃም ይስሐቅን ሊሰዋ ሲል በተአምራት በግ በእፀ ሳቤቅ ተይዞ ተገኝቷል:: [ዘፍ.፳፪፥፲፫] ያዕቆብ በቤቴል ድንቅ መሰላልን ተመልክቷል:: [ዘፍ.፳፰፥፲፪] ሙሴ በጽላቱ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: [ዘጸ.፴፬፥፳፱, ዘሌ.፲፥፩]
- የአሮን በትር ስትለመልም ድንቅ ተአምራቱ እመቤታችንን ያሳያል:: ኢሳይያስ የድንግልን መጽነስ "ምልክት [ተአምር] ይሰጣቹሃል" ሲል ገልጾታል:: [ኢሳ.፯፥፲፬]
- በሐዲስ ኪዳንም የድንግል :-
- ያለ በደል መጸነሷ:
- ንጽሕት ሆና መወለዷ:
- በቤተ መቅደስ ለ፲፪ ዓመታት ምድራዊ ምግብን አለመመገቧ:
- ያለ ወንድ ዘር መጸነሷ [ሉቃ.፩፥፳፮] :
- ያለ ምጥ መውለዷና
- በልደት ዕለት የታዩ ተአምራት [ሉቃ.፪፥፩] :
- እናትም: ድንግልም መሆኗ [ሕዝ.፵፬፥፩] ሁሉ በራሱ ድንቅ ተአምር ነው::
- ከዚህ ባለፈም በቃና ዘገሊላ ያደረገችውን ዐይነ ልቡናው ከታወረበት ሰው ውጪ ዓለም ያውቃል:: [ዮሐ.፪፥፩] ባለ ራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ:-
- "ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ:: ፀሐይን ተጐናጽፋ: ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት: በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች" ብሎ የእመቤታችን መገለጥ [መታየት] በራሱ ተአምር መሆኑን ነግሮናል:: [ራዕይ.፲፪፥፩]
- ድንግል እመቤታችን በሕይወተ ሥጋ ከሠራችው ተአምራት በበዛ መንገድ ላለፉት ፪ሺ ዓመታት ስትሠራ ኑራለች:: እየሠራች ነው:: ገናም ትቀጥላለች:: ለሚያምናት ተአምራትን መሥራት ብቻ አይደለም: ነፍሱንም ከሲዖል ታድነዋለች::
- ሁሉን ቻይ ልጅ አላትና እርሷም ሁሉን ትችላለች:: እንኩዋን የፈጣሪ እናት ድንግል ማርያም የክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያቱም "የሚሳናችሁ የለም" ተብለዋል:: [ማቴ.፲፯፥፳]
🕊 † ቅዱስ ደቅስዮስ † 🕊
- ይህ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ በዘመነ ጻድቃን አካባቢ እንደ ነበረ ይታመናል:: ከምናኔ ሕይወቱ ባሻገር በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ የጥልጥልያ ሃገር ዻዻስም ነበር:: ይሕ ቅዱስ ሰው በእውነቱ ያስቀናል::
- እመቤታችንን ሲወዳት መንጋትና መምሸቱ እንኩዋ አይታወቀውም ነበር:: ፍቅሯ በደም ሥሮቹ ገብቶ በደስታ ያቃጥለው ነበርና ዘወትር እያመሰገናት አልጠግብ አለ:: የሚያስደስትበትን ነገር ሲያስብ ደግሞ የተአምሯ ነገር ትዝ አለው::
- ከዚያ በፊት የእመቤታችን ተአምሯ በየቦታው ይነገራል: ይጻፋል: ይሰበካል:: ግን በአንድ ጥራዝ አልተያዘም ነበርና በሱባኤ: በፈጣሪው እርዳታ: በፍጹም ድካም የእመ ብርሃንን ተአምራት ሰብስቦ በአንድ ጠረዘውና ለአገልግሎት ቀረበ::
- እርሷን ከመውደዱ የተነሳ ይህንን አድርጉዋልና እመ ብርሃን ወደ እርሱ ወረደች:: "ወዳጄ ደቅስዮስ ደስ አሰኘኸኝ" አለችው:: መጽሐፉንም ተቀብላው ባረከችው:: "አመሰግንሃለሁ" ብላውም ተሰወረችው::
- በዚህ ጊዜ ቅዱሱ ሐሴትን አደረገ:: [እመቤታችን ማየት እንዴት ያለ ሞገስ ይሆን!]
ቅዱስ ደቅስዮስ ግን ፍቅሯ እንደ እሳት ልቡን አቃጠለው:: አሁንም ደስ ሊያሰኛት ምክንያትን ይሻ ነበር::
- እመቤታችን ጌታን የጸነሰችበት በዓል [መጋቢት ፳፱] ሁሌም ዐቢይ ጦም ላይ እየዋለ ለማክበር አይመችም ነበርና ቅዱሱ ታሕሳስ ፳፪ ቀን ሊያከብረው ወሰነ:: በሃገሩ ያሉ ክርስቲያኖችን ጠርቶ ታላቅ በዓልን ለድንግል አከበረ::
- ሕዝቡም ጸጋ በዝቶላቸው ስለ እመቤታችን ታላቅ ሐሴትን አደረጉ:: በዚያች ሌሊትም እመ ብርሃን በሞገስ ወረደች:: "ወዳጄ ደቅስዮስ! ዛሬም ፍጹም ደስ አሰኘኸኝ! እኔም ስለ ክብርህ ይህንን አመጣሁልህ" ብላ ሰማያዊ ልብስና ዙፋን ሰጠችው::
- ማንም እንዳይቀመጥበት ነግራው: ባርካው ዐረገች:: ከዚህች ዕለት በሁዋላ ቅዱስ ደቅስዮስ ፈጣሪውንና ድንግል እናቱን ሲያገለግል: ተአምሯን ሲሰበስብ: ምዕመናንን ሲመራ ኑሮ በዚህች ዕለት ዐርፏል:: ከእርሱ በሁዋላ የተሾመው ዻዻስም በድፍረት በእርሱ ዙፋን ላይ በመቀመጡ መልአክ ቀስፎ ገሎታል::
- የእመቤታችንን ተአምር መስማትና ማንበብ ያለውን ዋጋ የሚያውቅ ጠላት ሰይጣን ግን ዛሬም ድረስ ባሳታቸው ሰዎች አድሮ ተአምሯን ይቃወማል:: " እኛ ግን ለእመቤታችን እንሰግዳለን!! ተአምሯንም እንሰማለን!! ጥቅማችን እናውቃለንና!! "
- ለመረጃ ያህልም :-
- የእመቤታችን ተአምር የሰበሰበ [ ቅዱስ ደቅስዮስ ]
- የተአምሯን ሥርዓት ያዘጋጁ [ ቅዱሳን አበው ማቴዎስ: ማርቆስና አብርሃም ሶርያዊ ]
- እሰግድ ለኪን የደረሰው [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ]
- የተአምሯን ሃሌታ [ ቅዱስ ያሬድ ]
- የዘወትሩን መቅድም [ ቅዱሳን ሊቃውንት ] ናቸው::
" ልመናዋ ክብሯ በእውነት ለዘለዓለሙ ይደርብን !! "
🕊 † ቅዱስ አንስጣስዮስ † 🕊
የግብጽ ፴፮ኛ ፓትርያርክ የሆነው ይህ አባት በ፮ኛው ክ/ዘ የተወለደ ሲሆን በትጋቱ: በትምሕርቱና በድርሰቱ ይታወቃል:: ምዕመናንን ለማስተማርም ከ፲፪ ሺህ በላይ ድርሰቶችን ደርሷል:: ብዙ መከራዎችን አሳል በ፯ኛው መቶ ክ/ዘ ዐርፏል::