#መምህሩን በሃይማኖት የመሰለው አብሪ ኮከብ
ቅዱሱ ታላቅ የሃይማኖት ጠበቃ ሲሆን የተወለደው ግብጽ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው፡፡ ሲሆን በምግባሩ፣ በትምሕርቱ ለምዕመናን ጥቅም ሆኗቸዋል፡፡ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ገና ልጅ ሳለ ምሥጢረ ክርስትናን ይማር ዘንድ ወደ ተፍጻሜተ_ሰማዕት ቅዱስ_ዼጥሮስ ሔዷል፡፡ ቅዱስ ዼጥሮስ የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክና ሊቅ ሲሆን በታሪክ የዘመነ ሰማዕታት መጨረሻ ተብሎ ይታወቃል፡፡ እርሱ ያስተማራቸው ብዙ አርድእት ቢኖሩም 3ቱ ግን ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ አኪላስ ውዳሴ ከንቱ ወዳጅ፣ ሆዱ ዘመዱ፣ አርዮስ ደግሞ ወልድ ፍጡር ያለ የቤተ ክርስቲያን ጠላት ሆኑ፡፡ አኪላስ ስለ ምንም የማይጨንቀው ሰው ነበር፡፡ ደጉ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በሃይማኖት በመመሰል በጾምና በጸሎት እየተጋ መምሕሩን ቅዱስ ዼጥሮስን ለመተካት ለመምሰል ይጥር ነበር::
ወቅቱ ዘመነ ሰማዕታት እንደ መሆኑ ቅዱሱ ከመምሕሩ ጋር ብዙ ነገሮችን አሳልፏል፡፡ አርዮስ ክዶ ቅዱስ ዼጥሮስ ካወገዘው በሁዋላ እንደ ባልንጀራ ገስጾ ሊመልሰውም ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን የአርዮስን ክፋት ከጌታ ዘንድ የተረዳው ቅዱስ ዼጥሮስ ደቀ መዝሙሩን እለእስክንድሮስን ጠርቶ መከረው፡፡ "እኔ ከሞትኩ በሁዋላ አኪላስ ይተካል:: ከአርዮስ ጋር ስለሚወዳጅ በ6 ወሩ ይቀሠፋል:: አንተ ግን ከአርዮስ መርዝ ተጠበቅ" አለው:: ይህንን ካለው በሁዋላ ወታደሮች የቅዱስ ዼጥሮስን አንገት ቆረጡ:: ይህ የተደረገውም እ.ኤ.አ በ311 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም አኪላስ ተሾመ:: እንደ ተባለውም ከአርዮስ ጋር ስለተወዳጀ በ6 ወሩ ተቀሰፈ:: በዚያው ዓመትም ቅዱስ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ ወይም ግብጽ 19ኛ ፓትርያርክ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ::
ሊቁ ሲሾም መልካም አጋጣሚ የነበረው ያ የመከራ ዘመን ማለፉ ሲሆን በጣም ከባዱ ግን የአርዮስ ተከታዮች ከተገመተው በላይ መበብዛታቸው ነው፡፡ ቅዱሱ በዽዽስ መንበሩ ለ17 ዓመታት ሲቆይ ዕንቅልፍና ዕረፍትን ትቶ እየጾመ፣ እየጸለየ፣ ምዕመናንን ከአርዮስ የኑፋቄ መርዝ ለመታደግ በቃልም በደብዳቤም መሸ ነጋ ሳይል ሕዝቡን እያስተማረ ታግሏል፡፡ በመጨረሻም በ325 ዓ.ም በንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አዋጅ በተዘጋጀው የኒቂያ ጉባኤ ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ካሳለፉ ከ318 ሊቃውንት ጋር አውግዞታል ለይቶታል፡፡ በጉባኤው መጨረሻም ጸሎተ ሃይማኖትን ሠርተው፣ መጽሐፈ ቅዳሴ ደርሰው፣ 20 ቀኖናወችን አውጥተው፣ አሥራው መጻሕፍትን ወስነው፣ ቤተ ክርስቲያንን በዓለት ላይ አጽንተው ተለያይተዋል:: የዚህ ሁሉ መሪ ደግሞ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ነው::
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልድ ዋሕድ፣ አምላክ ወልደ አምላክ፣ የባሕርይአምላክ፣ መሆኑን መስክሮ ክብርን አግኝቷል፡፡ የእምነታችንም መሠረቱ ይሔው ነው፡፡ ክርስቶስን ከአባቱ ጋር በመለኮቱ የሚተካከል ብለው ካላመኑ እንኩዋን ድኅነት ክርስትናም አይኖርም፡፡ ከጉባኤ ኒቅያ በሁዋላ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመልካሙ ጐዳና ሲጋደል ምዕመናንንም ሲያጸና ኑሯል፡፡ ዘወትር ወንጌልን በፍቅር ያነብ ነበርና ሲጸልይ የብርሃን ምሰሶ ይወርድለት ነበር፡፡ ስለ ውለታውም ቤተ ክርስቲያን በግብጽ ካበሩ 5ቱ ከዋክብት ሊቃውንት እንደ አንዱ ታከብረዋለች፡፡ ቅዱሱ ሊቅ በ328 ዓ.ም ዐርፎ በክብር ተቀብሯል፡፡
ገዳማዊያን በዓለም ላለነው ለኛና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገራችንም ይጸልያሉ፡፡ ገዳማቸውን በመርዳት፣ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444