"ከአባቱ ሳይወጣ መጣ፣ ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ። ከሦስትነቱ ሳይለይ መጣ፣ ከአንድነቱም ሳይለይ ወረደ። ከዙፋኑ ሳይለይ በሥጋ ልጅ አደረ። ምላቱ ሳይወሰን በማኅፀን ተጸነሰ፣ በላይ ሳይጎድል በማኅፀን ተወሰነ፤ በታችም ሳይጨመርበት ተወለደ። ከኃጢአት በቀር ፈጽሞ ሰው ሆነ። እንደ እግዚአብሔር እየሠራ እንደ ባርያ ታዬ። ወንጌሉን ያስተማሩ እንደመሰከሩ። ከአባቱ ዘንድ ተመሰገነ፣ ከራሱም ከበረ። የጌትነቱም ምስጋና በሰማይና በምድር መላ። እኛም እንግዲህ በልቡናችንዘወትር አናርፍም። ቅዱስ እያልንም የጌትነቱን ምስጋና እንናገራለን።"
/ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ/
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን አደረሳችሁ።
በግርግም ተወልዶ የእኛን ራቁትነት ያራቀ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በትልቅ መከራ እና ችግር ውስጥ ያለችውን ሀገራችንን ከመከራ እና ከችግር አላቅቆ የምሕረት እና የይቅርታ ልብስ ያልብስልን።
ለመላው የክርስትና እመነት ተከታይ በሀገር ውስጥም በውጪም ላላችሁ መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላችሁ ምርጡና ተወዳጁ ቻናላችን መልዕክቱን ያስተላልፋል።
በዚው አጋጣሚ የቻናላችን ፯ተኛ አመቱ ነው ለዚህ ያደረሰን የድንግል ማርያም ልጅ ይክበር ይመስገን።
ሠናይ በዓል
✟እንዘምር✟