Postlar filtri






ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በሞጆ እና አዳማ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች የስራ ጉብኝት አደረጉ
***************************************************
( ጉምሩክ ኮሚሽን፤ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም)

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ የሞጆ እና አዳማ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ኮሚሽነሩ በጉብኝታቸው በሁለቱ ቅ/ፅ/ቤቶች በገቢ አሰባሰብ፣ ህግ ተገዢነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ላይ ምልከታ አድርገዋል፡፡

ቅ/ፅ/ቤቶቹ በኮሚሽኑ ገቢ አሰባሰብ እቅድ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑን እና በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን ገቢ ለማሳካት በተለይም በእቃ አወጣጥ እና እዳ አሰባሰብ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም ቅ/ፅ/ቤቶቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በላቀ ሁኔታ መፈፀም እንዲችሉ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም ቅ/ፅ/ቤቶቹ በገቢ አሰባሰብ፣ ህግ ተገዢነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ላሳዩት መሻሻል ኮሚሽነሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission






በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል ፣ የነገን ሰብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ቃል 21ኛው ዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡
#######################

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም )

በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል ፣ የነገን ሰብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ቃል 21ኛው ዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡

በአከባበር ስነስርዓቱ የገቢዎች ሚንስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ፣ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መስከረም ደበበ፣ የጉምሩክ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሙሉወርቅ ደረሰ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ አማካሪዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ የስራ ሂደት መሪዎች እና የቡድን አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ፤ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መታገል የአመራር ወይም የስነ ምግባር መከታተያ የስራ ክፍሎች ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሊታገለው የሚገባ ችግር መሆኑን ጠቅሰው በተለይም ሁለቱ ተቋማት ሰፊ ወጣቶችን ያቀፉ እንደመሆናቸው ወጣቶች ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን እንዲታገሉ ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም፣ ሙስና ነፃ የገበያ ውድድር እንዳይኖር፣ ኢንቨስትመንት እንዲቀጭጭ እና የሃገር ኢኮኖሚ እንዳያድግ የሚያደርግ በተለይም በገቢው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ እንዳይሰበሰብ የሚያደርግ ማነቆ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተቋማቱ በርካታ ሰራተኞች በታማኝነት የተሰጣቸውን ሀላፊነት የሚወጡ ቢሆኑም ጥቂቶች ደግሞ ሀላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው ብልሹ ምግባር የታየባቸው መኖራቸውን ገልፀው በጥፋተኞች ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ሚንስትሯ ጠቁመዋል፡፡
የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መስከረም ደበበ በበኩላቸው በተለይም ከደረሰኝ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚስተዋል ችግር የብልሹ ምግባር ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን በቴክኖሎጂ ለመፍታት ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሙሉወርቅ ደረሰ በበኩላቸው፤ በታሪፍ ፣ በዋጋ ትመና እና በኮንትሮባንድ መከላከል ስራዎች ለስነምግባር ግድፈት በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ለማረም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ እና ሥነምግባር ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በተመለከተ በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራር እና ሥነምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች በሆኑት በአቶ ደደኔ ደስታ እና በወ/ሮ ሰርካለም አበበ የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት :-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsommission



7 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.