ግጥሞች ፣ ሀገረኛ ወጎች እና ሌሎችም


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ሀገረኛ ግጥሞች
ወጎች
ድርሰቶች እና
ሌሎችም...

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ኤፍሬም ስዩም

ሰሞነኛ ፡ ሃሣብ

ከ ፡ አንድ በሬው ጋር
የራሱን፡ ትከሻ ፡ አጣምዶ፡ ለሚኖር
ወይም ፡ ለሚቆፍር ፡ ? ፡
የ ፡ አንድ-ገበሬ ፡
አንደኛ ፡ ጥያቄው ፡
ብቸኛም ፡ ጥያቄው ፡
በትከሻው ፡ ፈንታ
ተጣምዶ ሚያርስለት ፡ ''አንድ በሬ ፡ ነበር''።
ምትክ የሌለውን
ብቸኛውን ፡ ልጁን
ደብተሩን ፡ አስቀምጦ ፡ ውጊያ ፡ በማሣደር
ደረቱን ፡ ለቀለህ ፡ ጠጠር ፡ በማስገበር
የትም ፡ ወድቆ ፡ ባይቀር ፡ ? ፡
በአሞራዎች ፡ አንጀት ፡ ወድቆ ፡ ባይቀበር። ?።
ለአንድ ፡ ገበሬ ፡ ብቸኛ ፡ ጥያቄው
አልነበረም ፡ ሥልጣን ፡ በደም ፡ የሚከብር።
አልነበረም ፡ ዙፋን ፡ ሚፀና ፡ ባሻጥር።
አልነበረም ገንዘብ ፡ ናላን ፡ የሚያሰክር።
ግን
አንድ ፡ በሬ ፡ ብቻ፣አንድ ፡ በሬ ፡ ነበር
አንጀትን ፡ በማሰር
የምድርን ፡ በረከት ፡ ቆፍሮ ፡ ለማደር።
ሚበቃውን ፡ ያህል
በመዝራት ፡ ለማፈስ ልጁን ለማስተማር።

ኤፍሬም ሥዩም
16 02 2015 ዓመተ ፍዳ
(በኢትዮጵያውያን ፡ ዘመን ፡ አቆጣጠር)
https://www.facebook.com/ephraimsoliana


@ethio_poem
🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴


ኤፍሬም ስዩም
ሰሞነኛ ሃሣብ

"በሬ ፡ እየጎተቱ ፡
አቀርቅሮ-መሄድ ፡ መሬት እያረሱ ፡
እነዚህ ፡ ቀንበሮች
ከትሻችሁ ላይ ፡ ፈጥነው እንዲነሱ?
ሰይፋችሁን ፡ ሳሉ
ጠመንጆቻችሁን ከግድግዳው፡ አንሱ" ፡ ፡
ብለው የመከሩን ፡ ዛሬ ፡ የት ፡ ደረሱ ፡ ፡?::

ብለህ ፡ ብትጠይቅ ፡ ይሄ ፡ ነበር መልሱ::?::...

ተቀምጠዋል ፡ አሉ ፡
ደም ፡ ካቃቡህ ፡ ጋራ
ጠረጴዛ ፡ ዙርያ ፡ እንጀራ ፡ ሊቆርሱ ፡
በአፍሪካ ፡ ትሪ ላይ
የፈረንጅ አልጫን፡ ወጥ-እያጠቀሱ ፡
አጥንት ፡ ሊያስቆጥሩ ፡ ሬሳ ፡ ሊያስነሱ ፡
"ድርድር ፡ ላይ ፡ ናቸው
ያለምንም ፡ ምክንያት
ሜዳ ፡ የወደቁ ፡ የልጆቻችሁን ፡ ደምን ፡ እያገሱ።

ኤፍሬም ፡ ሥዩም
15 ፡ 02 ፡ 2015 ፡ ዓመተ፡ ፍዳ።
(በኢትዮጵያውያን ፡ አቆጣጠር)
https://www.facebook.com/ephraimsoliana

@ethio_poem
🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴


ኤፍሬም ስዩም
ሰሞነኛ ሃሣብ ፡

የእርሱን ፡ ቃል ፡ አድምጦ
በ'ርሱ ፡ ቃል ፡ ተ ፡ መ ፡ ስ ፡ ጦ፤
ሙዚቃውን ፡ ሰምቶ
መፈክሩን ፡ ነስቶ፣ምንሽር-አንግቶ፤
ቁጥር ፡ የሌለው ፡ ህዝብ ፡ ስለስሙ ፡ ሞቷል
ለስሙ ፡ ተጋድሏል።
እርሱ ፡ ቴ ፡ ምንተዳው ፡
አላማውን ፡ ስቷል ፡
መፈክሩን ፡ ትቷል ፡:
ሻምፓኝ ፡ እየረጨ
ጮማ ፡ እየቆረጠ ውስኪውን ፡ ያስቀዳል ፡
የሆነን ፡ ረስቶ ፡
በሬሦች ፡ ክምር ላይ ፡ ህይወቱን ፡ ቀጥሏል
የውሾች ፡ ነፍስ ፡ እንጂ
መቼ ፡ የሰው ፡ ህይወት ፡ ያለፈ ፡ መስሎታል።
ይሄ ......!......!.....!....?

inspired by Earnest Heamingway
''half a million are dead
because of him
and heis living right
this son of a bitch''.
ኤፍሬም። ሥዩም

https://www.facebook.com/ephraimsoliana

@ethio_poem

🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴


5ሺ ሴቶች ወርቅ
ጉደፍ ፀጋዬ


ሴቶች ማራቶን ወርቅ
ጎተይቶም ገብረስላሴ


ወንዶች ማራቶን ወርቅ
ታምራት ቶላ


10ሺ ሴቶች ወርቅ
ለተሰንበት ግደይ


ቄለም ወለጋ 😪😪😭😭😭😭😭

የወገኖቻችን ሞት ይብቃ።


አዝማች
የግጥም ኮንሰርት
ከ ረድኤት ተረፈ ጋር

ሐሙስ
ሰኔ 30
በአለም ሲኒማ
ምሽት 11:30


ተለቋል....😍💪💪💪💪💪


(በላይ በቀለ ወያ)

@ethio_poem

ምን አይነት ቄስ ናቸው ፣ ምፀት የለመዱ
"አባት ይፍቱኝ" ስል
"አብይ ይፍታህ "ብለው ፣ አሳልመውኝ ሔዱ
።።።።።
ዳሩ እውነት አላቸው ፣ ቀልዳቸው ቢመርም
ምህረት ያውቃልና
እኛ ብናጠፋም ፣ አምላክ ሰው አያስርም።

(( በላይ በቀለ ወያ ))

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@ethio_poem
@ethio_poem
@ethio_poem


(በላይ በቀለ ወያ)
@ethio_poem


እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ሞኝ ነሽ ተላላ
ትዝ ትይኛለሽ ፣ ሸንኮራ ስበላ፡፡
"እንዴት " አትበይኝ!
እንደዚህ ነው ብዬ ፣ ካንቺ አልሟገትም
ጥርሳም ገዢ ሁሉ...
ጠአምሽን መጦ ፣ ይጥልሻል የትም!!!

(በላይ በቀለ ወያ)
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@ethio_poem
@ethio_poem
@ethio_poem


"ለምን ሞትህ" ቢሉት ...
አልሞትኩም እያለ ፣ ትውልድ ይሟገታል
ድሮስ
ኖሮ የማያውቅ ህዝብ ፣ ምን ሆኖ ይሞታል?!!!
።።።።።
(በላይ በቀለ ወያ ©)
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@ethio_Poem
@ethio_Poem
@ethio_Poem


free በላይ በቀለ ወያ 😡😡😡😡


ብሶት የወለደው ወቅታዊ ሆያ ሆዬ
(በላይ በቀለ ወያ)

@ethio_poem
.
.
መጣና በአመቱ
ሰበር ዜና ተመልከቱ
በሎም በሎም ነው
የምንለው
ሆያ ሆዬ ናና
ተንከባለል በጎዳና
ሆያ ሆዬ ጉዴ
ጦርነት ነው ልማዴ
።።።፣
የኢትዮጵያ ህዝቦች /ሆ/ እንደምን ናቹ
ከቆላ ተንቤን / ሆ/ መጣንላቹ
ሆ ስንል አመፅ /ሆ / እንዳይመስላቹ
ሆያ ሆዬ ነው /ሆ/ ምንልላቹ
ሆያ ሆዬ ዝና
ተቆፃፀር ደምስስና
።።
ሆያ ሆዬ /ሆ/ ሆይ የኔ ጌታ /ሆ/ ጌታ ጠንበለል
ድሮኗ መጣች /ሆ/ ወዴት ልጠለል
ምሽጌ ሁሉ /ሆ/ ተደረማምሷል
የዘር ጥላቻ /ሆ/ በአንድነት ፈርሷል
ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ /ሆ/ የት ይደረሳል
ሆያ ሆዬ ጉዴ
መፈርጠጥ ነው ልማዴ
ሆያ ሆዬ ናና
እዝ በወሬ ደምስስና
።።
የኛማ አብይ "ሆ/ ጥርሰ በረዶ
የማይናደፍ "ሆ" ከንብ ተወልዶ
በለውጥ ሰበብ /ሆ/ሲገድለን ስንቱ
ወንጌል ይመሥል ሆ/ ህገ መንግስቱ
ምህረት ፍቅር ነው ሆ/ ሁሌም ቃላቱ
ብለን ስናማው "ሆ" ንቀን ስናየው
ጭስ ሆኖ መጣ /ሆ / ንብ ላሰቃየው
በሎም በሎም ነው የምንለው
በነጋታው ደግሞ ወየው ወየው
ህወሀቴ ናና
በጡዘት ጎዳና
እዛ ማዶ ሆ እሳት ይነዳል
እዚህ ማዶ ሆ ቦንብ ይፈነዳል
ድሮኗን ያየ /ሆ/ ዓለም ይፈርዳል
እንኳን ከገደል /ሆ/ ሲኦል ያወርዳል

ዓመት ዓውደ አመት /ድገምና/ አመት /ድገምና/
ኢትዮጵያ ሀገራችን /ድገምና/ አመት /ድገምና/
ምድራዊ ገነት /ድገምና/ አመት /ድገምና/
ከሲኦል ተላቃ /ድገምና/ አመት /ድገምና /
ሰላም ይብዛላት /ድገምና/ ዓመት ድገምና
ፍቅር ይፍሰስባት "ድገምና" አመት /ድገምና /
አመት ድገምና
አመት ድገምና
ዓመት ድገምና
ድገም በስንዴ ድገም በጤፍ
ጠላቷ ይርገፍ
እንሾላ ፍሬ እንደቆላ ጤፍ።
ድገም በስንዴ ድገም በጤፍ
ከማንም ከምንም ኢትዮጵያ ትግዘፍ
፣፣፣፣

(በላይ በቀለ ወያ)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@ethio_poem
@ethio_poem
@ethio_poem


ቀጥረሽኝ....
ፈላስፋ አደረግሽኝ(ርእሱ ነው)
(በላይ በቀለ ወያ)

@ethio_poem
.
.
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፣።።፣።፣
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!

(በላይ በቀለ ወያ)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@ethio_poem
@ethio_poem
@ethio_poem


( ረድኤት ተረፈ )

@ethio_poem
.
.
.
የማይወዳደር እኩያ የሚያጣ
ከልቤ ግርጌ ስር አንዳች ስሜት ወጣ
ተሰማኝ ወደድኩህ ያንተን ጣዕም ለየሁኝ
ቆዳዬ ቀመሰህ ምላሴን ከዳሁኝ

ከየትኛው አካሌ ፍቅርህ የወደቀው
የሚያርበተብተኝ ጥፍሬን የሚነዝረው
አካልስ አለ ወይ የሚታይ ሚቀመስ
ሴትነት ገላዬን ነክቶ ሚያጎለምስ

ንገረኝ አንተዬ ከደጅ እንዳያድር ዳስም ልጣልለት
እንዲህ ያለ ፍቅር አያድርም ከኔ ቤት
በአዳፋዬ ባያድፍ ንፁህ ጥሩ ፍቅርህ
ከቆሸሸ ገላ ከዚህ በድን ይሽሽ

እንዲህ ያለ ልመና ሚዛን አያነሳም
የፍቅር ባህሪ ዙፋንን አይሻም
የት ጋር ነው የሚሰማኝ ምኔን ነው የያዝከው
የት ጋር ነው ያገኘኸኝ ምኔን ነው ያጣኸው
ብቻ ከልቤ ስር ስሜቴ ይፈልቃል
የደረስክበትን ያልደረስክበትን
ረቂቁ ፍቅርህ እሱ ብቻ ያውቃል።

ረድኤት ተረፈ

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@ethio_poem
@ethiop_poem


አልወዳትም እንጂ አልጠላትም ....#5
(የመጨረሻ ክፍል)

(ሜሪ ፈለቀ)

@ethio_poem
.
.
"ኤደን ምን ይሰማሻል?"

"ምንም"
(ዝም ተባብለን ሰዓቴ አልቆ እመለሳለሁ::)

በሌላኛው ቀንም ........

"ኤደን ዛሬስ ለማውራት ዝግጁ ነሽ?"

"አይደለሁም!! ማውራት አልፈልግም!"
(ዝምምምምም..... ሰዓቱ ያልቃል)

ደግሞ በሌላኛውም ቀን

"ኤደን ዛሬስ ለመጀመር ዝግጁ ነሽ?"

"ምኑን?"

" ማውራት ትፈልጊያለሽ?"

"እኔ ምንም የማድረግ ፍላጎት የለኝም!!"

(የምፈልገው አንድና አንድ ነገር .... የቀብሯ ቀን ጭልጥ አድርጎ የወሰደኝ ጨለማ ለዘለዓለሙ እንዲወስደኝ ነው)

በሌላኛው ቀን አልጠየቀኝም:: ገብቼ ስቀመጥ ሰላምታ ሰጥቶኝ ዝም አለ::

"ዛሬ አትጠይቀኝም እንዴ?"

"ምኑን?"

"ዝግጁ መሆን አለመሆኔን?"

"ነሽ?"

"አይደለሁም!"

"ጥሩ!! ዝግጁ እስክትሆኚ ድረስ የሚሰማሽ እዚህ መጥቶ መቀመጡ ከሆነ ዝም በይ... ማውራት ሲሰማሽ አውሪ.... ማልቀስ ሲሰማሽ አልቅሺ.... መጮህ ሲሰማሽ ጩሂ ..... ሰዎች ሀዘናቸውን በተለያያየ መንገድ ነው የሚያስተናግዱት.... የተለያየ ጊዜ ይወስድባቸዋል::"

"ሀዘን አይደለም የሚሰማኝ!!"

"እሺ!! ምንድነው የሚሰማሽ?"

"ምንም!!! ዝም ... ፀጥ .... ያለ ስሜት!!"

ለብዙ ቀናት ተመላለስኩ .... እሄዳለሁ:: እቀመጣለሁ:: ሰዓቴ ያልቃል:: እመለሳለሁ::

"ዛሬ አሻንጉሊትሽን የት ትተሻት መጣሽ?" አለኝ

"ሰጥቻት መጣሁ:: ..... 'ያውልሽ' ብዬ መቃብሯ ላይ ወርውሬላት መጣሁ:: ትውሰደው .... " እንባዬ ከወራት በኃላ ላስቆመው እንዳልችል ሆኖ ይንጠኝ ገባ ...... ማልቀስ ማቆም እፈልጋለሁ:: .. አቃተኝ.... የቀብሯ ቀን እንደሆነው ራሴን የምስት መሰለኝ .... ጨለማው ናፈቀኝ... ግን አልመጣም... አልወሰደኝም.... ደብዳቤዋን ከኪሴ አውጥቼ ሰጠሁት::

"አየህ በዝህች ሁለት መስመር ደብዳቤ እንዳልሞትም እንዳልኖርም አስራኝ ሞተች:: አንብበውማ! ጮክ ብለህ አንብበው!!"

" አንቺ ደግሞ በተራሽ የእኔንም ደርበሽ ኑሪልኝ:: የከፈልኩትን ዋጋ እንዳታከስሪኝ .... ደስ ተሰኝተሽ ኑሪና ዋጋዬን ክፈዪ!! .... ፖኒን ትቼልሻለሁ::" ጮክ ብሎ አነበበው .... ቤተሰቦቻችን እንዳልገባቸው ሁሉ እሱም አልገባውም..... የሆነው ሳይገባቸው ነው 'ጭንቅላቷ ተቃውሷል' ብለው ሳይካትሪስት የቀጠሩልኝ....

"ፖኒ ያቺ አሻንጉሊት ናት!" እንደገባው ራሱን ነቀነቀ.... "በጣም ልጅ ሆነን ለሁለት አንድ አሻንጉሊት ተገዛልን:: እሷ ስም አወጣችላት:: አልተቃወምኩም:: .... የሆነ ቀን እኔ ስጫወት ደርሳ ካልወሰድኩ አለች ... ተደባደብን ... አባታችን መጥቶ አሻንጉሊቷን ከእኔ ቀምቶ ለሷ ሰጣት ... ቀን ቀን በአሻንጉሊቷ መጫወት የምትችለው እሷ መሆኗን አወጀ:: ከፈለግኩ ማታ እሷ ስትተኛ መጫወት እንደምትችል... ያውም እሷ ከፈቀደችልኝ..... ነገረኝ:: ምርርርርርር ብዬ አለቀስኩ::...... ያስለቀሰኝ ከአባታችን ለሷ ማገዝ በላይ የሷ መደሰት ነበር:: እንዳለመታደል ሆኖ ሁሌም እሷ ስትተኛ ጠብቄ ለመጫወት እቀመጥና እንቅልፍ ቀድሞ ስለሚጥለኝ ያልፈኛል::.... ምን ማለቷ ነው? ስትሞት ትታልኝ የምትሞተው?"

"ምን ማለቷ ይመስልሻል አንቺ?"

"እኔ ምን አውቅላታለሁ? ህይወትሽን የቀማሁሽ እዛጋ ነው ... ከዛ ጀምሪ ማለቷ? ያውልሽ ይስፋሽ ማለቷ? እኔ ምን አውቅላታለሁ ምን አድርጊ እንደምትለኝ? ቆይ እሷ ራሷን እንደክርስቶስ ነው የምታየው? ማነኝ ብላ ነው የምታስበው ህይወቷን ስትሰጠኝ ..... በቃ ሞተችልኝ ብዬ በደስታ የምኖር ነው የመሰላት? ደሞ ቆይ ክርስቶስኮ ለአንድ ሰው አልሞተም .... ለዓለም ህዝብ ነው የሞተው... ክርስቶስ ለአንተ እንደሞተልህ ብታውቅም ስላላመንከው እኔ አሁን የሚሰማኝ አይነት ሸክም አይሰማህም .... ሌላ የሆነ ሰው አምኖ እንደሚያገለግለው ታውቃለህ ... እሷ ምን አስባ ነው ለአንድ ለእኔ ህይወት ከፍላ ... ከዛ በደስታ እንድኖርላት የምትፈልገው? ቆይ የቱጋ ሀ ብዬ መኖር እንድጀምርላት ነው? ቆይ አንተ ስታስበው ጤነኛ ሆኜ ራሱ መኖር የምችል ይመስልሃል?"

"አዎ ይመስለኛል!!"

"እኮ እንዴት?" ..... እስከዛሬ ያላወራሁበትን ሰዓታት ጨምሬ ለፈለፍኩ::

"ራስሽን ይቅር በማለት ትጀምሪያለሽ!!"

"ሌላ 30 ዓመት መኖር ቢሰጥሽም መኖር አትጀምሪም አትለኝም ታዲያ?"

"ሳይኖሩ ከመሞት መኖር ጀምሮ መሞቱ አይሻልም ታዲያ? ...... "
......
.....
"ለራሴ ስል መኖር አልፈልግም..... ለሷ ስል ደግሞ መሞት አልፈልግም"

.....

"ሁለቱን ለማስታረቅ ነው ከራስሽ መታረቅ ያለብሽ..... "

................. ጨርሰናል................

(አላለቀም ብትሉም አልቋል..... አልቋል ብትሉም እንደዛው)

(ሜሪ ፈለቀ)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@ethio_poem
@ethio_poem
@ethio_poem


……ህልሜን አደራ!
(በውቀቱ ስዩም)

@ethio_poem
.
.
ባይመረመሬ ፥ ጥበብ ተሽከርክሮ
ከወርቃማ ብርሃን ፥ ከብርማ ፀዳል
የተሰራ ሸማ ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ስር ፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ ፥ ከህልሞቼ በቀር፤
:
የኔ ውድ እንግዲህ
ህልሜን እግሮችሽ ስር ፥ ከዘረጋሁ ወዲህ
ዝግ ብለሽ እርገጪ ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና ፥ የምትራመጂ።

የማለዳ ድባብ

(በእውቀቱ ስዩም)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@ethio_poem
@ethio_poem
@ethio_poem


እስከዛሬ ድረስ...
@ethio_poem

(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
ስኳር ስኳር ለሚል ፣ እድሜ ላንቺ ከንፈር
ስኳር ጠፋ ብዬ ፣ አልጮሁም እንዳገር፡፡
አንዴ ስትስሚኝ..
አንድሺ ቶን ስኳር ፣ ትለግሺኝ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ዛሬ ግን ስትስሚኝ...
ስኳር ስኳር የሚል ፣
የከንፈርሽ ጠአም ፣ ጠፍቶብኛል ውዴ
እስቲ ልጠይቅሽ...
አንቺም ለኬንያ ፣ ተሽጠሻል እንዴ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
(በላይ በቀለ ወያ)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@ethio_poem
@ethio_poem
@ethio_poem

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

3 030

obunachilar
Kanal statistikasi