°°°መሰላል°°°
መሰላል ለመውጣት
አለው ትልቅ ብልሀት ።
ያላዩን ጨብጦ ፤
የታቹን ረግጦ ፤
ወደላይ መመልከት
እጆችን ዘርግቶ በሀይል መንጠራራት።
ጨብጦ መጎተት የላዩን ፤
ላይ ታች እንዲሆን ።
አንድ በአንድ እየረገጡ
መሰላል የወጡ ፤
ብልሆች የማይጣደፉ
ሞልተዋል በያፋፉ ።
ዘርግተው የጨበጡት መርገጥ
የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ ።
ሲወርዱ ግን ያስፈራል የረገጡትን ያስጨብጣል ።
#መስፍን_ወልደማርያም ፣ እንጉርጉሮ ፤
@ethopianism
መሰላል ለመውጣት
አለው ትልቅ ብልሀት ።
ያላዩን ጨብጦ ፤
የታቹን ረግጦ ፤
ወደላይ መመልከት
እጆችን ዘርግቶ በሀይል መንጠራራት።
ጨብጦ መጎተት የላዩን ፤
ላይ ታች እንዲሆን ።
አንድ በአንድ እየረገጡ
መሰላል የወጡ ፤
ብልሆች የማይጣደፉ
ሞልተዋል በያፋፉ ።
ዘርግተው የጨበጡት መርገጥ
የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ ።
ሲወርዱ ግን ያስፈራል የረገጡትን ያስጨብጣል ።
#መስፍን_ወልደማርያም ፣ እንጉርጉሮ ፤
@ethopianism