ከጥቅምት ወር 2017 ዓ፣ም ጀምሮ ተግባራዊ ይኾናል ተብሎ የነበረው የመንግሥት ሠራተኞች የደምወዝ ጭማሪ ከተያዘው ታኅሳስ ወር ጀምሮ እንደሚከፈል ዋዜማ ሰምታለች።
የዘገየው የጥቅምትና የኅዳር ወራት ደመወዝ በታኅሳስ ወር ደምወዝ ላይ ተጨምሮ ለሠራተኞች እንደሚከፈል ዋዜማ ተረድታለች።
በዚህም መሠረት፣ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በኹሉም ወረዳዎች ከዛሬ ጠዋት እስከ ቀትር ድረስ ስለደመወዙ አከፋፈል ሂደት ለሠራተኞቹና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ገለጻ ሲደረግ እንደዋለ ዋዜማ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች መረዳት ችላለች።
መንግሥት ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለኾኑ ሠራተኞች ከጥቅምት ወር 2017 ዓ፣ም ጀምሮ የደመወዝ ማስተካከያ አደርጋለኹ ብሎ የነበረ ቢኾንም፣ ኾኖም የደመወዝ ጭማሪው ባለፉት ኹለት ወራት ተፈጻሚ ሳይኾን መቅረቱ በብዙ የመንግሥት ሠራተኞች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ ቆይቷል።
መንግሥት፣ በተያዘው ዓመት ለሠራተኞች ለሚከፍለው ደመወዝ ከተጨማሪ በጀቱ ላይ 90 ቢሊዮን ብር መመደቡ ይታወሳል።
https://t.me/ethio_mereja_news