መዝሙር ሠርዐ ሰንበተ
አመ ፳ወ፭ ለሰኔ በአተ ክረምት መዝሙር
(በ፭/ሴ) ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ለእለ በሰማይ ወለእለ በምድር ለእለ በባሕር ወለእለ በየብስ (ሠ) ለአበዊነ ለነቢያት ወለሐዋርያት (ሠ) ለጳጳሳት ወለቀሳውስት ለዲያቆናት ወለመነኮሳት (ሠ) ለጻድቃን ወለኃጥአን ለሙታን ወለሕያዋን ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ሰንበቱሰ ለክርስቶስ ይእቲ ወማኅደረ ስሙ ለልዑል።
ትርጕም፦
ለሰው ዕረፍት ሰንበትን ሠራ፤ በሰማይናበምድር በባሕርና በየብስ ላሉት ሁሉ። ለአባቶቻችን ለነቢያትና ለሐዋርያት፤ ለጳጳሳትና ለቀሳውስት ለዲያቆናትና ለመነኮሳት፤ ለጻድቃንና ለኃጥአን ለሙታንና ለሕያዋን፤ ለሰው ዕረፍት ትሆን ዘንድ ሰንበትን ሠራ ይህች የክርስቶስ ሰንበት ናት የልዑል የስሙ መጠሪያም ናት።
የዕለቱ ምንባባት፦
ዕብ ፮፥፯ – ፲፫፤
ይሁዳ ፩፥፩ – ፮፤
ግብ ፲፬፥፲፮ – ፍጻሜ፤
ወንጌል፦ ዮሐ ፲፬፥፲፰ –፳፯፤
ቅዳሴ፦ ዘሐዋርያት
የዕለቱ ምስባክ፦
ወአንተ ገበርከ አድባረ ምድር ኵሎ፤
ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ፤
ወተዘከር ዘንተ ተግባረከ። መዝ ፸፫፥፲፯፤
ትርጒም፦
አንተ የምድር ዳርቻዎችን ሁሉ ሠራህ፤
በጋና ክረምትን አንተ አደረግህ፤
ይህን ፍጥረትህን አስብ።
ምሥጢር፦
(አድባረ) ተራራውን ኮረብታውን
(ወምድረ) ደልዳላውን መሬት የፈጠርህ አንተ ነህ።
ዘጠኝ ወር በጋን ሦስት ወር ክረምትን የፈጠርህ (የሠራህ) አንተ ነህ
ይህን ያደረግህለትህን ፍጥረትህን አስብ አስበህ አውጣን።
ቦ አድባረ ወምድረ - ሙሴ አሮንን ሰባ ሊቃናትን ያስነሣህ አንተ ነህ፤
ክረምተ ወሐጋየ - ዘመነ ኤልያስን ያመጣህ አንተ ነህ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ድርቅ ሆኗልና።
ቦ አድባረ ወምድረ - ልዑላኑን ትሑታኑን የፈጠርህ አንተ ነህ።
ክረምተ ወሐጋየ፦ ተማርከው ሲሄዱ የሚጠጡት አጥተው ማድጋቸውን እያንኳኩ ወርደዋል በሚጠት ጊዜ ዝናም እየዘነመላቸው በየወንዙ ውኃ ሞልቶላቸው እየጠጡ ወጥተዋልና።
ቦ አድባረ ወምድረ - ሐዋርያትን ሰባ አርድእትን ያስነሣህ አንተ ነህ።
ክረምተ ወሐጋየ - ኦሪትን ወንጌልን የሠራህ። በክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ እንዳይገኝ በኦሪትም ተስፋ እንጂ ሀብት ሥርየት አልተሰጠምና። በበጋ ፍሬ እንዲገኝ በወንጌል ሀብት ሥርየት ተገኝቷልና።