ሱፊያ ተሳዳቢ አደለም
____
"ወሀብያ እያላችሁ ሱፊያን አታሰድቡ ፣ ሱፊያ ከስድብ የጠራ ፣ ሰዎችን በጥሩ ስነ-ምግባር የሚጣራ ነው
እንጂ ወሀብያ እያለ ሚሳደብ አደለም " ፣ የድምፅ ብክለት እንዳላስከትል የት ሄጄ ልሳቅ 😁😁😁
ይህ አባበል ለታክሲ ጥቅስነት ከተፈለገ አሪፍ ነው ፣ ከዛ ውጪ ግን በውስጡ የያዘዉ ምንም አይነት ሀቂቃ (እዉነታ)የለውም።
ሲጀመር “ ወሀቢያ “ ማለት ስድብ ነው ያለው ማነው ?? እነርሱ በስማቸዉ አፍረው ስድብ ነው ሲሉ ሰምተህ እኛ ጋር መጥተህ ማቀርሸት ትንሽ አይከብድም ⁉️
ታላቁ ሱፊይ ሁጀቱል ኢስላም ኢማም አል- ገዛሊ ረሂመሁላህ በተሰውፍ የዒልም ዘርፍ አቻ ያልተገኘለትን ና من لم يقرأ الإحياء فليس من الأحياء ) ኢህያእ ኪታብን ያላነበበ ህይወት እንዳለው አይቆጠርም ) የተባለለት የኢህያእ አል- ዑሉሙዲን ኪታብ አዘጋጅ ቢሆኑም የጥመት አንጃዎች ላይ ምላሽ ከመስጠና እነርሱን ከማጋለጥ አላገዳቸዉም ።
ለምሳሌ ያክል :-
አንደኛ : ኢልጃም አል-ዐዋም ላይ ሙተሻቢህ አንቀፆችን ብትንትን አድርገው አብራርተዋቸዋል ፣ አሏህ ሱብሀነሁ ወተዐላ ከክፍለ አካላት የተዋቀረ ( ሙረከብ ) ነው ብሎ የሚያምን ሰው በኢጅማዕ ካፊር እንደሆነ አስቀምጠዋል።
ሁለተኛ :
ተሀፋት አል-ፈላሲፋህ ወይም "የፈላስፎች ውድቀት" በሚለው የተወሰኑ መሰረታዊ የዐቂዳ ነጥቦችን የተቃረኑ ሙስሊም ፈላስፎችን አክፍረዋል
ሶስተኛ :
አል ቂስጣሱል ሙስተቂም የተሰኘ ለባጢኒያዎች ምላሽ የሆነ ኪታብ ፅፈዋል ፣ ከዚህም በተጨማሪ ኢህያእ ዑሉሙዲንን ጨምሮ ብዙ ኪታቦቻቸው ላይ የተለያዩ ፊርቃዎች ለሚያነሷቸው ከንቱ አስተሳሰቦች መልስ ሰጥተዋል ።
ኢማም ዒዝ ቢን አብዱሰላም ከሀዲስ ልሂቁ ከኢማም ኢብኑ ሰላህ ጋር ትልቅ ትንቅንቅ ውስጥ ገብተው የነበሩት “ ድንበር አላፊ ሀናቢላዎችን ዝም"እንበል በሚለው ፈትዋቸው ነበር። ዒዝ ቢን አብዱስሰላም ዝም ማለት የለብንም ብለው ብእራቸውን ካነሱ ዑለሞች መካከል ነበሩ ።
🚯መራር እውነታ ቢሆንም
የኛ ሀገር የታላላቅ አሊም ልጆች በቲንሹ አንዱ ወሀብያ ነው ፣
ስም እየጠቀስኩ እገሌ እገሌ ማለት እችላለሁ ግን ጥቅም የለውም። አንተ ዝም ብትል ልጆችህ ላይ የሚሰራ ፣ በብዙ ነገር የተደራጀ ፣ ታላቅ የሆነ ሚዲያ የገነባ ፣ከላይ እስከታች በሀብታም ሀገሮች የሚደገፍ፣ውሸት በመቅጠፍና በፕሮፓጋንዳ የሚስተካከለው የሌለ እንደው እንደ ስድብ አትቁጠሩብኝ እንጂ ዱርዬ የሆነ የባጢል ጭፍራ አለ።
ይህን ቡድን በሀላጅና በኢብኑ አረቢ እንዲሁም በሩሚ አለፍ ሲል ደግሞ በመጅኑኑ ለይላ ቂሷ ፣ በመንዙማ እቋቋመዋለሁ አሸንፈዋለሁም ካልክ ቀጥልበት ፣ ይህ አካሄድ ባለፋት ሰላሳ አመታት ሱፊያውን ማህበረሰብ ምን ያክል ዋጋ እንዳስከፈለው ግን አትርሳ ፡ ከገሀዱ አለም በላይ ትክክለኛ ፈራጅ የለምና ።
በሀቅና ባባጢል መሀከል በሚደረግ ጦርነት ላይ ሰበብ ሳታደርስ ከራማ ብቻ የምትፈልግ ከሆነ የበድር ጦርነት ፣የኡሁድ ጦርነት ፣ሂጅራና ሌሎችም ከፍተኛ ትግሎች ጥቅም ከንቱ ነበሩ ማለት ነውን ⁉️ የሙእጂዛ ባለቤት የሆኑት ፣ እጃቸውን ቢያነሱ ዱዐቸው የማይመለሰው ውዱ ነቢያችን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ይህን ያክል ከለፋ ፡ ቀሳሱል ከራማ ( ቁጭ ብለው የወልዮችን ከራማ የሚተርኩ ) ምን ያክል መልፋት እንዳለባቸው ማሰብ አይከብድም።
🚯በጣም የሚያስቀኝ ነገር ቢኖር ሌሎች ጋር የአቂዳ ኡስታዛቸዉን ፡” የአቂዳ አንበሳ “ ፣ “ የእነ እገሌ ራስ ምታት “ ፣ የእነ እገሌ ውጋት 😁😁ወዘተ በሚል ስም ይጠራሉ ።
እኛ ጋር ደግሞ ባለችህ አቅም የባጢል ባለቤቶችን ስትታጋል የማይወጣልህ ስም የለም ፡ በቅርቡ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው የቲቪ ጣቢያ “ ኡስታዝ ኢሳን “ ማቅረብ ፈልገው ነገር ግን ከወሀብያ ጋር ሰለሚመላለስ ማቅረብ እንደማይፈልጉና እራሳቸውን ማስበላት እንደማይፈልጉ ነገሩኝ።
ይህ የድድብና ጥግ ነው ምንም ሳይከፈለው፣ እራሱን አደጋ ላይ ጥሎ ለዲኑ አንዳች ነገር ላበርክት ያለን ሰው በዚህ ልክ መንካት ከሞራልም ከዲንም አንፃር የተወገዘ ነው።ደግሞ እነዚሁ ሰዎች መልሰው የሆነ ወሀብያ እንዲህ አለኝ ብለው ኡስታዝ ኢሳ ጋር መደወላቸው ገርሞ ይገርማል።
✍ዘ.ሐ