የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ግጭት ተሳትፈዋል ብላ አሜሪካ እንደምታስብ ሮይተርስ ከአንድ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣን እና ከ5 የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዲፕሎማቶች ሰምቻለሁ በማለት ዘግቧል።ኤርትራ ጦሯን ስለማስገባቷ የአሜሪካ መንግሥት ግንዛቤ ያገኘው፣ ከሳተላይት ምስሎች፣ ከተጠለፉ የመልዕክት ልውውጦች እና ከትግራይ ክልል ከሚወጡ ሪፖርቶች እንደሆነ ዘገባው ገልጧል።የአሜሪካ መንግሥት እዚህ ድምዳሜ ላይ ስለመድረሱ ግን፣ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ማረጋገጫ አለመስጠቱን ዘገባው አመልክቷል።የኤርትራ ወታደሮች በዛላንበሳ፣ ራማ እና ባድመ ከተሞች በኩል እንደገቡ ከምንጮች መስማቱን የገለጠው ዜና ወኪሉ፣ የወታደሮቹ ብዛት እና በጦርነቱ ስላላቸው ሚና ግን መረጃ እንዳልተገኘ አክሏል።ብሉምበርግም ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ፣ የኤርትራ ወታደሮች መቀሌ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች መታየታቸውን ዘግቧል።
[Reuters/Wazema]
@ebs_official @ebs_official
[Reuters/Wazema]
@ebs_official @ebs_official