ጉርሻ
በ 😍አዳም ረታ
‘ጉርሻ የሚያቀራርብ ነው። በጉርሻ አይኖቻችን የፈጠሩት ርቀት ይጠፋል። በኋላ እንዳየሁት መጎራረስ ወደ ወሲብ የሚጠጋ ኢትዮጵያዊ ድርጊት ነው።
በማዕድ ዙርያ እንዲቀመጥ የተገደደው ተከፋፍሎ ግለሰብ የሆነው ቡድንና ማሕበረሰብ በሚዘረጋው የበላተኛ እጅ ድልድይነት ይቀራረባል። ‘አብረን በልተን’ ሲባል ውስጡ ከባድ የጉርሻ ይዘት አለ። ጉርሻ አገናኝ አቀራራቢ ድርጊት ነው።
ሌላም ዝርዝር ረድፍ አለው።
በርበሬና ሚጥሚጣ በመብላት ሂደት ውስጥ ዜጋ ያልበዋል። በዚህም በእያንዳንዱ እንጀራ ሰበከት ላይ የአብሮ በላተኛችን የወዝ አሻራ ይታተማል። ይሄ አስገራሚ የሆነ ግላዊ ማህተም ያለው (እያንዳንዱ ሰው የራሱ ከማንም ግለሰብ የሚለየው የጣት አሻራ ስላለው) የተቀናበረ ድራማ በሚጠጋ ‘ማጉረስ’ ተብሎ በተሰየመ ድርጊት ማሕበራዊ ቅንጅት ይከናወናል። በጉርሻ ሂደት የግልና የማሕበራዊ አላማዎች ሳይጋጩ ይቀርባሉ።
ይሄ ሁሉ አማካይ ወደ ሆነው ብልት ወደ አፍ ያመጣል።
ጉርሻ በአፍ መግባት አለበት። የጉርሻ አጉራሽና ጎራሽ የሚረካከቡት ታላቁ ቀዳዳ አፍ ነው። ለሕይወት የሚያስፈልገው ምግብ የሚገባበት፣ ቋንቋ የሚሰራበትና ሰዎች በራሳቸውና በሌላው መሃል ያለውን ልዩነት የሚያጠቡት ወይንም የሚያሰፉት በአፍ ነው። (ሃሃሃሃ) አፍን ሴቶችና ወንዶች የሚጋሩት ቀዳዳ ነው። ይሄ ግንዛቤአችንን ጠንካራ ሁለንተናዊነት ይሰጠዋል። ጎራሽ አፉን ሲከፍት አጉራሽ ሕይወት እንደሚሰጠው አምኖ ነው።
እኔና አንተ፣ አንተና አንቺ….. ወዘተ በስምረት ውስጥ የሚጠፉበትና ‘እኛ’ የሚሆኑበት ነው። የቦታ ርቀት የሚወድምበት ነው።
አብረው ተቀምጠው ሲበሉ የማይጎራረሱ ሃበሾች ቁጥራቸው ከበዛ ኢትዮጵያ የምትባል እንደሌለች ወይ በመለወጥ ላይ እንዳለች ምልክት ነው።’
እቴሜቴ ሎሚ ሽታ
@ethopianism