ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


#education #education_Minstry #ትምህርት_ሚኒስቴር #ትምህርት
Buy ads: https://telega.io/c/education_Minstry_ET

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


🎓#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

🟡የምዝገባ ቦታ፦

🟡 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
🟡 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግብርና ኮሌጅ እና በቬተርናሪ ሕክምና ኮሌጅ

🟡ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

🟡 የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
🟡 የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
🟡 አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
🟡 የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ልብስ

ወደ ተቋሙ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በሌላ ማስታወቂያ ወደፊት ይገለጻል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


🔻በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


⚪️#WoldiaUniversity

በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


🔖የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2019 ትምህርት ዘመን በሕክምና ዲግሪ ፕሮግራም (Doctor of Medicine) አመልካቾችን እየተቀበለ ነው።

ኮሌጁ በሁለት አማራጮች ማለትም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ (Generic) እንዲሁም በአዲስ ኢኖቬቲቭ የሕክምና ትምህርት ኢኒሼቲቭ (NIMEI) አመልካቾች በመቀበል ላይ ይገኛል።

ያሉ ክፍት ቦታዎች ➡️ 80
በመንግሥት ስፖንሰር ➡️ 40
በግል ስፖንሰር ➡️ 40

✅የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇
መስከረም 22/2019 ዓ.ም ምሽት 12:00

✅ኦንላይን ያመልክቱ 👇
https://sis.y12hmc.edu.et/pages/admission

የፅሑፍ ፈተና መስከረም 27/2019 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን የቃል ፈተና ጥቅምት 01/2019 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

(ማመልከት የሚቻለው በኦንላይን ብቻ ነው። ለማመልከት የሚያግዝ ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


🟡የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና መመዝገቢያ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።

የኦንላይን መመዝገቢያ ቁጥር እና የይለፍ ኮድ በመግቢያ ፈተና ወቅት በተሰጣችሁ ኢሜይል የተለካላችሁ መሆኑ ተገልጿል።

የተመደባችሁበትን የማደሪያ ህንጻ ቁጥር እና የዶርም ቁጥር estudent.astu.edu.et ላይ በመግባትና የተሰጣችሁን Username እና Password በመጠቀም መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


🚀 TRADE YOUR WAY WITH BRAVE TRADE PRO

📈 Crypto CFDs. Global markets. One platform.
₿ Bitcoin • Ethereum • 100+ Crypto CFDs
🤖 Optional Trained Trading Engine
🎁 $100 Bonus to get started
👥 Refer a friend — earn $25 each when eligible.

🔥 Want market updates, trading ideas & Brave Trade news?
👉 Join our Telegram: https://t.me/BraveTP

🌐 Trade with Brave Trade Pro: https://tglink.io/b7d5be9096be56

⚠️ CFDs are complex leveraged products and carry a high risk of losing money.

#BraveTradePro #CFDTrading #CryptoTrading #Trading #Forex #Bitcoin #Ethereum #TradingCommunity


⚠️#AASTU

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ለቅድመ-ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ያመለከታችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ነገ መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ አዲሱ ዲጂታል ላይብራሪ ህንጻ ቁ. 46 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ከላይ በተያያዘው ምስል ዝርዝር ውስጥ ስማችሁ ያልተጠቀሰ አመልካቾች ያለመግቢያ ፈተና የምትመዘገቡ መሆኑን ተገልጿል።

ለፈተና የምትቀርቡ አመልካቾች ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ምንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደመፍተኛ ክፍል ይዞ መግባት እንደማይቻል ተመላክቷል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
▶️ https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
▶️ https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


🟡የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን አጠናቀው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራም (Extension) መመዝገብ እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


#ASTU በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ እና ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ገለፃ (Orientation) መስከረም 22/2019 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን፣ በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን መስከረም 22/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ ትምህርት መስከረም 25/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

ℹ️አዲስ ገቢ ተማሪዎች ልትይዟቸው የሚገቡ፦

🟡 የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
🟡 የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
🟡 ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
🟡 አራት ፖስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
🟡 አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


#AASTU በ2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ℹ️ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

🟡 ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፣
🟡 የ8ኛ ክፍል የውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
🟡 ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
🟡 የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
🟡 አራት 3×4 ፎቶግራፍ።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


#MoE የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7-11/2019 ዓ.ም ድረስ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇
https://student.ethernet.edu.et/preferences
 
💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


#MoH

ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ከዛሬ መስከረም 06/2019 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት እንደምትችሉ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁ. 952 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

🔔 ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከነገ መስከረም 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፈቃዳችሁን 12ኛ ክፍል በጨረሳችሁበት ክልል ማውጣት ትችላላችሁ።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


#ተጨማሪ

በትምህርት ሚኒስቴር የተደረገው ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ምንን መሠረት አድርጓል?

ምደባው የተደረገባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች

🟡 የተማሪዎች ውጤትና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ
🟡 የዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም
🟡 የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የት/ቤት ስርጭት
🟡 የሴት እና የወንድ ተማሪዎች የፆታ ስብጥር
🟡 የዓይነ ስውራን እና የመስማት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች

70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።

30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉ ተገልጿል።

500 እና ከዚያ በላይ አጠቃላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው ተመድበዋል።

ይህም ተማሪዎቹ ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ዕውቅና ለመስጠት እና ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማበረታታት የተደረገ ነው ተብሏል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


🟡ምደባ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የዞን እና የትምህርት ቤት ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተጨማሪም ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው መመደባቸውን አስታውቋል።

ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል።

🟡ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን  ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ባቀረቡ ቅሬታ መሰረት በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ተወሰነ።

ትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በክልሉ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው ለቅሬታቸው መፍትሔ ለመጠየቅ በትምህርት ሚኒስቴር ግቢ ከተገኙ ተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት፣ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ደህንነታቸው ወደሚጠበቅባቸው ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም፣ ወጣቶች በአሁኑ ወቅት ማተኮር ያለባቸው በትምህርታቸው ላይ በመሆኑና ወደፊት ሀገራቸውን የሚረከቡ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል።

ሀገር ማጽናት የሚቻለው የዛሬው ትውልድ ለነገው ትውልድ ማሰብ ሲጀምር ነው ያሉት ሚኒስትሩ ጦርነትና ግጭትን በመሸሽ ከትግራይ ክልል የወጡ ተማሪዎች በሰላም የመኖርና የመማር መብት ያላቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመሆኑም እነዚህን የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች በተለያየ መንገድ ማስተናገድና ትምህርታቸውን ያለመስተጓጎል እንዲቀጥሉ ማድረግ ተገቢ መሆኑን
ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

በዚህም ተማሪዎች ለምዝገባ በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባቸው ከዛሬ ማታ ጀምሮ ይፋ በሚደረገው የበየነ መረብ (Online) መተግበሪያ በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

በምዝገባው ወቅትም ተማሪዎች ከዚህ በፊት ይማሩበት የነበረውን ዩኒቨርስቲ፣ የትምህርት ዘመናቸውን እና የሚማሩበትን የትምህርት መርሐ ግብር (field of study) በመግለጽ ባሉበት ቦታ ሆነው የዝውውር ፎርሙን በአጭር ግዜ እንዲሞሉ አሳስበዋል።

ዛሬ በአካል በትምህርት ሚኒስቴር ግቢ የተገኙት በርካታ ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወትን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከላይ የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።


🟡#AASTU

በ2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ያመለከቱና የመግቢያ ፈተና የወሰዱ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የቅበላ የመቁረጫ ነጥብ በዩኒቨርሲቲው ይፋ ሆኗል።

ለኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች
➡️ አማካይ ውጤት 69.50 እና ከዚያ በላይ

ለአፕላይድ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች
➡️ አማካይ ውጤት 48.00 እና ከዚያ በላይ

ይህ የመቁረጫ ነጥብ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ለመረጡ ብቻ የሚሠራ ነው፡፡

🟡ውጤት ለመመልከት 👇
https://www.aastu.edu.et/result/

የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እና ሌሎች መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚገልፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


🟡#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ትምህርት ዘመን ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም ለመልሶ ቅበላ ብቁ የሆናችሁ ተማሪዎች የመግቢያ፣ የምዝገባ እና የትምህርት መጀመሪያ መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

➡️ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን 👇
ሰኞ መስከረም 11/2019 ዓ.ም

➡️የትምህርት ክፍል ምርጫ 👇
መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም (የ1ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች)

➡️የምዝገባ ቀናት 👇
መስከረም 12 እና 13/2019 ዓ.ም

➡️ትምህርት የሚጀምርበት ቀን 👇
ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም.

በመሆኑም ነባር ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሳችሁ በሚገኙ የሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል በመገኘት የምዝገባ ሂደታችሁን እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET


ተራዝሟል!

በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ እስከ መስከረም 05/2019 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ስለሆነም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ምርጫችሁን ያላስገባችሁ ተማሪዎች በተራዘመው የጊዜ ገደብ ውስጥ https://student.ethernet.edu.et  ላይ በመግባትና የፋይዳ መለያ ቁጥራችሁን በመጠቀም ምርጫችሁን እንድታጠናቅቁ አሳስቧል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
@education_Minstry_ET
@education_Minstry_ET

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.