#ባለጸጋ ያደረጉን ድሆች፣ የደስታችን ምንጭ የሆኑ ሀዘንተኞች
በዓለት መሀል የሚገኝ በመነኮሳት ፀሎት ብቻ እየተቆረጠ ለፀበልተኞች የሚሰጥ የማር እምነት መገኛ፣ ድውያንን ከመፈወስ አልፎ ሙት ያስነሳ ድንቅ የሚያደርግ ጸበል ያለበት፤ ከዘጠና በላይ መናንያን ዓለምን ንቀው የተጠለሉበት ነገር ግን ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ፤ ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አድነት ገዳም።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ይህ ገዳም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ 6÷10 “ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።” ያለው ሕያው ቃል በዘመናችን በተግባር የሚታይበት ቦታ ነው፡፡
ምንም እንኳን መነኮሳቱና ገዳማውያኑ አሁንም ድረስ መንፈሳዊ ግዴታቸውን እየተወጡ በጽናት ቢቆዩም ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነው፡፡ ይህ ድንቅ ተአምር ያለበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም በአንድ በኩል አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት በድርቅ ምክንያት ምንም ዓይነት አዝርእት ያልበቀለበት በመሆኑ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆናል። ወዲህ ደግሞ በአካባቢው ያለው ጦርነት በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞች ፈጽመው እንዲሸሹና ገዳማውያኑ ያለምንም ጠያቂ በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ እንዲገኙ አድርጓቸዋል፡፡
ረሀብ፣ እርዛት፣ የማረፊያ ቦታ ችግር እጅግ ቢፈታተናቸውም፣ በአንድ በዓት ለሶስት ለአራት ለማደር ቢገደዱም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው የራሳቸውን ስጋዊ መከራ ችለው፤ ሌት ተቀን ስለ ሀገር ደህንነት፣ ስለ አሐቲ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ሰው ልጅ ሰላምና ጤንነት ሳያቋርጡ በጽናት የሚፀልዩ ናቸው።
ዙሪያችንን የከበበንና በእሳት ውስጥ ያሳለፈን መከራ ያልጣለን፣ በተገፋነው እጥፍ ጸንተን የቆምነው በእነዚህና በሌሎችም ገዳማውያን አባቶቻችን የማያቋርጥ የሕብረት ጸሎት ነው፡፡ የገዳማት መፈታት የመነኮሳት ከበዓታቸው መውጣት ይህን የሕብረት ጸሎት ያስተጓጉለዋል፡፡
ድውያነ ስጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የሚፈውሰውን ስፍራና ገዳማውያኑን ዛሬ ካልታደግን ዳሩ ሲወረር መሀሉ ዳር ይሆናል የሚለው ይፈጸምብናል፡፡ የተወረወረብን ጦር፣ የተመከረብን ክፉ ምክር በግላጭ ያገኙናል፡፡ በግንብ የታጠረ ቤታችን አቅበን የያዝነው ንብረታችን አይታደጉንም፡፡
ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበትን፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን ነገር ልናቀርብላቸው ይገባል። ለሰማያዊ ህይወታችን ስንቅ ይሆነናል ከመነኮሳቱ ፀሎት የበረከት ተካፋይ እንሆናለን፥ ለህሊናችንም እረፍት እናገኝበታለን።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444