ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው (John Climacus) "ትሕትና የራስህን በጎ ሥራዎች ከራስህ የሚሰውር መጋረጃ ነው'' ይላል:: ለብዙዎቻችን ትሕትና ማለት ራስን በሰዎች ፊት ዝቅ እያደረጉ ማውራት ፣ የሠራነውን በጎ ሥራ ለመደበቅ መሞከር ነው:: እርሱ ግን እንዲያውም ትዕቢት ነው:: በንግግርህ ራስህን ዝቅ ለማድረግ መሞክርህን እንደ ትሕትና ከቆጠርከው ራስህን የሆነ ተራራ ላይ አስቀምጠህ በሸለቆ ወዳሉት እያየህ ነውና ትዕቢት ነው:: በጎ ሥራህን ልታስተባብል መሞከርህም በልብህ ትልቅ ቦታ የሠጠኸው በጎ ሥራ አለኝ ብለህ እያሰብህ ነውና እርሱም ትዕቢት ነው:: ለዚህ ነው ዮሐንስ ዘሰዋስው "ትሕትና የራስህን ሥራ ከራስህ የሚሠውር መጋረጃ ነው'' ያለው:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርም "እንዳንተ ትሑት ለመሆን ምን እናድርግ?'' ብለው የጠየቁትን ሰዎች "እኔ እግዚአብሔርን ትሑት አድርገኝ ብዬ ስለምነው ዐሥር ዓመታት አለፈኝ:: እናንተ እንዳንተ እንሁን ትላላችሁ" ማለቱ የራሱ በጎነት ስለማይታየው እንጂ ይህንን አባባል ለዓለም ጥሎ ለማለፍ እየሞከረ አልነበረም:: ትሕትና በእርግጥ የልዑላነ ምግባር ሥራ እንጂ እኛ ኃጢአተኞች ራሳችንን ማወቅም በቂያችን ነው:: ኃጢአተኛ ሆኖ መታበይ ደግሞ ለሐኪም የሚያስቸግር በሽተኛነት ነው::
#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile
"አቤቱ፥ ልቤ አይታበይብኝ፥ ዓይኖቼም ከፍ ከፍ አይበሉብኝ" መዝ. 130:1
#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile