Hulu media (ሁሉ ሚዲያ) dan repost
የ ' ቅጥር ደመወዝ ' አልበቃ ቢላት ፤ ፊቷን ወደ " ሊስትሮነት " ያዞረችው የምህድስና ምሩቋ ምንታምር በለጠ
" ስሜ ምንታምር በለጠ እባላለሁ።
በሊስቶር ስራ ነው የምተዳደረው አዲስ አበባ፤ ቦሌ አካባቢ ።
የተወለድኩት በአማራ ክልል ፣ ዳንግላ ከተማ ነው። ተወልጄ የተማርኩትም እዛው አካባቢ ነው።
እናት አባቶቼ አቅመ ደካማ ነበሩ። አሁን ላይ በህይወት የሉም ሁለቱም። እህቶች እና ወንድሞች አሉኝ።
ዩኒቨርሲቲ የገባሁት በ2007 ዓ/ም ነው በ2011 ዓ/ም በቴክስታይል ኢንጂነሪንግ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቄያለሁ።
ከተመረቅኩ በኃላ ስራ ፍለጋ ነበር የወጣሁት ፤ ስራ ቶሎ ማግኘት ከባድ ስለነበር ወደ ሐዋሳ ነው የሄድኩት።
ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገባሁ፤ በ2500 ብር ደመወዝ ስራ ጀመርኩ የስራ ድርሻዬ የጥራት ደረጃ ማስጠበቅ ቁጥጥር ነበር እሰራበት የነበረው ጨርቃ ጨርቅ ነው፣ ጋርመት ቲሸርቶች ሱሪ ይሰራል እሱ ላይ ጥራት መቆጣጠር ነበር የኔ ስራ።
እዚያ ሁለት ዓመት ሰራሁ ፤ ከዛ በጦርነቱም በ #AGOA / አጎዋ ምክንያት እየቀነሱ ነበር ድርጅቶቹ ሰራተኞችን ፤ ከእሱ ወጥቼ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።
አዲስ አበባ መጥቼ እንደጠበኩት ስራ አላገኘኹም። እየፈለኩኝ ነበር አንዳንድ ቦታዎችም ገብቻለሁ ፤ ደሞዝ የማይሰጥ ድርጅትም አጋጥሞኝ ያውቃል፤ ብዙ ተግዳሮቶችን አሳልፌያለሁ።
ሰው ቤት በተመላላሽነት ምግብ መስራትም ጀምሬ ነበር መጨረሻ ላይ ሊስትሮ / ጫማ ማስዋብ ጀመርኩ።
ዲግሪ ይዣለሁ ፤ ያሳፍራል ዲግሪ ጥቅም የለውም፤ በዲግሪ ስራ ማግኘት አልቻልኩም። ባገኝም ህይወቴን Survive የማያደርግ ፣ የቤት ኪራይ የማይከፍል ፣ ቤተሰብ የማያስተዳድር ፣ ህይወቴን የማይቀይር ደመወዝ ነው ያለው።
ቤተሰብ መርዳት ቀርቶ እራስን መቀየሪያ የለም ፤ እኔ ዩኒቨርሲቲ ስማር የገዛሁትን ልብስ ነው እስካሁን የምለብሰው ፤ ምናልባት ይሄን ሊስትሮ ከሰራሁ በኃላ ልገዛ እችላለሁ።
ከጥዋቱ 11:30 ከቤቴ እወጣለሁ ፤ ታክሲ ይዤ እዚህ ስራ ቦታዬ ላይ 12:30 ደርሳለሁ ፤ ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:40 ድረስ ስራ ቦታዬ ላይ እገኛለሁ።
ደስ ብሎኝ ነው የምሰራው፤ የራሴ መመሪያ አለኝ ፤ በጥዋት ተነስቼ መጥቼ እሰራለሁ፤ ለኔ መስሪያ ቤቴ ድርጅቴ ነው።
ወጣቱ ተስፋ መቁረጥ የለበትም ፤ ያኔ ተስፋ ቆርጬ እራሴን አልጎዳሁም አማራጭ ሳጣ ወደ ሊስትሮ ዝቅ ብዬ መስራት እንዳለብኝ አእምሮዬ ነገረኝ ፤ ይህንን በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።
ይሄን ወጥሬ ስለምሰራ እራሴን ለመቀየረ፣ ወደዓላማዬ ፣ ወደ መንገዴ ያስገባኛል።
ከዚህ በኃላ የተሻለ ነገር መስራት አስባለሁ። ከዚህ ቀጥሎ ከሞያዬ ጋር ስለሚያያዝ ወደ ፋሽን ፣ ጋርመንት ፣ ስፌት ሞያ ሰልጥኜ ፣ ትንሽዬ ማሽንም ይሁን ገዝቼ ወደዛ የማዘንበል እቅድ አለንኝ። "
BBC AMHARIC
-----------------------
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏
👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
t.me/emsmereja