PULSE dan repost
የታሸገ ውሃ እና የፕላስቲክ ብክለት ስጋት
የፕላስቲክ ብክለት ዓለም አቀፍ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ጥምን ለመቁረጥ ለብዙዎቻችን ተመራጭ የሆነው የታሸገ ውሃ ግን በፕላስቲክ ብክለት ምክንያት ለጤና አስጊ ነገር ይኖረዋል ብለው አስበው ያውቃሉ?
በቅርቡ በአሜሪካ የሳይንስ አካዳሚ ያወጣው ጥናት በእያንዳንዱ ሊትር የታሸገ ውሃ ውስጥ ያለውን የፕላስቲክ ብናኝ መጠን በመለካት አስደንጋጭ መረጃ አውጥቷል። በአማካይ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ የማይክሮ ፕላስቲክ ብናኝ (Microplastic contaminations) አንዳላቸው አረጋግጧል።
በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች የፕላስቲች ብናኞችን ለመለካት የተጠቀሙበት መንገድ በጣም የተራቀቀ hyperspectral stimulated Raman scattering (SRS) የሚባል አውቶሜትድ መለያ ሲሆን በጣም ጥቃቅን የፕላስቲክ ብናኞችን ልቅም አድርጎ በቅንጣት ደረጃ መለየት የሚችል መመርመርያ መሳርያ ነው። ይህ መንገድ ከዚህ በፊት የታሸገ ውሃ ደህንነት ለመፈተሽ ከምንጠቀምባቸው የኬሚካል ምርመራዎች በእጅጉ ይልቃል። ይህን መመርመሪያ ዘዴ በመጠቀም የታሸጉ የዉሃ ናሙናዎች ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የፕላስቲክ ብናኝ ብክለት እንዳለው ታውቋል። በአማካይ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ የማይክሮ ፕላስቲክ ብናኝ አንዳላቸው አረጋግጧል።
ይህም ማለት እያንዳንዳችን ከእያንዳንዱ ሊትር የታሸገ ውሃ በአማካይ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ የማይክሮ ፕላስቲክ ብናኝ እንጠጣለን ማለት ነው። እነዚህ የፕላስቲክ ብናኞች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤና ስጋቶችን አስነስቷል። መርዛማ ናቸው ተብሎ ይታመናል።
ፕላስቲኮች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ በሁሉም ቦታ ተስፋፍተው እንደመገኘታቸው መጠን ይህን ተጋላጭነት ለመቀነስ ምን ማድረግ ይሻላልል ይላሉ? እስኪ ሃሳብዎትን እና የመፍትሄ አማራጮችን ያጋሩን።
ዋቢ
Qian et al. Rapid single-particle chemical imaging of nanoplastics by SRS microscopy. Proc. Natl. Acad. Sci. 2024; 121 (3) e2300582121. https://doi.org/10.1073/pnas.2300582121