….ማካበድ ይሻላል!
(ሕይወት እምሻው)
የዚህ የኮሮና ነገር አለምን ማስጠበብ ከጀመረ፣ በተለይም ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠ አንስቶ የሁላችንም አስተያየትና ጥንቃቄ፣ አንዳንዴም የፍርሃት መጠን ለየቅል ነው፡፡
ለምሳሌ እኔ….ጥቂት የማይባሉ የስራ ባልደረቦቼና ወዳጆቼ ዛሬ እንኳን፣
‹‹ስልክ በደወልኩ ቁጥር እጅህን ታጠብ መባል ሰለቸኝ….ቲቪ በከፈትኩ ቁጥር ኮሮና ኮሮና መባል አማረረኝ…የምወደውን ሰው አለማቀፍ፣ የምፈልገውን ሰው እጅ አለመጨበጥ ታከተኝ….››እያሉ ይማረራሉ፡፡ ‹‹መንግስት አካበደ›› እያሉ ይነጫነጫሉ፡፡
በዚህ ሁኔታ ተከብቤ ኮሮና አሜሪካን እና አውሮፓን ስለማመሱ ለቀናት ያልተቋረጠውን ተከታታይ ዜና አያለሁ፡፡
የኢትዮጵያን እና ሌሎች ሃገራትን የጤና ስርአት ለማሻሻል ገንዘብ የምትሰጠው አሜሪካ ለሃኪሞቿ የሚሆን ጭምብል አንሷት ሃኪሞቿን ‹በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም…! ሻሽ ቢጤ እያሰራችሁ አክሙ›› ለማለት መገደዷን ሰማሁ፡፡
ጣልያን ሆስፒታሎቿ በኮሮና ታካሚዎች ተጥለቅልቀው ቅንጡ ሆቴሎችን ጊዜያዊ ሆስፒታል እያደረገች ስለመሆኑ አየሁ፡፡
ኢራን በየአስር ደቂቃው አንድ ሰው ለበሽታው እየገበረች መሆኑን ተረዳሁ፡፡
ከዚያ ኢትዮጵያን በእነሱ ቦታ አሰብኳት፡፡
እኛ እኮ ለወትሮውም ህዝባችን ብዙና ምስኪን፣ አካሚዎቻችን እና ሃኪም ቤቶቻችን ደግሞ እጅግ ጥቂት ናቸው፡፡
የህክምና ስርአታችን በችግር የተተበተበ፣ እንኳንስ ገፍቶ የመጣን ወረርሽኝ ቀርቶ መደበኛ ታካሚን በአግባቡ አክሞ የማያረካ ኋላ ቀር ነው፡፡
‹‹ያደጉት›› ሃገሮች በዚህ ወረርሽኝ እንዲህ መላ ቅጣቸው ከወጣ እኛ ምስኪኖቹ ይሄን ወረርሽኝ ሳይዘን ካልያዝነው፣ ገፍቶ እንዲመጣ ከፈቀድንለት መዘዙ ብዙ ነው፡፡
የሚያዋጣን ይሄን በሽታ የመከላከል እድሉ ካለን ያንን እድል ሳያመልጠን መያዝ ብቻ ነው፡፡
….እና ምን ልል ፈልጌ ነው? ይሄ ወረርሽኝ በእኛ ጥንቃቄ እና አለመዘናጋት ሳይስፋፋ ካላቆምነው ልንገምተው የምንፈራው ጥፋት ያመጣብንናልና….ግድ የለም, በኮሮና ጉዳይ ማካበድ ይሻላል…..!
…እናም ወገኖቼ……
አካብዱ፣ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ እጃችሁን ፍትግ አድርጋችሁ ታጠቡ፡፡
አካብዱ፣ ምርጫ ካላችሁ በተፋፈገ አውቶብስና ታክሲ አትጓዙ፡፡
አካብዱ፣ ካልተገደዳችሁ ሰው የሚበዛበት ቦታ አትሂዱ፡፡
አካብዱ፣ ሊያቅፋችሁ የመጣን እምቢ በሉ፣ መጨባበጥን ለጊዜው ተዉ፡፡
አካብዱ፣ የጤና ባለሙያ የሚነግራችሁን ሁሉ አንድም ሳታጓድሉ ተግብሩ፡፡