"መንገድ ተዳዳሪ ነኝ።
'መተዳደር' ከባድ ቃል ነው። 'መተዳደር' የሚለው ቃል በሐምሌ
ብርድ ወፍራም ጋቢ ተከናንቦ አጃ መጠጣት ይመስላል። ግን
እንዴት ነው መንገድ ላይ እየኖሩ መተዳደር? . . .
ላውንቸር ተሸክሜ በኩራት የተራመድኩበት ጎዳና ላይ፤ ሀገር
እንደሌለው ሰው አፈር 'እፍ' ብዬ ተኛሁ . . . .
ያልሞትኩት ፈሪ ስለሆንኩ ይመስለኛል። ፈሪ አልነበርኩም፤ ግን
ይመስለኛል።
ያቺ ሀገሬን፣ ያቺ በሚስቴና በእንጀራ ልጄ የተካኋትን ሀገሬን
እሞትላታለሁ ስል እውነቴን ነበር።
የቆምኩት እስዋ ላይ አይደለ?
የምተነፍሰው እሷ ላይ ቆሜ አይደለ?
አቅም የላትም ግን እንደ ዶሮ ጭራ አብልታ ታሳድረኛለች። ግራና
ቀኝ በጠላት ተከባ፣ እንደ ልጅ መከራዋን እንዳላይ አድርጋ ከልላ፣
ጠራም ደፈረሰም ጠላዋን አጠጥታኛለች።
ወታደር ስለሆንኩ፤ እኔንም ደርቦ ልዩ ጥቅም እንዳገኘሁ ሁሉ
'የወታደር መንግስት' እያለ ሲሳደብ የኖረ ሲቪል ለእኔ ግድ
ይሰጠዋል?
ሲሰድበኝ ኖሮ እንደገና ሲጨንቀው 'ትታችሁ መጥታችሁ ሀገራችንን
አስወሰዳችሁ' እያለ ከሚያወራ ቀባጣሪ ምን ይጠበቃል? . . .
አገሬን ነክተውብኝ ጮኼ የተነሳሁ ነኝ። ምርምር አላደርግኩም።
ተማርን እንደሚሉት አገሬን በቃላት ነዝንዤ በፉክክርና በምቀኝነት
ለጠላት አልሰጠሁም። ጠላቷ እንዲደፍራት የእናቴን ቀሚስ ወደ
ላይ አልሰበሰብኩም። ደፋሪው የልጆቿን ታሪክ ሰምቶ ሲርበተበት፣
ሊደፍራትም ሲፎክር 'አይዞህ' ብዬ የሱሪውን አዝራር
አልፈታሁለትም።
እኔ የፊት በር ስዘጋ የጀርባ በር ከፍተው፣ ጠላታቸውን አገራቸው
እልፍኝ አስገብተው፣ እናታቸው ተከናንባ የተኛችበትን ብሉኮ
ገፈው፣ 'ይቻትልህ' እንዳሉት አጅሬዎች አይደለሁም . . .
ከርሞ ከርሞ መቆየት ደጉ፤ ጠላ እየጠጣሁ እዛ አለማያ ኮሌጅ
የሚያማምሩ ለጋ ወጣቶች ሳይ በልቤ 'ለመሆኑ ለእነሱ እግሬ
እንደተሰነከለ፣ ዐይኔ እንደጠፋ፣ ሳንባዬ በብርድ እንደታመመ
ይገባቸዋል? እላለሁ . . .
ወሰናቸውን ስጠብቅላቸው አካሌን ባጎድልም፤ ከምንም
የማይቆጥሩኝ መዓት ናቸው። ድሮ በቆራጡ ዘመን ሀገር ለማዳን
ስንረባረብ፣ ዛሬ ምን የመሰለ የሚያምር ጫማ ለመግዛት ሲሻሙና
ሲያብዱ አያለሁ። እዛም ጥጥና ጎማ የሚሸት ጫማቸው ስር
ያልታዘነለት ተሸናፊ ነኝና አፈር እየተነፈስኩ፣ አስፋልት እየላስኩ
እርመጠመጣለሁ።
ከጫማቸው የረከስኩ ነኝ . . .
የጀልዴሳን አወዳይ ጫት በጎልማሳነቴ ከዚያድ ባሬ መንጋጋ
አላቅቄ እነሱ አፍ አስገብቼ፣ ይኸው መርቅነው በፈዘዙ አይኖቻቸው
እያዩ ጣል ጣል ያደርጉኛል . . .
እገረማለሁ?
.
.
ኧረ አልገረምም!
ክርስቶስን የከዳው አብሮት ቂጣ የቆረሰ እኮ ነው።
ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም ቢሉ ዕውነት አለው።
***
# የስንብት_ቀለማት
'መተዳደር' ከባድ ቃል ነው። 'መተዳደር' የሚለው ቃል በሐምሌ
ብርድ ወፍራም ጋቢ ተከናንቦ አጃ መጠጣት ይመስላል። ግን
እንዴት ነው መንገድ ላይ እየኖሩ መተዳደር? . . .
ላውንቸር ተሸክሜ በኩራት የተራመድኩበት ጎዳና ላይ፤ ሀገር
እንደሌለው ሰው አፈር 'እፍ' ብዬ ተኛሁ . . . .
ያልሞትኩት ፈሪ ስለሆንኩ ይመስለኛል። ፈሪ አልነበርኩም፤ ግን
ይመስለኛል።
ያቺ ሀገሬን፣ ያቺ በሚስቴና በእንጀራ ልጄ የተካኋትን ሀገሬን
እሞትላታለሁ ስል እውነቴን ነበር።
የቆምኩት እስዋ ላይ አይደለ?
የምተነፍሰው እሷ ላይ ቆሜ አይደለ?
አቅም የላትም ግን እንደ ዶሮ ጭራ አብልታ ታሳድረኛለች። ግራና
ቀኝ በጠላት ተከባ፣ እንደ ልጅ መከራዋን እንዳላይ አድርጋ ከልላ፣
ጠራም ደፈረሰም ጠላዋን አጠጥታኛለች።
ወታደር ስለሆንኩ፤ እኔንም ደርቦ ልዩ ጥቅም እንዳገኘሁ ሁሉ
'የወታደር መንግስት' እያለ ሲሳደብ የኖረ ሲቪል ለእኔ ግድ
ይሰጠዋል?
ሲሰድበኝ ኖሮ እንደገና ሲጨንቀው 'ትታችሁ መጥታችሁ ሀገራችንን
አስወሰዳችሁ' እያለ ከሚያወራ ቀባጣሪ ምን ይጠበቃል? . . .
አገሬን ነክተውብኝ ጮኼ የተነሳሁ ነኝ። ምርምር አላደርግኩም።
ተማርን እንደሚሉት አገሬን በቃላት ነዝንዤ በፉክክርና በምቀኝነት
ለጠላት አልሰጠሁም። ጠላቷ እንዲደፍራት የእናቴን ቀሚስ ወደ
ላይ አልሰበሰብኩም። ደፋሪው የልጆቿን ታሪክ ሰምቶ ሲርበተበት፣
ሊደፍራትም ሲፎክር 'አይዞህ' ብዬ የሱሪውን አዝራር
አልፈታሁለትም።
እኔ የፊት በር ስዘጋ የጀርባ በር ከፍተው፣ ጠላታቸውን አገራቸው
እልፍኝ አስገብተው፣ እናታቸው ተከናንባ የተኛችበትን ብሉኮ
ገፈው፣ 'ይቻትልህ' እንዳሉት አጅሬዎች አይደለሁም . . .
ከርሞ ከርሞ መቆየት ደጉ፤ ጠላ እየጠጣሁ እዛ አለማያ ኮሌጅ
የሚያማምሩ ለጋ ወጣቶች ሳይ በልቤ 'ለመሆኑ ለእነሱ እግሬ
እንደተሰነከለ፣ ዐይኔ እንደጠፋ፣ ሳንባዬ በብርድ እንደታመመ
ይገባቸዋል? እላለሁ . . .
ወሰናቸውን ስጠብቅላቸው አካሌን ባጎድልም፤ ከምንም
የማይቆጥሩኝ መዓት ናቸው። ድሮ በቆራጡ ዘመን ሀገር ለማዳን
ስንረባረብ፣ ዛሬ ምን የመሰለ የሚያምር ጫማ ለመግዛት ሲሻሙና
ሲያብዱ አያለሁ። እዛም ጥጥና ጎማ የሚሸት ጫማቸው ስር
ያልታዘነለት ተሸናፊ ነኝና አፈር እየተነፈስኩ፣ አስፋልት እየላስኩ
እርመጠመጣለሁ።
ከጫማቸው የረከስኩ ነኝ . . .
የጀልዴሳን አወዳይ ጫት በጎልማሳነቴ ከዚያድ ባሬ መንጋጋ
አላቅቄ እነሱ አፍ አስገብቼ፣ ይኸው መርቅነው በፈዘዙ አይኖቻቸው
እያዩ ጣል ጣል ያደርጉኛል . . .
እገረማለሁ?
.
.
ኧረ አልገረምም!
ክርስቶስን የከዳው አብሮት ቂጣ የቆረሰ እኮ ነው።
ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም ቢሉ ዕውነት አለው።
***
# የስንብት_ቀለማት