ጎንደር ዩኒቨርሲቲ "የጎንደር ቃልኪዳን ቤተሰብ" የተመሠረተበትን ስድስተኛ ዓመት አክብሯል።
በ2012 ዓ.ም "የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት" በሚል የተጀመረው ፕሮግራም ስድስተኛ ዓመት በዓል፥ የዩኒቨርሲቲው አዲስና ነባር ተማሪዎችና የቃልኪዳን ወላጆች በተገኙበት ተከብሯል፡፡
ባለፉት ስድስት ዓመታት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች በፕሮጀክቱ ትስስር ተፈጥሮላቸውና የቃልኪዳን ወላጆችን አግኝተው ትምህርታቸውን በሚገባ ሲከታተሉ መቆየታቸውን ምስክርነት ሰጥተዋል።
"የጎንደር ቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት" ተሞክሮ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮጳ እና በጃፓን በሚገኙ የትምህርት ተቋማት የተለመደ አሠራር እንደሆነ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ፈንድ ፎር ኢኖቬሽን ኢን ዴቨሎፕመንት በተባለ የፈረንሳይ ተቋም ድጋፍ በጎንደር የቤተሰብ ትስስር ፕሮጀክት ላይ ምርምር እየተካሄደ እንደሚገኝም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገልፀዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ለፕሮጀክቱ ዕውቅና እንደሚሰጥና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።