"፭ኛ ኮርስ "ነገረ ማርያም"
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
፩.፪, #የእመቤታችን_ታሪክ
በዚህ ርዕስ የምንመለከተው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዘር ሐረግ፣ ከማን ወገን እንደሆነች፣ እንዴት እንደተወለደች እና በቤተ መቅደስ የአስተዳደጓን ሁኔታ እንዲሁም ከቤተ መቅደስ በዘመኑ ከነበሩ ሽማግሌዎች መካከል በተለያየ አይነት ምልክት ተመርጦ አረጋዊ ዮሴፍ እመቤታችንን እንዲጠብቃት መሰጠቱና በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት ጌታን በሕቱም ድንግልና ፀንሳ በሕቱም ድንግልና መዉለዷ፣ ከጌታችን ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር መኖሯ ከጌታችን በኋላ ከሐዋርያት ጋር መኖሯ ብሎም ከዚህ ዓለም ድካም በ64 ዓመቷ በ49 ዓም ገደማ ማረፏ እና አይሁድ በክፋት ሥጋዋን ሊያቃጥሉ ሲመጡ በተደረገ ገቢር ታአምራት ወመንክራት የእመቤታችን ሥጋ መሰወሩ እና በሐዋርያት ጾም እና ጸሎት መገለጡ በስተመጨረሻም የእመቤታችን ትንሣኤ እና ዕርገት የሚነገርበት ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜ ከብዙ በጥቂቱ ለማሳያ ያህል ተገልጿል።
በአጠቃላይ በዚህ ርዕስ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታሪክ የምንማርበት ነው።
፩.፪.፩, #የእመቤታችን_የልደት_ታሪክ
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር”። (ኢሳ 1፥9)። ይህ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የተናገረው ቃል ምስጢር አዘል ሲሆን የተነገረውም ለወላዲተ አምላክ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነው።
ነቢዩ በመንፈስ ቅዱስ ተቀኝቶ እንደተናገረ ስለ አዳም ልጆች መዳን ያስቀራት ንፅሕት ዘር ማለትም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። በሌላም ሥፍራ ቅዱስ ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ነገር ሲገልፅ እንዲህ አለ። (መዝ 86፥1) “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን (መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው)።”
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት መሰረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ብሎ ከአዳም ጀምሮ እነ አብርሃምን፣ እነ ዳዊትን፣ እነ ሰልሞንን ወ.ዘ.ተ እስከ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ያሉትን በምስጢር ማንሳቱ ነው። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷን ታሪክ ከብዙ እንደሚከተለው እንመለከታለን።
የእመቤታችን የዘር ሐረግ ከአዳም ጀምሮ እስከ ኢያቄምና ሐና ድረስ በተቀደሱ አባቶችና እናቶች በኩል ልደቷ ሲወርድ እንደመጣ ሊቃውንተ ቤተ ከርስቲያን ይመሰክራሉ፡፡
➥ይህም ከአዳም ልጆች በሴት በኩል
➥ከኖኅ ልጆች በሴም በኩል
➥ከአብርሃም ልጆች በይስሐቅ በኩል
➥ከያዕቆብ ልጆች በይሁዳና በሌዊ በኩል
➥ከዳዊት ልጆች በሰሎሞን በኩል
በተመረጡና በተቀደሱ አባቶችና እናቶች በኩል በጥበብ እግዚአብሔር ስትወርድ ከመጣች በኋላ ከቤተ ሌዊ ከነገደ አሮን ከካህናቱ ወገን ከሆኑት ከቅድስት ሐናና ከነገደ ይሁዳ ከነገሥታቱ ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም እንደምትወለድ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበር፡፡
የቅድስት ድንግል ማርያምና የዮሴፍ ዝምድና ደግሞ፦ አላዛር ቅስራን እና ማትያስን ወለደ።
➥ቅስራ ኢያቄምን፣ ኢያቄም እመቤታችንን ወለደ።
➥ማትያስ ያዕቆብን፣ ያዕቆብ ዮውሴፍን ወለደ።
ዝምድናቸው እንዲህ ነው።
በነገው ክፍላችን ከዳዊት ልጅ ከሰለሞን የልጅ ልጆች ማለትም ከነ ጴጥርቃና ቴክታ ጀምረን የእመቤታችንን የትውልድ ተዋረድ እናያለን።
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->የእመቤታችን የዘር ሐረግ
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯