የክርስቶስ አካል የተገነዘበት ጨርቅ እንደሆነ ሲነገር የኖረው የቱሪን ከፈን (Shroud of Turin) ዕድሜው 2000 ዓመታት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ጥናት ይፋ ሆኗል። በዚህ ጨርቅ ላይ የሚታየው በዘመናዊ ካሜራ ቴክኖሎጂ ሊፈጠር የሚችለው ኔጌቲቭ ምስል የአንድ ከመስቀል የወረደ እጆቹና እግሮቹ የተቸነከሩ ሰው ትክክለኛ ምስል ሲሆን ምስሉ እንዴት እንደተፈጠረ ባይታወቅም ጨርቁ በመካከለኛው ዘመን የተዘጋጀ እንደሆነ በካርበን ዴቲንግ እንደተረጋገጠ ሲነገር ነበር የቆየው። አንዳንድ ምሑራን ለምርመራ የተወሰደው የጨርቁ ክፍል ከቃጠሎ በኋላ በመካከለኛው ዘመን በጨርቁ ላይ የተጣፈ እንጂ ዋናው ጨርቅ አለመሆኑን ቢናገሩም ሰሚ አላገኙም። አሁን በተደረገ አዲስና ልዩ ምርመራ ግን ትክክለኛ ዕድሜው እንደተረጋገጠ እየተነገረ ይገኛል። ይህንንም ዜና የዓለም ሚድያዎች እየተቀባበሉት ይገኛሉ። በርግጥ ቀደም ሲል የካርበን ምርመራው ዕድሜውን ቢያሳንስም በጨርቁ ላይ የተገኙት የዕፅዋት ቅሪቶች በመጀመርያው ክፍለ ዘመን በምድረ እስራኤል የሚበቅሉት እንደሆኑ ጥናቶች አሳይተዋል። በአሁኑ ወቅት በዚህ አዲሱ ግኝት የዓለም ተመራማሪዎች ግራ እየተጋቡ ይገኛሉ። ምርመራውን ካደረጉት ተመራማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው እንግሊዛዊው ዴቪድ ሮልፍ ቀደም ሲል አምላክ የለሽ ቢሆንም ከግኝቱ በኋላ ክርስትናን ተቀብሏል። https://www.mirror.co.uk/news/world-news/athiest-who-set-out-prove-33507055
እነዚህን ሊንኮች ተመልከቱ፦
https://www.thesun.co.uk/tech/29974040/scientists-shroud-of-turin-evidence-imprint-jesus/
https://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-13758359/scientists-discovery-jesus-cloth-buried-shroud-turin.html
https://inews.co.uk/news/shroud-of-turin-real-jesus-evidence-3237452?ico=related_stories&srsltid=AfmBOorh55zRCT6hXE8xrWBdssAidQpho2uSCOKw265PtB5zF48vq_FP
ዋናው የጥናቱ ውጤት እዚህ ይገኛል፦
https://www.mdpi.com/2571-9408/5/2/47#